ኤንግላ ሜርክል ለአራተኛ ጊዜ አሸነፉ

የጀርመኗ መራሂተ-መንግስት ኤንግላ ሜርክል ለአራተኛ ጊዜ ምርጫ አሸንፈዋል Image copyright Getty Images

የጀርመኗ መራሂተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ለአራተኛ ጊዜ ምርጫ በማሸነፍ ቦታቸውን ቢያስጠብቁም ተቀናቃኙ እና ወግ አጥባቂው የኤ.ኤፍ.ዲ ፓርቲ ከሰባት አስርት ዓመታት በኋላ የምክር ቤት መቀመጫ ማግኘት ችሏል።

የሜርኬል ተቀናቃኝ የሆነው የሶሻሊስት ዲሞክረቲክ ቅንጅት ፓርቲ ከመሰል ፓርቲዎች ጋር በመሆን ጥምር መንግሥት ለማማቋቋም የሜርክልን ፓርቲ እንደሚሞግት አስታውቋል።

ፀረ-ሙስሊም እና ፀረ-ስደተኛው የኤ.ኤፍ.ዲ ፓርቲ ደግሞ ምርጫውን ሦስተኛ በመሆን አጠናቋል።

• ሲ.ዲ.ዩ - 33%

• ኤስ.ፒ.ዲ - 22%

• ኤ.ኤፍ.ዲ - 12.6%

• ኤፍ.ዲ.ፒ - 10.7%

• ግራ ዘመም ፓርቲ - 9.2%

• ግሪን ፓርቲ - 8.9%

በመራሄ-መንግሥትነት ለ12 ዓመታት የቆዩት አንጌላ ለደጋፊዎቻቸው ባሰሙት ንግግር 'የተሻለ ውጤት' ለማምጣት አቅደው እንደነበር አስታውቀዋል። ጨምረውም የኤ.ኤፍ.ዲ ፓርቲ ደጋፊዎችን ድምፅ ለመስማት የተቻላቸውን እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።

እንደ የቢቢሲ በርሊን ዘጋቢ ጄኒ ሂል ከሆነ ምርጫው ለሜርክል በጣም አስጊ ነው። ጀርመን በሯን ለ900 መቶ ሺህ ያህል ያልተመዘገቡ ስደተኞች ክፍት ማድረጓ ለገዢው ፓርቲ ውጤት ማሽቆልቆል እንደ ዋና ምክንያት እንደሚቆጠርም የሂል ዘገባ ያመላክታል።

ከ1950 በኋላ የጀርመን ፓርላማ ስድስት ፓርቲዎች የተካተቱበት ምክር ቤት ያቅፋል። ነገር ግን አምስቱም ፓርቲዎች ከኤ.ኤፍ.ዲ ፓርቲ ጋር አብሮ ለመስራት እንደማይፈልጉ አስታውቀዋል።

ተያያዥ ርዕሶች