ባርሴሎና ከላስ ፓልማስ ጋር ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታም ላልታወቀ ጊዜ ተዛውሯል

Spanish Civil Guard officers remove demonstrators outside a polling station for the banned independence referendum in Barcelona, Spain, October 1, 2017 Image copyright Reuters

የስፔን ፖሊስ የካታሎንያን ሕዝበ-ውሳኔን ለማስቆም በወሰደው እርምጃ በትንሹ 337 ሰዎች ተጎዱ።

የስፔን መንግስት ሕገ-ወጥ ነው ያለውን የካታሎንያን ሕዝበ-ውሳኔ ለማስቆም ቃል ገብቶ እንደነበር የሚታወስ ነው።

የስፔን ፖሊስ ካታሎንያውያን ወደ ምርጫ ጣቢያ እንዳይሄዱ እያገደ እንዳለም ታውቋል። በየጣቢያው በመዞር የምርጫ ቁሳቁሶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉም ተዘግቧል።

ፖሊስ በካታሎንያ ትልቋ ከተማ ባርሴሎና ሕዝበ-ውሳኔውን ደግፈው ሰልፍ የወጡ ሰዎች ላይ የጎማ ጥይት ተኩሷል።

የስፔን የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስቴር እንደገለጸው በተፈጠረው ግርግር 11 ፖሊሶች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የስፔኑ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ሳንታማርያ እንደተናገሩት "ፖሊስ ሕጋዊ በሆነ መንገድ ስራውን እየሰራ ነው።"

የካታሎንያ መሪ ካርሌስ ፒዩጅመንት በበኩላቸው ህዝበ-ውሳኔውን ለማስቆም በገፍ ወደ ካታሎንያ የመጡትን የማዕከላዊ ስፔን ፖሊሶች ኮንነዋል።

"ሕጋዊ ያልሆነው የስፔን መንግስት ተግባር የካታሎንያ ሕዝብ ያሰበውን ከማሳካት አያግደውም" በማለትም ለጋዜጠኖች ተናግረዋል።

Image copyright Reuters

የስፔን የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ሁዋን ኢግናሲዮ የካታሎንያውን መሪ "ረብ የለሽ ዝግጅት ያዘጋጀ" ሲሉ ወቅሰዋል።

በተያያዘ ዜና ባርሴሎና ከላስ ፓልማስ ጋር ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታም ላልታወቀ ጊዜ ተዛውሯል።

ባርሴሎና በካታሎንያ በከተከሰተው ግርግር ምክንያት ጨዋታው ወደሌላ ጊዜ እንዲዛወርለት ላሊጋውን ጠይቋል። በዚህም መሠረት ባርሳ ከላስ ፓልማስ ጋር ሊያደርገው የነበረው ጨዋታ እንዲራዘም ሆኗል።

ተያያዥ ርዕሶች