ከግብር የሚሰወረው የዓለም ሃብት የት ነው?

ታክስ Image copyright Getty Images

የግብር ወይም ታክስ ኩባንያዎች የገንዘብን ፍሰትን በተለመለከተ ዋነኛ ስራቸው ነገሮችን ማጠላለፍ እና በተቻለ መጠን እውነታው እንዳይታወቅ ማድረግ ነው።

ጭንቅላታችንን እስኪያመን ድረስ ጥልፍልፍ ሂሳብ ውስጥ የሚከቱን የሂሳብ ቀማሪ ኩባንያዎች ጉግል፥ ኢቤይ እና አይኪያ የመሳሰሉ በጣም ሀብታም ድርጅቶች እጅግ አነስተኛ ግብር በህጋዊ መንገድ እንዲከፍሉ ያደርጋሉ።

ሰዎች ለምን ስለ ግብር ሲወራ እንደሚናደዱ ወይም ደስተኛ እንደማይሆኑ ግልፅ ነው።

ግብር ልክ ለአንድ ማህበር እንደሚከፈል ክፍያ ነው።

ክፍያውን አለመክፈል ብንፈለግም ማህበሩ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለመጠቀም ሲባል መክፈል ግድ ነው። የጦር ሀይል፥ ፖሊስ፥ መንገድ፥ ትምህርት እና የመሳሰሉትን አገልግሎቶች ለማግኘት ሲባል።

የግብር ማስወገድ እና ግብር ወረራ

የግብር ኩባንያዎች ለእነዚህ ሁለት አበይት ጉዳዮች ማለትም ግብር ማስወገድ እና ግብር ወረራ እጀጉን ይወቀሳሉ።

ግብር ማስወገድ ህጋዊ ሲሆን ግብር ወረራ ግን ህገ-ወጥ በሆነ መልኩ ከመንግስት እና ከሕዝብ ገንዘብ መሰወር እንደማለት ነው።

ምስጢራዊ ባንክ እ.አ.አ. በ1920ዎቹ በስዊዘርላንድ እንደተጀመረ ይነገራል።

በአንድ በኩል አብዛኛዎቹ የአውሮፓ ሀገራት በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት የነበረባቸውን ዕዳ ለመክፈል በማሰብ ግብር ያጭበረብሩ የነበረ ሲሆን በሌላ በኩል ሀብታም አውሮፓውያን ያላቸውን ገንዘብ ለመደበቂያ መንገድ ይጠቀሙበት ነበር።

ምስጢራዊ ባንክ የሚለው ኃሳብ ብዙ ደንበኛ እንዳፈራላቸው የተረዱት ስዊዞች እ.አ.አ. በ1934 ዓ.ም. ያለባለቤቱ ፍቃድ የባንክ ሂሳብ ይፋ ማድረግ ወንጀል እንዲሆን ደነገጉ።

ቀስ በቀስ የግብር ኩባንያዎች እንደ ማልታ እና ካሬቢያን ባሉ ደሴቶች ላይ ግዛታቸውን ማስፋፋት ጀመሩ።

ይሀንን የሚያደርጉበት ምክንያት መሰል ትናንሽ ደሴቶች ለግብርናም ሆነ የተለያዩ ዕቃዎችን ለማምረት ምቹ ስላልሆኑ የባንኩ ዘርፍ በጣም የተሻለ አማራጭ ሆኖ በመገኘቱ ነው።

ልዩነቱ ሲሰፋ

የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ጋብርኤል ዙክማን በባህር ዳርቻዎች ወይም በደሴቶች ላይ ምን ያህል ገንዘብ ተሰውሮ እንዳለ የሚመረምር መላ መታ።

በህጉ መሰረት ዓለም ላይ ትላልቅ የገንዘብ ተቋማት ይፋ ከሚያደርጉት መረጃ በመነሳት ተቀማጭ እና ተንቀሳቃሹ ቢሰላ የመጨረሻው ሂሳብ የተጣጣ መሆን አለበት። ማለትም ወጭና ገቢ ሂሳብ ተጣርቶ ትርፉ እና ኪሳራው መለየት አለበት።

ነገር ግን የተደረገው ጥናት ያሳየው ነገር ቢኖር እያንዳንዱ ግለሰብ ከትርፍ ይልቅ በስምንት በመቶ የበዛ ኪሳራ በሂሳብ መዝገቡ ላይ መመዝገቡን ነው።

ዙክማን ጥናቱን ሲጨርስ ስምንት በመቶ ያህል የዓለም ሃብት የት እንደገባ እንደማይታወቅ ወይንም የግብር ወረራ ሰለባ መሆኑን ተረዳ።

ከዛም አልፎ ችግሩ አዳጊ ተብለው በሚጠሩ ሀገራት ላይ የበለጠ ጎልቶ እንደሚታይ ተገነዘበ።

ከአፍሪቃ ሰላሳ በመቶ የሚሆነው ሃብት 'በባህር ዳርቻ' የተደበቀ ነው።

በግብር ስብሰባ ወቅት በአንድ ዓመት ብቻ ወደ አስራ አራት ቢሊዮን ዶላር የሚሆን ገንዘብ ተሰልቧል።

Image copyright Getty Images

የግብር ወረራ ከምናስበው በላይ በጣም ጥልፍልፍ ኃሳብ ነው።

እስቲ እርስዎ ቤልጂየም ውስጥ የዳቦ ፋብሪካ እንዳሎት እናስብ፥ የወትተ ተዋፅኦ ምርቶች ፋብሪካ ደግሞ በዴንማርክ እንዲሁም የሳንድዊች ሱቅ በስሎቬንያ። ከእያንዳንዱ ሳንድዊች ሽያጭ ላይ አንድ ዩሮ ያተርፋሉ።

እናም ከዛ ከሚያተርፉት ትርፍ ምን ያህሉ በስሎቬንያ ግብር ይከፍላሉ? ምን ያህሉስ ቺዝ በሚያመርቱበት ዴንማርክ? ምን ያህሉስ ዳቦ በሚያመርቱበት ቤልጂም? እርግጥ የሆነ ምላሽ የለም።

የሂሳብ ማታለያ መንገዶች

በዚህ ዘርፍ እንደ ትልቅ ማሳያ ተደርጎ የሚቆጠረው 'አፖክሪፋል' እየተባለ የሚጠራው ምሳሌ ነው።

በትሪኒዳድ የሚገኝ አንደ ኩባንያ እስክርቢቶ አምርቶ በሌላ ሀገር ለሚገኝ እህት ኩባንያው አንዱን አስክርቢቶ በ8500 ዶላር ዋጋ ይሸጣል።

ይህም ዝቅ ያለ ግብር በምታስገብረው ትሪኒዳድ ትርፍ እንዲያስመዘግብ በሌሎች ላቅ ያለ የግብር ምጣኔ ባላቸው ሀገራት ደግሞ ዝቅ ያለ ትርፍ እንዲያመጣ አደረገው።

እኒህን የመሳሰሉ ማታለያ መንገዶች በጣም የሚታወቁ ሲሆኑ ምን ያህል ገንዘብ እንደተጭበረበረ ለማወቅም እጀግ አዳጋች ናቸው።

ዙክማን እንደሚያምነው ከሆነ በአሜሪካ ግብር ከፋዮች እስከ 130 ቢሊዮን ዶላር የሚሆን ገንዘብ በየዓመቱ ይታለላሉ። ከዛም አልፎ በእርዳታ መልክ ወደ አዳጊ ሀገራት የሚሄደው ገንዘብ የትየለሌ ነው።

ለነዚህ የሂሳብ ማታለያ መንገዶች መፍትሄ ማበጀቱ ከባድ ባይሆንም ፖለቲካዊ ቀርጠኝነት ወሳኝ ነው ይላል ዙክማን።

መቼም የዓለም መሪዎች ይህ ጠፍቷቸው አይደለም ነገር ግን በዚህ ቀዳዳ የሚጠቀሙ ሰዎች ይህንን ለማድረግ ፈቃደኝነታቸው እጅግ ዝቅ ያለ ነው።

በጣም አነስ ያሉ ደሴቶች ምጣኔ ሀብታቸውን ለማሳደግ ሲባል በሂሳብ እና የባንክ አገልግሎት ሕጋቸው ላይ ላላ ይላሉ።

ነገር ግን ከዛም የላቀው አደጋ የግብር ኩባንያዎች የዓለማችንን ሃብታሞች፥ ፖለቲከኞች እንዲሁም ለአዳጊ ሀገራት እርዳታ የሚሰጡ ዲታዎችን ለመደገፍ ሲሉ የግብር ስርዓቱን እንዳሻቸው ያሾሩታል።

ተያያዥ ርዕሶች