የአፍሪካ ትልቁ የጥበብ ውጤቶች ማሳያ በኬፕ ታውን ተከፍቷል

ደቡብ አፍሪካዊው አርቲስት አቲ ፓትራ ሩጋ ስራ Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ ደቡብ አፍሪካዊው አርቲስት አቲ ፓትራ ሩጋ የጥበብ ውጤት

በአፍሪካውያን እና ከአፍሪካ ውጭ በሚኖሩ የአህጉሪቱ ልጆች ስራዎች የተሞላው በአፍሪካ ትልቁ የኮንቴምፖራሪ ጥበብ ማሳያ በደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታውን ተከፍቷል።

'ዘይትዝ' የተሰኘው ይህ ኮንቴምፖራሪ ጋለሪ በእንግሊዛዊው ዲዛይነር ቶማስ ሄዘርዊክ የታነፀ ሲሆን በተለያየ ቅርፅ ባላቸው መስኮቶች ያሸበረቀ ነው።

ጎብኚዎች ወደ ማሳያው ሲገቡ ደቡብ አፍሪካዊው አርቲስት ኒኮላስ ህሎቦ ከጎማ የሰራው ግዙፍ ድራጎን ይጠብቃቸዋል።

Image copyright AFP

ለዕይታ የቀረቡት አብዛኛዎቹ ስራዎች የሙዚየሙ ደጋፊ ከሆነው ጀርመናዊው ዮኬን ዜይትዝ የተገኙ ናቸው።

"አፍሪካውያን ወደ ጥበቡ ግንባር መምጣት አለባቸው። ይሄ የኔ የግሌ ሙዚየም አይደለም። የአፍሪካ እንጂ" ሲል ይናገራል።

Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ የ32 ዓመቱ ኬንያዊ አርቲስት ሳይረስ ካቢሩ የጥበብ ስራዎች
Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ ከመዳብ እና አልሙኒዩም ስብጥር ጋናዊው ቀራጭ ኤል አናቱሲዊ 'ቀላጭ አህጉራት' በማለት የሰራው ስራ

ተቺዎች እንደሚጠቅሱት ማሳያው የአፍሪካ ስራዎች ስብስብ ይጎድለዋል።

የካሜሩናውያኑ አርቲስቶች ሳሙኤል ፎሶ፣ ፓስካል ማርቲን ታዮ እና ደቡብ አፍሪካውያኑ ሮቢን ሮዴ እንዲሁም ትሬሲ ሮዝ ስራቸው መታየት ነበረበት ግን አልታየም ሲሉ ተቺዎች ይወቅሳሉ።

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ደቡብ አፍሪካዊው አርቲስት ኬንደል ጊርስ አፓርታይድን ለማንፀባረቅ ሰራው ስራ
Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ ሙዚየሙ በ1920ቹ በተገነባ የእህል ጎተራ ላይ የተሰራ ነው

ሙዚየሙ የአፍሪካ ፓስፓርት ላላቸው በሳምንት ለተወሰኑ ቀናት በነፃ ክፍት ሆኖ እንደሚሆን ተነግሯል።

ተያያዥ ርዕሶች