"ካታሎንያ በሕዝበ-ውሳኔ አገር የመሆን መብቷን አሸነፈች"

ካታሎናውያን ባንዲራቸውን በማውለብለብ ብሄራዊ መዝሙር ሲዘምሩ
አጭር የምስል መግለጫ ካታሎናውያን ባንዲራቸውን በማውለብለብ ብሄራዊ መዝሙር ሲዘምሩ

እሁድ በተካሄደው የካታሎንያ ህዘበ-ውሳኔ ካታላን ከስፔን ተገንጥላ ራሷን የቻለች አገር የመሆን መብቷን አሸንፋለች።

የካታሎንያ መሪ ካርለስ ፑይግዴሞንት እንደተናገሩት የስፔን አንድ ግዛት የነበረቸው ካታሎንያ አገር የመሆን መብቷን አነጋጋሪና ግጭት ከተቀላቀለበት ከተባለው ሕዝበ-ውሳኔ በኋላ አሸንፋለች። ከአንድ ወገን በኩል ነፃነትን ለማወጅ በሩ ክፍት ነበርም በሚል አስተያየተቸውን ሰጥተዋል። ከዚህም በተጨማሪ የካታሎንያ ኃላፊዎች እንደተናገሩትም በእሁዱ ምርጫ ላይ የመረጡት 90% ነፃነትን የሚደግፉት ናቸውም ብለዋል። ምንም እንኳን የመጣው የህዘብ ቁጥር 42.3 ቢሆንም

የስፔን ህገ-መንግስታዊ ፍርድ ቤት የምርጫ ጣቢያዎችን ህገወጥ ናቸው በሚል ያወጀ ሲሆንም ፖሊስም ምርጫውን ለማገድ ኃይልን በመጠቀሙ ብዙ መቶዎች ቆስለዋል። የፖሊስ ኃይል በምርጫ ጣቢያዎቹ ላይ የመምረጫ ካርዶቹንም በኃይል ወስደዋቸዋል።በሌላ በኩል በዚህ ጭካኔ በተሞላበት የመብትና የነፃነት ጥሰት የተነሳ 40 የሚሆኑ የካታሎንያ የንግድና ሌሎች ማህበራት በግዛቱ ትልቅ የሚባለውን ሕዝባዊ አመፅ ማክሰኞ ቀን ጠርተዋል።

እሁድ ማታ ቁጥራቸው ብዙ የሚባል የነፃነት ደጋፊዎች በባርሴሎና ባንዲራቸውን እያውለበለቡ እንዲሁም የካታሎንያ ብሄራዊ መዝሙር ሲዘምሩ አምሽተዋል። ትይዩ በሆነ መልኩ የነፃነት ተቃዋሚዎችም በባርሴሎና እንዲሁም በሌሎች የስፔን ግዛቶች የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል።

ግጭቱ ምን ያህል የከበደ ነበር?

የካታሎንያ መንግስት እንደሚለው ከ800 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በግጭቱ ምክንያት አደጋ ደርሶባቸዋል። የ ስፔን የአገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር በበኩሉ ግጭቱን ተከትሎ 12 ፖሊሶች እንደቆሰሉና ሶስት ሰዎችም እንደታሰሩ ተናግረዋል። ይህንንም ተከትሎ 92 የምርጫ ጣቢያዎች ተዘግተዋል። በጊሮና ግዛት የተደራጀ የፖሊስ ኃይል ካርለስ ፑይጅዲሞንት የሚመርጡበት የምርጫ ጣቢያ ላይ በኃይል ሰብረው በመግባት ሊመርጡ የተዘጋጁትን በኃይል እንዲወጡ አስገድደዋቸዋል።

ፑይጅዲሞንትም ሌላ የምርጫ ጣቢያ ሄደው እንዲመርጥ ተገደዋል። በተለያዩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የታዩ ቪዲዮዎችም እንደሚያሳዩት በጊሮና ግዛት ህዘቡን ይከላከሉ የነበሩ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ሳይቀሩ በፖሊስ ድብደባ ደርሶባቸዋል።

የባርሴሎና ከንቲባ አዳ ኮላው ምንም መከላከያ በሌለው ህዘብ ላይ ፖሊስ ያደረሰውን ጥቃት ያወገዙ ቢሆንም የስፔን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ሶራያ ሳንዘ ደ ሳንታማሪያ በተቃራኒው ፖሊስ ስርአት ባለውና በተመጣጣኝ መልኩ የአፀፋ ምላሽ እንደሰጠ ተናግረዋል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ