ጥበብን ከቆሻሻ

ልጅ ያሬድ እና ጓደኛው እስጢፋኖስ በከተማችን ውስጥ ያለ አንድ ጉዳይ እጅጉን ያሳስባቸዋል፤ ይህም በየቦታው ተጥለው የሚታዩት ላስቲኮችና አጥንቶች !

''ላስቲክና አጥንት በአከባቢና በሰው ልጆች ላይ የሚያስከትለውን ከፍተኛ ጉዳት እንረዳለን ለዚህም በቆሻሻ አወጋገድ ላይ ህብርተሰቡን ለማስተማር ይህን እያደርግን ነው'' ብለዋል።

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ,

የተፍጥሮ አከባቢ ተቆርቋሪ የሆኑት ጓደኛሞች ከቆሻሻ አዲስ ጥበብን እየፍጠሩ ነው!

የቆሻሻ አያያዝ፣ አጓጓዝና አወጋገድ ሥርዓት ደካማ በሆነባቸው እንደ ኢትዮጲያ ባሉ ታዳጊ ሃገራት ውስጥ የሚፍጠሩት ቆሻሻዎች በሰው ልጆች፣ በአካባቢና በእንስሳት ደህንነት ላይ ከፍተኛ አደጋን ያሰከትላሉ። የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም ሪፖርት እንደሚያሳየው በቆሻሻ ምክንያት የሚከሰተው ብክለት ለአካባቢ ደህንነት አንዱና ዋነኛው አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን አርጋግጧል፡፡

በመዲናችን አዲስ አበባም የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ሂደት ላይ የሚታየው ደካማ ሥርዓት በከተማዋ ነዋሪዎችና እንስሳት ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተጽዕኖን ፍጥሯል። የከተማዋ የአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የከተማዋን ጽዳት ለመጠበቅ የተለያዩ ጥረቶችን እያደርገ ቢሆንም የማህበርሰቡ የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ልማድ ደካማ በመሆኑ ከተማችን ለነዋሪዎቿም ሆነ ለእንስሳት ደህንነት ምቹ አይደለችም።

ልጅ ያሬድና ጓደኛው እሰጢፍኖስ የአካባቢን ንጽህና መጠበቅ የሁሉም ሃላፊነት እንደሆነ ይስማማሉ። ለዚህም ህብርተሰቡም የሚጠበቅበትን በመወጣት የአካባቢ ብክለትን እንዲቀርፍ ለማስተማር በጥበብ ሙያቸው አንድ ተግባር በመፍጸም ላይ ይገኛሉ።

ልጅ ያሬድና እስጢፍኖስ ከወዳደቁ ላሰቲኮች፣ አጥንቶችና የብረት ቁርጥራጮች የተለያዩ ሰዕሎችንና ቅርጻ-ቅርጾችን ይሰራሉ።

ልጅ ያሬድ እንደሚለው ከቆሻሻና ከአጥንት የተለያዩ ቅርጻ ቅርጾችን እየሰሩ ሰዎች ቆሻሻን በአግባቡ እንዲያሰወግዱ ለማስተማር ጥረት እያደርጉ ነው።

የምስሉ መግለጫ,

ይህ የሞተር ሳይክል ቅርፅ ከአጥንትና ተጥለው ከተገኙ ብረቶች የተሰራ ነው

እስጢፋኖስ በበኩሉ ከወዳደቁ ላስቲኮችና የብሰኩት ማሸጊያዎች የሚሰራቸው ስራዎች ህብረተሰቡ ለአጭር ጊዜ ተጠቅሞ የሚጥላቸው ላሰቲኮች የእድሜ ልክ ችግር ሊሆኑ እንደሚችሉ እንዲገነዘቡ ሊያደርጋቸው ይችላል ይላል።

የምስሉ መግለጫ,

ይህ ስዕል ከተጣሉ የብስኩት መጠቅለያ ላሰቲኮች የተሰራ ነው

''በእነዚህ ስራዎች ምንም አይነት የገንዘብ ጥቅም አናገኘም። ይህን የምናደርገው በቆሻሻ ምክኒያት የሚመጣ የአካባቢ ብክለት ሰለሚያሳስበንና ጥቅም የላቸውም ተብለው የሚጣሉ ቁሶችን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል በማሰብ ነው። ገንዘብ ብንፍልግ ሌሎች ብዙ ገንዘብ ሚያሰገኙ ነገሮችን መስራት እንችላለን'' ይላል ልጅ ያሬድ።

የምስሉ መግለጫ,

ልጅ ያሬድ ለሥራው ግብዓት የሚሆን አጥንት ሲለቅም

በሥራቸው ላይ የሚሰጧቸው አስተያየቶች አበረታች አለመሆናቸው ልጅ ያሬድን ቅር ያሰኘዋል ''ይህን ሥራ ስንሰራ መልካም አስተያየት የምናገኝ ይመስላል፤ የሚያሳዝነው ግን ብዙ ውጣ ውርዶችን እያለፍን ነው ያምንሰራው። ሰዎች አላማዬን ሳይገነዘቡ ለምን አጥንት ትለቃቅማለህ? ከቴሌቪዥን ጠፍተህ ቆሻሻ ውስጥ ለምን ትዞራለህ? መቼ ነው እንደሰው የምትሆነው ይሉኛል? ቆሻሻውን አፅድቼ ነው ንፁህ የሆነ ጥበብ የምሰራው። ሰዎች ይህንን ሊገነዘቡልኝ ይገባል። በተጨማሪም አይረቡም ከተባሉ ነገሮች ብዙ ጠቃሚ ነገር መስራት እንደሚቻል ነው ማሳየት የፈለኩት።'' ብሏል።

ልጅ ያሬድና እስጢፋኖስ እንደሚሉት ለዚህ ሥራቸው ከየትኛውም ወገን ምንም አይነት ድጋፍም ሆነ የሞራል ማበርታቻ ስለማያገኙ ተሰፋ ቆርጠው ስራቸውን ሊያቆሙ እንደሆና ተናግረዋል።

ልጅ ያሬድ ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ ላይ መስራት የጀመረ ሲሆን በ2003 ዓ.ም በሃገር አቀፍ ደርጃ የሚሰጠውን የአካባቢ ጥበቃ ሽልማት የሆነውን 'ግሪን አወርድ' አሸንፏል።