የዚህ ሳምንት እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ግምቶች

ማርክ ላውረንሰን Image copyright BBC Sport
አጭር የምስል መግለጫ ማርክ ላውረንሰን የቢቢሲ ስፖርት ተንታኝ ሲሆን የየሳምንቱን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት በማስቀመጥ ይታወቃል

ለሊቨርፑል ከ200 በላይ ጨዋታዎችን ያደረገው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን የዚህ ሳምንት የሊጉ ፍልምያዎች መጨረሻ እንዲህ ነው ሲል ከታች ባለው መልኩ አስቀምጦታል።

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከተጀመረ አምስተኛ ሳምንት ላይ ደርሰናል። እንዲያም ሆኖ ክሪስታል ፓላሶች እንኳን ነጥብ ማምጣት ጎል ማስቆጠርም ተስኗቸዋል። የሊጉን መሪ ማንቸስተር ሲቲን ቅዳሜ ዕለት የሚገጥሙት ፓላሶች ይህን ይቀይሩት ይሆን?

ላውሮ ድሉ ወደ ሲቲ እንደሚያመዝን ጠቅሶ ነገር ግን ሮይ ሆጅሰንን በአሰልጣኝነት የቀጠሩት ፓላሶች ለሲቲዎች አደጋ ሊሆኑ እንደሚችሉ ያክላል።

በዚህ ሳምንት የላውሮ ተቀናቃኝ ሆኖ የቀረበው 'ሼርሎክ ሆልምስ' እና 'ኪንግስማን' በተሰኙ ፊልሞቹ የሚታወቀው እንግሊዛዊው ተዋናይ እና ቀንደኛ የአርሰናል ደጋፊ የሆነው ማርክ ስትሮንግ ነው።

ፉክክር ቤት. . .

ዌስትሃም ከቶተንሃም

Image copyright BBC Sport

ባለፈው ሳምንት ከስዋንሲ ጋር የተፋለሙት ቶተንሃም ሆትስፐሮች አቻ መለያየት ግድ ሆኖባቸዋል። ከዚህ በኋላ የሚያደርጓቸው ተከታታይ ሶስት ጨዋታዎች ከሜዳቸው ውጭ የሚካሄዱ በመሆነቻው ጉዟቸው ቀላል እንደማይሆን ግልፅ ነው።

አጀማመራቸው ያላማረው ዌስትሃሞች በበኩላቸው ባለፉት ጥቂት ሳምንታት መነቃቃት ታይቶባቸዋል።

ላውሮ፡ 1 - 1

ስትሮንግ፡ 1 - 2

በርንሌይ ከሀደርስፊልድ

Image copyright BBC Sport

ሊጉን በጥሩ ሁኔታ ለጀመሩት ሀደርስፊልዶች ይህ ወሳኝ ወቅት ነው ይላል ላውሮ። በዌስትሃም የተሸነፉበት ጨዋታ ግስጋሴያቸውን እንዳያጨናግፈው ከበርንሌይ ጋር ያላቸውን ፍልሚያ ማሸነፍ ግድ ይላቸዋል ባይ ነው ላውሮ።

በርንሌይ ከሜዳቸው ውጭ ከሊቨርፑል፣ ቼልሲ እና ቶተንሃም ጋር ባደረጉት ጨዋታ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል። ሜዳቸው ላይ ግን ጎል ማስቆጠር ከብዷቸው ተስተውለዋል።

ሆኖም በጠንካራው አሰልጣኝ ሾን ዲቼ የሚመሩት በርንሌዮች ለሀደርስፊልድ ፈተና ይሆናሉ ይላል ላውሮ።

ላውሮ፡ 2 - 1

ስትሮንግ፡ 1 - 1

ኤቨርተን ከቦርንማውዝ

Image copyright BBC Sport

"በካራባዎ ዋንጫ' ፍልሚያ ረቡዕ ማታ ኤቨርተን ሰንደርላንድን 3-0 ሲረታ ተመልክቻለሁ። ጨዋታውም ቀሏቸው እንደነበር አስተውያለሁ። የኤቨርተን ችግር ከቦርንማውዝ ተቃራኒ ይመስለኛል። ኤቨርተኖች ጎል ማስቆጠር ሲከብዳቸው ቦርንማውዞች ግን ጎል ከማስቆጠር የሚያቆማቸው ጠፍቷል" ይላል ላውሮ።

ላውሮ፡ 2 - 2

ስትሮንግ፡ 2 - 0

ማንቸስተር ሲቲ ከክሪስታል ፓላስ

Image copyright BBC Sport

"ክሪስታል ፓላስ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር የሚያደርገው ፍልሚያ የመፃኢ ፈተናው መባቻ ነው። ፓላስ በቀጣይ ከማንቸስተር ጋር ከሜዳው ውጭ እንዲሁም በሜዳው ከቼልሲ ጋር ይፋለማል። ሲቲዎች አሁን ካላቸው አቋም በመነሳት ፓላሶችን ሊረቱ እንደሚችሉ መገመት አያዳግትም" ይለናል ላውሮ።

ላውሮ፡ 3 - 0

ስትሮንግ፡ "4 - 0 ብዬ ልገምት ነበር ግን እስቲ ፓላሶች አንድ ጎል እንኳን ይቅናቸው።" 4 - 1

ሳውዛምፕተን ከማንቸስተር ዩናይትድ

Image copyright BBC Sport

"ሳውዝምፕተኖች ካለፉት አራት ጨዋታዎች ሁለቱን ማሸነፍ ሲችሉ በሁለቱ አቻ ተለያይተዋል። በቅፅል ስያሜያቸው 'ቅዱሳኑ' በመባል የሚታወቁት ሳውዝምፕተኖች ግስጋሴያቸው መልካም ቢሆንም አቋማቸው በጥሩ ሁኔታ የሚገኘውን ዩናይትዶችን ይረታሉ ብሎ ማሰብ አዳጋች ነው። እኔ ዩናይትድ ተጭኖ በመጫወት ጨዋታውን በድል ይወጣል ብዬ አስባለሁ" ሲል ላውሮ ይተንብያል።

ላውሮ፡ 0 - 2

ስትሮንግ፡ 1 - 3

ስቶክ ከቼልሲ

Image copyright BBC Sport

ስቶክ ለቼልሲ ሌላ ፈተና እንደሚሆን ይጠበቃል። ሊጉን ከሲቲ ጋር በጋራ እየመራ የሚገኘውን ማንቸስተር ዩናይትድ እንዴት ተቋቁሞ ነጥብ እንዳስጣለ ተመልክተናል።

ቼልሲዎችም በቀላሉ ነጥብ አሳልፈው የሚሰጡ እንዳልሆነ ይታወቃል። ይህም ጨዋታውን ከፍተኛ ፍልሚያ የሚታይበት ያደርገዋል።

ላውሮ፡ 1 - 1

ስትሮንግ፡ 1 - 1

ስዋንሲ ከዋትፎርድ

Image copyright BBC Sport

ባለፈው ሳምንት በተካሄደ የሊጉ ፍልሚያ ስዋንሲ ከቶተንሃም ጋር ነጥብ ሲጋራ ዋትፎርድ ደግሞ በማንቸስተር ተረቷል። የዌልሱ ክለብ ስዋንሲ በሜዳው ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች ቢሸነፍም ከሜዳው ውጭ የተሻለ ነጥብ ማስመዝገብ ችሏል።

ዋትፎርዶች ሊጉን በበጎ ውጤት ቢጀምሩም አያያዛቸው ግን ያስተማምን አያስተማምን እርግጥ አይደለም።

ላውሮ፡ 2 - 1

ስትሮንግ፡ 2 - 0

ሌይስተር ከሊቨርፑል

Image copyright BBC Sport

ሊቨርፑሎች በላፈው ማክሰኞ ምሽት ከሌይስተር ጋር በነበራቸው የካራባዎ ዋንጫ ፍልሚያ ጨዋታው ከመጋመሱ በፊት አሸንፈው መውጣት የሚያስችላቸውን ውጤት ማስመዝገብ ቢገባቸውም በስተመጨረሻ ተሸንፈው ወጥተዋል።

ሊቨርፑሎች በማጥቃት ጥሩ ሆነው ሳለ መከላከል ላይ ግን ድክመት ይታይባቸዋል።

በሌይስተር በኩል አጥቂያቸው ጄሚ ቫርዲ ከጉዳቱ ካልተመለሰ ሊቨርፑል የተሻለ ውጤት ሊያመጣ ይችላል ሲል ላውሮ ይተነትናል።

ላውሮ፡ 1 - 2

ስትሮንግ፡ 2 - 1

ዕለተ እሁድ

ብራይተን ከኒውካስትል

Image copyright BBC Sport

ማግፒዎቹ (ኒውካስትል) ያለፉትን ሦስት ጨዋታዎች እንዳሸንፉ ባውቅም በብራይተን እንደሚፈተኑ ግን አምናለሁ። ለብራይተኖች ጨዋታው በሊጉ አናት ላይ የመቆየት እና ያለመቆየት ጉዳይ ነው።

ላውሮ፡ 2 - 1

ስትሮንግ፡ 2 - 0

ዕለተ ሰኞ

አርሴናል ከዌስትብሮም

Image copyright BBC Sport

ዌስት ብሮም የጎል እጥረት እያጠቃው ቢሆንም መጥፎ አቋም ላይ ነው ማለት አይደለም። ነገር ግን እኔ አርሰናል ይህንን ጨዋታ በሜዳው በጥሩ ብቃት ያሸንፋል ባይ ነኝ ሲል ላውሮ የሊጉን የመጨረሻ ጨዋታ ግምት ያስቀምጣል።

ላውሮ፡ 2 - 0

ስትሮንግ፡ 3 - 1