ሰሜን ኮሪያ ሁለተኛውን የባለስቲክ ሚሳኤል ወደ ጃፓን አቅጣጫ አስወነጨፈች

የመጀመሪያውን ሙከራ ካደረግች ጥቂት ሳምንታት የሆናት ሰሜን ኮሪያ ሁለተኛውን የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራ ወደ ጃፓን ውቅያኖስ አቅጣጫ በማድረግ አስወንጭፋለች።

የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ሀይል እንዳስታወቀው ሰሜን ኮሪያ ያስወነጨፈችው የባለስቲክ ሚሳኤል 3700 ኪሎሜትሮችን ተጉዞ ሆካይዶ በተባለችው የጃፓን ደሴት አቅራቢያ አርፏል።