BBC News, አማርኛ - ዜና
ዜና
የጂቡቲው ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ስድስተኛው የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆኑ
ተቀራራቢ ፉክክር በተካሄደበት ምርጫ የጂቡቲው ዕጩ ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ስድስተኛ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ። ከኬንያው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የተቃዋሚ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ጋር ለስድስት ዙር በተካሄደ የምርጫ ሂደት የጂቡቲው ተወካይ አሸናፊ ሆነዋል።
የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ሥልጣን፣ ደመወዝ፣ እና ጥቅማ ጥቅሞች ምንድን ናቸው?
ሙሳ ፋኪ መሐማት የሁለት ዙር የሥልጣን ዘመናቸው ተጠናቅቆ ቦታቸውን ለአዲስ ሊቀመንበር ለማስረከብ ዛሬ ምርጫ ይካሄዳል። የሥልጣን ዘመናቸው ያበቃውን ሙሳ ፋኪ ማሐማትን ለመተካት የኬንያው ራይላ ኦዲንጋ፣ የጂቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የቀድሞው የማዳጋስካር ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪቻርድ ራንድራያማንድራቶ ይፎካከራሉ። የአህጉራዊው ድርጅት ሊቀመንበር ደመወዝ ስንት ነው? ምን ጥቅማ ጥቅምስ ያገኛል?
የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ነጻ ንግግር እና ስደትን አስመልክቶ አውሮፓውያን መሪዎችን ወረፉ
የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ በአውሮፓ ዲሞክራሲ ላይ ከፍተኛ ስጋት የጋረጡት ሩሲያ እና ቻይና ሳይሆኑ "ከውስጥ የመነጨ ነው" ሲሉ ጠንከር ያለ ወቀሳ ሰንዝረዋል።
የተከፋፈሉት የህወሓት አመራሮች ለፖለቲካ ግቦቻቸው "ኃይል ላለመጠቀም" መፈራረማቸው ተገለጸ
ክፍፍል እና እሰጣገባ ውስጥ ያሉት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አመራሮች የፖለቲካ ግቦቻቸውን ለማሳካት "ኃይልን ላለመጠቀም" መፈራረማቸውን የትግራይ የሃይማኖት አባቶች ይፋ አደረጉ። ለሁለት የተከፈለው ህወሓት አመራሮች የሆኑት የአቶ ጌታቸው ረዳ እና የዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ፊርማ ያረፈበት ይህ ሰነድ፣ አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ "የበላይነት ለማረጋገጥ ወደ ማንኛውም ዓይነት የአመጽ ተግባር" እንደማይገቡ የሚገልጽ ነው።
ታዋቂው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሙዚቀኛ በቪዲዮ ቀረጻ ላይ ተገደለ
ታዋቂው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሙዚቀኛ አማጺያኑ በተቆጣጠሯት ጎማ ከተማ በሙዚቃ የቪዲዮ ቀረጻ እያከናወነ ባለበት ወቅት ተገደለ። ሙዚቀኛው ኤም23 የተሰኙት የኮንጎ አማጺያን ከተማዋን መቆጣጠራቸውን የሚያወግዝ ዘፈን በቅርቡ ለቆ ነበር።
በሕንድ ሚስቱን ደፍሮ ለሞት ዳርጓል በሚል የተከሰሰው ግለሰብ በነጻ መለቀቁ ቁጣን ቀሰቀሰ
በሕንድ ባለቤቱን በመድፈር እና ከተፈጥሮ ውጪ የግብረ ስጋ ግንኙነት በመፈጸም ወንጀል ተከስሶ የተፈረደበት ግለሰብ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ በነጻ መለቀቁ ቁጣን ቀሰቀሰ።
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
አነጋጋሪ ጉዳይ
በአዲስ አበባ ብዙ ሰዎች 'የቫይታሚን ዲ' እጥረት አለባችሁ የሚባሉት በስህተት ነው?
ኸዲጃ እና ሪሐና እህትማማቾች ናቸው። ሁለቱም በተለያየ ምክንያት፣ በተለያዩ ቀናት ሐኪም ጎብኝተው ሁለቱም የቫይታሚን-ዲ እጥረት አላባችሁት ተባሉ። በሥራ ቦታ የሚያውቋቸው ሌሎች በርካታ ሰዎችም እንዲያ መባላቸውን ስለሚያውቁ ተገረሙ። ነገር ግን ሁኔታውን ከምር አልወሰዱትም፤ እንዲሁ ባለሙያዎቹ በዘፈቀደ 'የለጠፉባቸው እጥረት' አድርገው ወሰዱት። የጤና ባለሙያዎች ግን ነገሩ ወዲህ ነው ይላሉ።
ባለፈው ዓመት የጸደቀው የኢሚግሬሽን አዋጅ ወደ ኢትዮጵያ ስለሚገቡ መንገደኞች ምን ይላል?
በአሜሪካ የቆዩት ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው ወደ አገር ቤት እንዳይገቡ መከልከላቸውን መግለጻቸውን ተከትሎ ባለፈው ዓመት የተሻሻለው የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አዋጅ መነጋገሪያ ሆኗል። ለመሆኑ ይህ አዋጅ ወደ ኢትዮጵያ ስለሚገቡ እና ከኢትዮጵያ ስለሚወጡ ተጓዦች ምን ይላል?
የዓመቱ የአገራት የሙስና ደረጃ ሪፖርት፤ ኢትዮጵያ በስንተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች?
በዓለም ላይ በሕዝባዊ አገልግሎቶች ዘርፍ ያለውን የሙስና ሁኔታ እየተከታተለ ዓመታዊ ሪፖርት የሚያወጣው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በተጠናቀቀው የአውሮፓውያኑ 2024 ዓመት የአገራትን የሙስና ደረጃን ይፋ አድርጓል። ሪፖርቱ የ180 የዓለም አገራትን የሙስና ደረጃ ያወጣ ሲሆን ከፍተኛውን ነጥብ በማግኘት ሙስና በጣም በዝቅተኛ ደረጃ የሚገኝባቸው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እና ግጭት የሌለባቸው አገራት ሲሆኑ፣ ሙስና ሥር የሰደደባቸው ደግሞ ግጭት እና ቀውስ ያለባቸው አገራት መሆናቸውን አመልክቷል።
ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው "ወደ ሀገሬ እንዳልገባ ተከልክያለሁ" አሉ
በአሜሪካ የነበሩት ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው "ወደ ሀገሬ እንዳልገባ ተከልክያለሁ" ሲሉ ወደ ኢትዮጵያ መጓዝ እንዳልቻሉ ለቢቢሲ ተናገሩ። ነገር ግን ይህ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሊያደርጉት የነበረው ጉዞ በኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል እንደጣለባቸው የተገለጸላቸው የጉዞ ዕገዳ ቢኖርም፣ በሌላ ሀገር አየር መንገድ አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚጓዙ ገልጸዋል።
የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ከሠራተኞች ደመወዝ የፓርቲ አባልነት መዋጮ እንዳይቆርጡ የሚከለክል ረቂቅ ሕግ ተዘጋጀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የፖለቲካ ፓርቲ አባልነት መዋጮን ከሠራተኞቻቸው ደመወዝ ላይ "በቀጥታ" እየቆረጡ ለፓርቲዎች እንዳያስገቡ የሚከለክል ረቂቅ ሕግ አዘጋጀ። ረቂቁ ሕጉ፤ በሁሉም አካባቢዎች በተመሳሳይ ጊዜ ጠቅላላ ምርጫ ማካሄድ በማይቻልበት ጊዜ ምርጫው "በተለያየ ጊዜ" ሊካሄድ እንደሚችልም ይደነግጋል።
"በፍፁም የማያላውስ ነገር ካለ ወደ ግል ሥራዬ እመለሳለሁ" አዲሱ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር አቶ ብርሃኑ አዴሎ
አዲሱ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር አቶ ብርሃኑ አዴሎ ሥራቸውን በጫና ምክንያት መፈፀም ካልቻሉ እንደሚለቁ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ዋና ኮሚሽነሩ ኃላፊነቱን በተረከቡ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ከ10 ዓመት በፊት ስለተሰናበቱት ፖለቲካ ጉዟቸው፣ በኢሰመኮ ምን ሊሠሩ እንዳሰቡ እና ሌሎች ጉዳዮችንም ዳሰዋል።
በአምስት ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ ምን ያህል ጨመረ?
ባለፉት አምስት ዓመታት የነዳጅ ዋጋ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል። መንግሥት በየወሩ መጀመሪያ ላይ በአገሪቱ የሚኖረውን የነዳጅ መሸጫ ዋጋን ይፋ ያደርጋል። ይህ ተመንም አንዳንድ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ ጭማሪ ሲያሳይ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ባለበት ሲቀጥል፣ ነገር ግን አስካሁን ሲቀንስ አልታየም። ባለፉት ዓመታት በአገሪቱ የታየው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ከፍተኛ መሆኑ፣ በሁሉም ምርት እና አገልግሎቶች ላይ ተንጸባርቋል። የነዳጅ ዋጋ በአምስት ዓመታት ውስጥ ከየት ተነስቶ የት ደረሰ?
ከየፈርጁ
የሰው ልጅ ለአንድ ዓመት በማርስ ላይ ቢቆይ ኑሮው ምን ሊመስል ይችላል?
ከጥቂት አስርት ዓመታት በፊት ወደ ቀይዋ ፕላሌት ማርስ የሚደረግ ጉዞን በልቦለድ ፊልሞች ብቻ የምንመለከተው ነገር ነበር። ዛሬ ላይ ቴክኖሎጂ ዘምኖ፤ የተመራማሪዎች እውቅት እና ፍላጎት ዳብሮ ወደ ማርስ የሚደረግ ጉዞ እውነት ሊሆን የሚችልበት ሁኔታ አለ። ለዚህም ቅድመ ዝግጅት በሚመመስል ሁኔታ የሰው ልጅ ወደ ማርስ ለመጓዝ ቢነሳ ረዥሙን ጉዞ እና ተስማሚ ባልሆነ ቦታ መኖርን ለማላመድ አራት ሰዎች በማርስ አምሳያ ወደተሠራ ቦታ ከዓመት በፊት ተልከው ነበር።
የምታጌጥበትን ወርቅ ሸጣ የኦቲዝም ማዕከል የከፈተችው እናት
ኢማን ትኖርበት ከነበረው ሳዑዲ አረቢያ ቤተሰብ ለመጠየቅ ወደ ኢትዮጵያ በሄደችበት ወቅት ያየችው ታዳጊ ሁኔታ ነበር ማዕከሉን እንድትከፍት ምክንያት የሆናት። ማዕከሉን ለመደገፍ ያላትን ሁሉ አሟጣ ማጌጫ ወርቋን ጭምር እስከመሸጥ ደርሳለች። ማዕከሉ ከተከፈተ አጭር ጊዜ ቢሆንም አገለግሎቱን ለማግኘት ከትግራይ እና ከአፋር ጭምር ልጆቻቸውን ያመጡ ወላጆች አሉ። በአሁኑ ወቅት 40 ለሚሆኑ ኦቲዝም ላለባቸው ልጆች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
በፕሬዝዳንት ትራምፕ ዕቀባ የተጣለበት ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ሥራው ምንድን ነው?
መቀመጫውን ዘ ሄግ ኔዘርላንድስ ያደረገው ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት (አይሲሲ) የአሜሪካ ወዳጅ የሆኑት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ጋዛ ውስጥ የጦር ወንጀሎች እንዲፈጸሙ አድርገዋል በሚል ከወራት በፊት የእስር ማዘዣ አውጥቶባቸዋል። አሁን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ ሥልጣን ከተመለሱ ከጥቂት ሳምንት በኋላ ውሳኔን በመቃወም በፍርድ ቤቱ ላይ ዕቀባ ጥለዋል። ለመሆኑ ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ምን ያህል አቅም አለው?
ወላጆችን እያሳሰበ ያለው ከ6 ዓመት ጀምሮ ያሉ ታዳጊዎች የወር አበባ እንዲያዩ የሚያደርጉ ምክንያቶች
ዕድገት በሴቶች ወይም በወንዶች ሰውነት ውስጥ ያለ ሂደት ሲሆን፣ ይህም የመራቢያ አካላትን ያካትታል። ይህ የዕድገት ለውጥ በሴቶች ላይ ከ8 ዓመት እስከ 13 ድረስ፣ በወንዶች ላይ ደግሞ ከ9 ዓመት እስከ 14 ድረስ ይስተዋላል። በልጆች ላይ ለሚታየው የዕድገት መፍጠን ምክንያቱ ምንድን ነው?
ቻትጂፒቲን 'ያስናቀው' ዲፕሲክ እንዴት በኢትዮጵያ ቋንቋዎች 'ጎበዝ' ሆነ? ዓለምን ያስደነገጠበት ምሥጢርስ ምንድን ነው?
ከሳምንታት በፊት ነበር የቻይናው ሰው ሠራሽ አስተውሎት ተቋም ዲፕሲክን የለቀቀው። መተግበሪያው ለአገልግሎት ከበቃ በኋላ ማሻሻያ ተደርጎበት በዚህ ሳምንት ያልተጠበቀ የቴክኖሎጂ 'አብዮት' ፈንድቷል። ቻይና ሠራሹ ቻትቦት በአማርኛ፣ በኦሮምኛ እና በትግርኛ ከሌሎች መሰል ቻትቦቶች በተሻለ አገልግሎት እንደሚሰጥ እየተነገረለት ነው። ዲፕሲክ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን ከሌሎች መተግበሪያዎች በተሻለ የሚገነዘበው በምን መንገድ ነው? ዓለምንስ ድንገት ያናወጠው ለምንድን ነው?
"...ይጨክናሉ ብዬ አላሰብኩም ነበር" ሁሉን ነገር ጨርሶ ከነቤተሰቡ ወደ አሜሪካ የመሄድ ዕድሉ የጨነገፈበት ኢትዮጵያዊ
ዶናልድ ትራምፕ ሥልጣን በጨበጡ በሰዓታት ውስጥ ስደተኞችን የሚያሳድድ እና ከአሜሪካ የሚያርቅ እርምጃ እየወሰዱ ነው። በርካቶች እየታደኑ እየተያዙ ሲሆን፣ ወደ አሜሪካ ለመግባት የሚጠባበቁት ደግሞ በዚያው እንዲቀሩ የሚያደርግ እርምጃ እየተወሰደ ነው። ጦርነት ሽሽት ከነቤተሰቡ በስደት ላይ የሚገኘው ብርሃነ ሁሉን ነገር ጨርሶ ከሳምንት በኋላ ወደ አሜሪካ ለማቅናት እየተዘጋጀ ሳለ ጉዞው መሰረዙ ተነግሮታል። ታሪኩን እነሆ. . .
አጃኢብ!
የሽንታችን ቀለም ስለጤናችን ምን ይነግረናል? ምን ዓይነት ቀለም ሲኖረው ነው ሊያስጨንቀን የሚገባው?
የሸንታችን ቀለም ስለጤናችን ብዙ ይነግረናል። ለዚህ ነው የጤና ባለሙያዎች “የሽንታችሁ ቀለም እንዴት ያለ ነው?” ብለው የሚጠይቁት። እኛም የጤናችንን ሁኔታ በቅርበት ለመከታተል የሽንታችንን ቀለም ልብ ብለን መመልከት እና ለሐኪም ማሳወቅ ያስፈልጋል። እስቲ ዋና ዋና የሚባሉት በሽንታችን ላይ የሚከሰቱ ቀለማት እና የምን ምልክት ሊሆኑ እንደሚችሉ እንመልከት።
የስሪላንካ ሚኒስትር ለመብራት መቋረጥ አንድ 'ዱርዬ' ዝንጀሮን ተጠያቂ አደረጉ
የስሪላንካ ሚኒስትር በአገሪቱ ለመብራት መቋረጥ አንድ 'ዱርዬ' ዝንጀሮን ተጠያቂ አደረጉ
ስለቴስላ ሳይበርትራክ የሚታወቁ ዋና ዋና እውነታዎች
የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ቴስላ ሳይበርትራክ ሲል ስያሜ የሰጠውን መኪናውን በአውሮፓውያኑ 2019 ነበር ያስተዋወቀው። መኪናው በኤሌክትሪክ የሚሠራ ነው።
በጸሎት ትፈወሳለች በሚል ታዳጊዋን የስኳር በሽታ መድኃኒቷን ያስተዉ አማኞች በነፍስ ማጥፋት ጥፋተኛ ተባሉ
የስምንት ዓመቷን የስኳር ህመምተኛ ታዳጊ ለአንድ ሳምንት ያህል የሚያስፈልጋትን ኢንሱሊን የተባለውን መድኃኒት በመከልከል ህይወቷ እንዲያልፍ ምክንያት ሆነዋል የተባሉ 14 የአውስትራሊያ የሃይማኖት ቡድን አባላት ጥፋተኛ ተባሉ።
'ከአስከሬን ጋር መሥራት ትሑት ያደርጋል' የምትለው የአስከሬን መርማሪ
ዶ/ር ቫሱ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ የአስከሬን ምርመራ አድርጋለች። በዚህ ዘመን ውስጥ 20 ሺህ ገደማ አስከሬኖችን መርምራለች። በዚህ ጊዜ ውስጥ የተፈጸሙ ወንጀሎችን የሚያጋልጡ ምርመራዎችን የሟች ቤተሰቦችን ጥያቄ የሚመልሱ ምረምራዎችን አከናውናለች።
አሜሪካዊቷ ታዳጊ በቲክቶክ ቪዲዮዎች ምክንያት በፓኪስታን በአባቷ በጥይት ተገደለች
በቅርቡ ቤተሰቡን ከአሜሪካ ወደ ትውልድ ስፍራው ፓኪስታን የወሰደው አባት ታዳጊ ልጁ በቲክቶክ ላይ በምትለጥፋቸው ቪዲዮዎች ምክንያት በጥይት መግደሉን ማመኑን ፖሊስ ለቢቢሲ ገለጸ።
የዓለም 'መጥፊያ ሰዓት' ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ወደ መጨረሻው እየተቃረበ መሆኑ ተገለጸ
የሰው ልጆችን የመጥፊያ የምጽዓት ሰዓትን ለመጠቆም በተምሳሌትነት የተቀመጠው ሰዓት አንድ ሰከንድ የቀነሰ ሲሆን፣ በዚህም የዓለም መጥፊያ ጊዜ ከመቼው በበለጠ ወደ መጨረሻው እየተቃረበ ነው ተብሏል።
የተመለሱ ጥያቄዎች
በልምምድ የሚዳብረው በርካታ ፈዋሽ ጠቀሜታ ያለው የአተነፋፈስ ጥበብ
የአተነፋፈሳችን ሁኔታ በጤናች ላይ የራሱ የሆነ ውጤት አለው። የተለያዩ የአተነፋፈስ ዘዴዎችን በመጠቀም በሰው ልጆች ጤና ላይ ለውጥ ማምጣት በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት የታወቀ ነው።
ከናዚ ጭፍጨፋ የተረፉ የኦሽዊትዝን 80ኛ ዓመት መታሰቢያ ለማክበር በማጎሪያ ካምፑ ተገኙ
ከናዚው የሞት ጣብያ ኦሽዊትዝ-ቤርከናው በሕይወት የተረፉ 50 ያህል ሰዎች የማጎሪያ ካምፑ ነጻ የወጣበትን ዕለት ለማሰብ ሰኞ፣ ጥር 19/ 1937 ወደ ስፍራው ተመልሰዋል።
የፋሲል ግንብ እድሳት እንዴት ተካሄደ? የመንጣቱ ምክንያት ምንድን ነው?
የጥገና እድሳት እየተከናወለት ያለው ታሪካዊው የፋሲል ግንብ በቅርቡ ይፋ መደረጉን ተከትሎ መወዛገቢያ መሆኑ አልቀረም። ታሪካዊው ሽሯሟ ቀለም ያለው የፋሲል ግንብ ቀለሙ ነጥቶ መታየቱ ለበርካታ መላምት ክፍት እንዲሆን አድርጎታል። የታሪካዊው ግንብ ቀለም ለዘመናት ከሚታወቅበት ተለውጦ ለምን ነጣ? የሚል ጥያቄ እንዲነሳም ምክንያት ሆኗል።በጥገና እድሳቱ በአማካሪነት እንዲሁም በጥናት የተሳተፉት አንጋፋው አርክቴክት ፋሲል ጊዮርጊስ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ ለጉዳዩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ከልክ ያለፈ ውፍረት (ኦቤሲቲ) ምንድነው? ትርጉሙስ እንደገና ሊጤን ይገባል?
በዓለማችን ከአንድ ቢሊዮን በላይ የሚሆነው ሕዝብ ከመጠን በላይ የሆነ ውፍረት (ኦቤሲቲ) አለባችሁ መባላቸውን ተከትሎ ይህ የክብደት አገላለጽ አዲስ ትርጉም እንደሚያስፈልገው ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች የተሳተፉበት አዲስ ሪፖርት አጽንኦት ሰጠ።
የነዳጅ መኪኖችን አስቀርታ የኤሌክትሪክ መኪኖችን በመጠቀም ቀዳሚ የሆነችው ኖርዌይ
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም ኖርዌይ በዓለማችን ቁንጮ ስፍራ ላይ ተቀምጣለች። ባለፈው ዓመት በአገሪቱ ካሉ አስሩ መኪኖች ዘጠኙ የኤሌክትሪክ መኪኖች መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ። ሌሎች አገራት ከኖርዌይ ምን መማር ይችላሉ?
በቻይና ስለተከሰተው አዲስ ቫይረስ ምን እናውቃለን?
ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በቻይና በሚገኙ ሆስፒታሎች ጭምብል ያጠለቁ በርካታ ሰዎች ፎቶ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ መሠራጨቱ ሌላ ወረርሽኝ ተከስቶ ይሆን የሚል ስጋትን አስከትሏል። ከጉንፋን ጋር የሚመሳሰለው 'ሂውማን ሜታኒሞቫይረስ' (ኤችኤምፒቪ) በተለይም በልጆች ላይ በስፋት መከሰቱን ቤይጂንግ አምናለች። የተከሰተውም ከወቅቶች መቀያየር ጋር ተያይዞ መሆኑንም ገልጻለች።
ፕላስቲክ የሚያብላሉት የአፍሪካ ነፍሳት
ዶ/ር ፋቲያ ካሚስ ናይሮቢ ውስጥ በሚገኝ ቤተ ሙከራ ምርምር እያደረገች ነው።እሷ የምትመራው ቡድን ፕላስቲክ የሚበላ ነፍሳት ላይ ነው ጥናት የሚሠራው። "ጠዋት ስንገባ ሁላችንም ደስ አለን። ፕላስቲኩ ተፈርፍሯል" ትላለች።ጥቁሩ ነፍሳት ፕላስቲኩን መብላቱ ትልቅ ድል ነው። ነፍሳቶቹ ፕላስቲኩን ከበሉ በኋላ ማብላላት ይችላሉ።
በኢራን አስከፊ እስር ቤቶች ውስጥ የሚማቅቁት ሴቶች ሕይወት ምን ይመስላል?
ናሲም ስቃይ ከሚያደርሱባት ሰዎች ውጭ ሌላ ሰው አይታ አታውቅም። ብዙ ጊዜ “በቃ እዚህ ሞቼ ማንም ሳያውቀው ተረስቼ ልቀር ነው?” ብላ ታስባለች። በአስከፊው ኢቪን እስር ቤት ሕይወት ለናሲም እና ለሌሎች ሴት እስረኞች ምን ይመስላል?
ሌላ ዕይታ
ከማኅደራችን
“ሰው መሃል ሆኜ ሁሉም ጨካኝ ሆኖብኝ ነበር” - የፀጋ በላቸው ዘጠኝ የጠለፋ ቀናት
ግንቦት 2015 ዓ.ም. የተፈጸመው የፀጋ በላቸው ጠለፋ ብዙዎችን ያስቆጣ፣ መነጋገሪያም የሆነ የወንጀል ድርጊት ነበር። ፀጋ፤ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት ተጠልፋ ያሳለፈቻቸውን ቀናት በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቢቢሲ በዝርዝር ተናግራለች። ከቢቢሲ ጋር በነበራት ዘለግ ያለ ቆይታ፤ ስለተጠለፈችበት መንገድ እና ስላሳለፈቻቸው ዘጠኝ ቀናት በዝርዝር ተርካለች። ከጠለፋው ነጻ የወጣችበት መንገድም አስቀድሞ በክልሉ መንግሥት ከተገለጸው የተለየ እንደሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናግራለች። ለምን ከኢትዮጵያ እንደተሰደደች እና ስለ ቀጣይ ዕቅዶቿም እንዲሁ አጋርታለች።
ሙዝ በዳቦ እየበሉ 'ፒኤችዲ' የሚማሩ የዩኒቨርስቲ መምህራን ሰቆቃ
ይህ ጥናታዊ ዘገባ የዩኒቨርስቲ መምህራን ላይ ያጠነጥናል፤ ከእነርሱም ውስጥ ፒኤችዲ (ዶክትሬት) የሚማሩት ላይ ያተኩራል። መምህራኑ የበለጠ በተማሩ ቁጥር የበለጠ እየተራቡ እንደሆነ ያወሳሉ። ቢቢሲ በርከት ያሉ የፒኤችዲ ተማሪዎችን ለወራት ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ ቆይቷል። ከጉዳዩ ስፋት የተነሳ የብዙዎቹ አስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ እና ታሪክን በሚወክሉ በአምስት መምህራን ተወክሎ ቀርቧል።
"ብልጽግናዎች ይዘውን እንዲጠፉ አንፈቅድም፤ አገራችን ሕዝባችን ነው፤ ዝም አንላቸውም" - ጃዋር መሐመድ
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ካላቸው ፖለቲከኞች መካከል ጃዋር መሃመድ አንዱ ነው። ለዓመታት ያህል በኦሮሚያ የነበሩ ትግሎችን እንዲሁም ተቃውሞዎችን ከጀርባም ሆነ ከፊት ሆኖ በማስተባበር እና በመምራት ግንባር ቀደም ነው።የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ አመራሩ ጃዋር ከትውልድ አንስቶ በፖለቲካ ህይወቱ የተጓዘበትን ህይወቱ ላይ የሚያጠነጥን 'አልጸጸትም' የተሰኘውን መጽሐፍ ታህሳስ 10/ 2017 ዓ.ም በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ያስመርቃል። ጃዋር መሃመድ በአገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ፣ በቀጣይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ስለሚኖረው ሚና፣ አገሪቱ ስላለችበት ሁኔታ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ቆይታ አድርጓል።
ቪዲዮ, በአርሰናል ‘ፍቅር የወደቁት’ የ65 ዓመቷ እናት፡ ወይዘሮ እቴቱ ማሞ, ርዝመት 3,29
ከእንግሊዝ ታላላቅ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው የአርሰናል የልብ ደጋፊ የሆኑት ወ/ሮ እቴቱ ማሞ የ65 ዓመት እናት ናቸው። ላለፉት 20 ዓመታት አርሰናልን ያለማቋረጥ ደግፈዋል። እንደብዙዎቹ የቡድኑ ደጋፊዎች ዘንድሮ አርሰናል ዋንጫ ባለማንሳቱ ቢከፉም ድጋፋቸው ግን እንደሚቀጥል ይናገራሉ። ከሁሉም ተጫዋቾች ይልቅ እሳቸው ገብረኢየሱ ለሚሉት ለጋብሬል ጀሱስ እና ለቡካዮ ሳካ የተለየ ፍቅር አላቸው።
ለአራት ዓመታት ከኢንዱስትሪ ፓርክ ሠራተኞች ጋር በመኖር የተቀረጸው ፊልም፡ ‘ሜድ ኢን ኢትዮጵያ’
የዘጋቢ ፊልሙ ደራሲ እና አዘጋጆች ማክስ ደንካን እና ዘንየን ዩ ናቸው። ከፕሮዲውሰሮቹ አንዷ ታማራ ማርያም ዳዊት ናት። ‘ሜድ ኢን ኢትዮጵያ’ በዋርሶው ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል፣ በትሪቤካ ፊልም ፌስቲቫል፣ በሼፊልድ ኢንተርናሽናል ዶክመንተሪ ፌስቲቫል እና በሌሎችም ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫሎች ላይ ዕውቅና አግኝቷል። ፊልሙ የቻይና ባለ ሃብቶች ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት፣ ሥራ አጥነትን፣ ባህልን፣ ቤተሰብን፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት እና የአርሶ አደሮች የተጠቃሚነት ጥያቄን በዋናነት ይዳስሳል።
የሳንቲም ትዝታዎች - ፕሮፌሰር እሌኒ ዘለቀ ስትታወስ
“ሐኪሞቹ ‘ሰዓት አልቋል’ አሉ። በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ይቺን ምድር እሰናበታለሁ።” እነዚህ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ፕሮፌሰር እና የፖለቲካ ሳይንቲስት እሌኒ ሳንቲም ዘለቀ ቃላት ናቸው። ፕሮፌሰር እሌኒ ይህን መልዕክት በማኅበራዊ ትስስር ገጿ ካስተላለፈች አንድ ሳምንት በኋላ ኒው ዮርክ በሚገኘው ኢስት ኢንድ ሆስፒስ ውስጥ ሕይወቷ አልፏል። ተማሪዎቿ፣ ወዳጆቿ እና የሚያውቋት እሌኒን እና ሥራዎቿን ዘክረዋል።
በቲክቶክ ዘመን ቆዳ አልፍተው፣ ብራና ወጥረው፣ ቀለም በጥብጠው ግዕዝ የሚማሩት የአዲስ አበባ ሕጻናት
አዳጊዎች ናቸው፤ የተገፈፈ የፍየል ቆዳ ያለፋሉ። ይደጉሳሉ። ይጠርዛሉ። ካራ፣ ጉጠት፣ መጥረቢያ. . . ተጠቅመው ቆዳ ያለሰልሳሉ። ቀጨም ተጠቅመው ብራና ይወጥራሉ። ይህን ሁሉ የሚሠሩቱ ርቆ ከሚገኝ መንደር ያሉ ቆሎ ተማሪዎች አይደሉም፤ ዘመናይ ከተሜዎች እንጂ። አንዳንዶቹ የቦሌ እና የካዛንቺስ ልጆች፤ አንዳንዶቹ የሳር ቤት እና የሲኤምሲ ተወላጆች ናቸው። ደግሞ ይህ ሁሉ የሚሆነው ደግሞ መሀል ፒያሳ ላይ ነው።
የኩላሊታችንን ጤና ለመጠበቅ የሚያግዙ 6 ቀላል መንገዶች
በኢትዮጵያ በስፋት እየተስተዋሉ ከሚታዩ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች መካከል የኩላሊት ችግር አንዱ እየሆነ መጥቷል። ወሳኝ ከሆኑት የሰውነት ክፍሎች መካከል አንዱ የሆነው ኩላሊት በተለያዩ ምክንያቶች እክሎች ይገጥሙታል። ነገር ግን የአኗኗር ዘይቤን በመቀየር እና ጥንቃቄ በማድረግ ጤናማ ኩላሊት እንዲኖረን ማድረግ ይቻላል። ከእነዚህም መካከል ለኩላሊት ጤና የሚረዱ ስድስት ቀላል ጥንቃቄዎችን እነሆነ. . .
የላጤዎች ጉባኤ በቦሌ
በፈረንጅ አፍ ‘ስፒድ ዴቲንግ’ ይባላል። የአማርኛ አቻ የለውም። በአቋራጭ መተጫጨት ነው-ነገሩ። ፖለቲካዊ ቋንቋ ይመስልብናል እንጂ ‘የትዳር ማሳለጫ’ ሊባል ይችላል። ነገሩ ‘የፍቅር-ጉድኝት’ ለመፍጠር የሚደረግ አጭር ጉዞ ነው። የፍቅር ጓደኛ ለማግኘት አደን እንደመውጣት ያለ ነው። የትዳር አሰሳ. . . የወደፊት ውሃ አጣጭን ለማማለል የሚሰጥ የአምስት ደቂቃ ፍጹም ቅጣት ምት ነው። የት? አዲስ አበባ ቦሌ ላይ. . .
ምሥሎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት እንዴት ይሠራሉ? ከእውነተኞቹስ እንዴት መለየት ይቻላል?
በሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) አማካይነት የሚዘጋጁት ምሥሎች ለእውነታ በእጅጉ የቀረቡ በመሆናቸው ምክንያት ትክክለኛ ፎቶዎች ወይም የሰው ልጅ የአእምሮ እና የእጅ ሥራ ውጤት ከሆኑት አንጻር ለመለየት አዳጋች እየሆኑ መጥተዋል። ታዲያ በዚህ ቴክኖሎጂ የተዘጋጁትን ምሥሎች ከእውነተኞቹ እንዴት መለየት እንችላለን?
የተጠጋገኑ እና ኦሪጂናል ያልሆኑ የሞባይል ቻርጀሮች እኛንም ስልካችንንም እንደሚጎዱ ያውቃሉ?
ሊበጠስ ጫፍ የደረሰ እና የተጠጋገነ የሞባይል ቻርጅ ማድረጊያን መጠቀም ብዙዎቻችን ምንም ጉዳት የሌለው ይመስለናል። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ያልተጠበቀ ሲከፋም አሰቃቂ አደጋን ሊያስከትል ይችላል። በጥሩ ሁኔታ ላይ ያልሆኑ የሞባይል ቻርጀሮችን መጠቀም ምን ችግርን ሊያስከትሉ ይችላሉ? ምን ዓይነት ቻርጀሮችን ብንጠቀም ይመከራል?
እየፈረሰች ያለችውን አዲስ አበባ በመሰንቆ 'እየገነባት' ያለው ሀዲስ ዓለማየሁ
ሀዲስ ዓለማየሁ መሰንቆ ተጫዋች ነው። ስለ መሰንቆ አውርቶ አይጠግብም። ዓለም ሙሉ በአንዱ የመሰንቆ ገመድ ቢተሳሰርለት ምኞቱ ነው። ሀዲስ እና መሰንቆን መለያየት አይቻልም ይላል። ስሙንና የሚወደውን መሰንቆ ገምዶ ራሱን ሀዲንቆ ሲል ይጠራል። የመጀመሪያን አልበሙን በቅርቡ ለቋል። አልበሙ እየፈረሱ ባሉት ቀደምት የአዲስ አበባ ሰፈሮች እና ጎዳናዎች ትዝታ የተሞላ ነው።


















































































