የፕሪሚየር ሊጉ የሳምንቱ ምርጥ አስራ አንድ

የቀድሞው የቶተንም እና ማንቸስተር ዩናይትድ አጥቂ ጋርዝ ክሩክ የሳምንቱን ምርጥ አስራ አንድ እነሆ ብሏል።

ፕሪሚየር ሊግ የሳምንቱ ምርጥ አስራ አንድ Image copyright BBC Sport

የሮይ ሆጅሰንን ክሪስታል ፓላስ 5-0 የረመረመው ማንቸስተር ሲቲ በጎል ብዛት ከማንቸስተር ዩናይትድ አናት በመሆን ሊጉን እየመራ ይገኛል። ከሳውዝሀምፕተን ጠንካራ ፍልሚያ የገጠመው ማንቸስተር ዩናይትድ 1-0 በማሸነፍ 3 ነጥብ ይዞ መውጣት ችሏል። የአልቫሮ ሞራታ ሀት-ትሪክ እና ሊቨርፑል ከሌይስተር የነበራቸው ፍልሚያም ያለፈው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክስተቶች ነበሩ።

የቀድሞው የቶተንሀምና ማንቸስተር ዩናይትድ አጥቂ ጋርዝ ክሩክ የሳምንቱን ምርጥ አስራ አንድ ተጨዋቾች እነሆ ብሏል።

ግብ ጠባቂ፦ ሲሞን ሚኞሌ (ሊቨርፑል)

Image copyright Getty Images

ሲሞን ሚኞሌ ሊቨርፑልን ከተቀላቀለ በኋላ በሊጉ ከ15 ፍፁም ቅጣት ምቶች 7 በማዳን ከማንኛውም የፕሪሚየር ሊግ ግብ ጠባቂ የተሻለ ሪኮርድ አለው።

እኔ እንደማስበው ከሆነ የርገን ክሎፕ ሚኞሌን በመሳሰሉ ሰዎች እጅ ባይሆን ኖሮ ባለው ደካማ መከላከል ሶስት ነጥብ ይዞ መውጣት ይከብደዋል ባይ ነኝ። ሁለት ጎሎች ቀድመው የተቆጠሩበት ሚኞሌ የቫርዲን ፍፁም ቅጣት ምት ማዳን ባይችል ኖሮ ሊቨርፑል ውጤት ሊጋራ ወይም ሊሸነፍ ሁሉ እንደሚችል እሙን ነው።

ተከላካይ፦ ሲዛር አዝፕሊኬታ (ቼልሲ)

Image copyright Getty Images

በያዝነው የሊግ ዘመን ሲዛር አዝፕሊኬታ አራት ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበል ብቸኛው ተከላካለይ በመሆን ይመራል። ባለፈው ሳምንት ጨዋታም ለጎል የሚሆን ኳስ በማመቻቸት ከተከላካይነቱ በላይ ብዙ ሚና እንዳለው መሳየት ችሏል። ስቶክ ሲቲን ተከላካዮች ለሁለት በመሰንጠቅ ለአልቫሮ ሞራታ ያቀበላት ኳስ እጅግ ማራኪ ነበረች።

ተከላካይ፦ ፊል ጆንስ (ማንቸስተር ዩናይትድ)

Image copyright PA

ፊል ጆንስ ሊጉ ከተጀመረ ወዲህ በአምስት ማንቸስተር ዩናይትድ ጎል ሳይቆጠርበት በወጣባቸው ጨዋታዎች ላይ በመሰለፍ ከሌሎች የተሻለ ታሪክ ፅፏል። እርግጥ ዩናይትድ ከሳውዝምፕተን ጋር የነበረው ጨዋታ ሁሉም ተጨዋቾች ውጤት ይዘው ለመውጣት የታገሉበት ቢሆንም ፊል ጆንስ ለውጤቱ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል።

ተከላካይ፦ አድርያን ማርያፓ (ዋትፎርድ)

Image copyright Getty Images

ማርያፓ ከተሳተፈባቸው ሶስት ጨዋታዎች ዋትፎርድ ሁለቱን ማሸነፍ ችሏል። በዚህም ከአምናው የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ችሏል። ማርያፓ 1-1 ሊጠናቀቅ የሚመስል ጨዋታ ላይ ከስዋንሲ የሚመጡትን አደገኛ ጎሎች በመመከት በታሚ አብራሃም ተጨማሪ ጎል ዋትፎርድ ውጤት ይዞ እንዲወጣ ማድረግ ችሏል።

አማካይ፦ ሌሮይ ሳኔ (ማንቸስተር ሲቲ)

Image copyright Getty Images

በዚህ የውድድር ዘመን ሌሮይ ሳኔ ወደ ጎል ከሰደዳቸው ስባት ሙከራዎች አምስቱን ወደ ግብ ቀይሯቸዋል። ከክሪስታል ፓላስ ጋር በነበረው ጨዋታ አንድ ጎል ሁለት ለለጎል የሚሆኑ ኳሶች በማቀበል ድንቅ ብቃቱን አሳይቷል።

አማካይ፦ ክርስቲያን ኤሪክሰን (ቶተንሃም)

Image copyright Rex Features

ክርስቲያን ኤሪክሰን በፕሪሚየር ሊጉ በርካታ ጎሎችን በማስቆጠር ብቸኛው ድንማርካዊ በመሆን ይመራል። 33 ጎሎች በስሙ አስመዝግቧል። ፊሊፕ ኩቲንሆ ለሊቨርፑል ወሳኝ እንደሆነው ሁሉ ክርስቲያን ኤሪክሰንም ለቶተንሃም ትልቅ ቦታ አለው። አጨዋወታቸውም ይህን ያህል ልዩነት አለው ብየ አላምንም። ሁለቱም ኳስ ይዘው በመጫወት ማራኪ ጎሎችን በማስቆጠር ይታወቃሉ። ኤሪክሰን ዌስትሃም ላይ ያስቆጠራት ግብ ከባድ የሆነች ነገር ግን በቀላሉ የተቆጠረች ነች።

አማካይ፦ ፊሊፕ ኩቲንሆ (ሊቨርፑል)

Image copyright Getty Images

ኩቲንሆ 16 ኳሶችን ከ16 ከ50 ውጭ በማስቆጠር ከየትኛውም የሊጉ ተጫዋጭ የተሻለ ታሪክ አለው።

ሞሃመድ ሳላህ የመክፈቻውን ጎል ሌይስተር ላይ ለማስቆጠሩ ምክንያት የሆነችው የኩቲንሆ ኳስ ለጨዋታው ድምቀት ነበረች። ሌይስተሮች ተመልሰው ወደ ጨዋታው መግባት ቢችሉም የኩቲንሆ ድንቅ ቅጣት ምት ግን ተስፋቸውን ያደበዘዘች ነበረች።

አማካይ፦ ኬቪን ዴብሮይን (ማንቸስተር ሲቲ)

Image copyright AFP

በመስከረም 2015 ሲቲን ከተቀላቀለ ወዲህ ዴብሮይን 30 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበል ጥሩ ታሪክ አለው።

ስለሲቲ አውርቼ የዴብሮይንን ስም አለመጥቀስ እጅግ ከባድ ነው። የያያ ቱሬን የኳስ አቀባይነት ሚና መተካት ለሲቲ ከባድ የነበረ ቢሆንም ድብሮይን ግን ይህንን አደራ ከቱሬ መረከብ ችሏል።

አጥቂ፦ ኦማር ኒያሴ (ኤቨርተን)

Image copyright Getty Images

በእንግሊዝ እግር ኳስ ለመጀመሪያ ጊዜ በተለያዩ ውድድሮች ላይ በተከታታይ ጎል በማስቆጠር ኦማር ኒያሴ ታሪክ እንዲያስታውሰው ሆኗል።

ኤቨርተኖች ሉካኩን የሚታካላቸው ተጫዋች እጅጉን በሚፈልጉበት ወቅት ነው ኒያሴን ያገኙት። ኒያሴ ለሃል ሲቲ ሲጫወት አስታውሰዋለው። ነገር ግን አሁን በጣም ለየት ያለ ተጫዋች ሆኖ አግኝቸዋለው።

አጥቂ፦ አልቫሮ ሞራታ (ቼልሲ)

Image copyright Getty Images

በቼልሲ በመጀመሪያዎቹ ስድስት ጨዋታዎች የተሳተፈው ሞራታ ስድስት ሲያስቆጥር ሁለት ደግሞ አመቻችቶ አቀብሏል።

የቼልሲ ንጉስ የነበረው ዲዬጎ ኮስታ ወደ አትሌቲኮ ባቀናበት በዚህ ወቅት ቼልሲ ሌላ ጥሩ ብቃት ያለው አጥቂ ያገኘ ይመስላል። ጉለበት ተጠቅሞ ጎል ከሚያስቆጥረው ኮስታ በአጨዋወቱ ለየት የሚለው ሞራታ ከስቶክ ጋር በነበረው ጨዋታ አስደናቂ አቋም ማሳየት ችሏል።

አጥቂ፦ ሃሪ ኬን (ቶተንሃም)

Image copyright Getty Images

ኬን በለንደን ክለቦች መካከል በተደረገ ጨዋታ 21 ጎሎችን በ29 ደቂቃዎች በማስቆጠር ክበረ ወሰኑን ይዟል።

ከዴሊ አሊ የተሻገረለትን ድንቅ ኳስ ኬን በጭንቅላት ወደ ጎል ቀይሯታል። ከዌስተሃም ጋር በነበራቸው ጨዋታ ቶተንሃሞች የተሻለ አጥቅተው ሲጫወቱ ኬንም በዕለቱ ጥሩ ብቃቱን ማሳየት ችሏል።