ካሜሩን ተቃውሞ ባለባቸው ግዛቶች የኢንተርኔት አገልግሎትን አቋረጠች

ካሜሩን ተቃውሞ ባለባቸው ግዛቶች የኢንተርኔት አገልግሎትን አቋረጠች

ካሜሮን የመገንጠል ጥያቄ በሚያነሱ የእንግሊዝኛ ተናጋሪ ግዛቶች በተነሳ ከፍተኛ ተቃውሞ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን አቋርጣለች።

የፀጥታ ኃይሎች ለተቀውሞ ወደ አደባባይ በወጡ ሰልፈኞች ላይበከፍቱት ተኩስ ቢያንስ 8 ሰዎችን ገድለዋል።

ባሜንድ በምትባለው የካሜሩን ከተማ የሚገኘው የቢቢሲ ሪፖርተር እንዳለው በከተማዋ ውስጥ ምንም አይነት እንቅስቃሴ የለም።

ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ሁኔታ በተፈጠረው ተቃውሞ የአካባቢው ባለስልጣናት የኢንተርኔት አገልግሎትን አቋርጠው ነበር።

የቢቢሲው ሪፖርተር እንደዘገበው ኤምቲኤን የተባለው የሃገሪቷ ትልቁ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ ለደንበኞቹ የኢንተርኔት አገልግሎት አሰጣጡ ላይ ችግር እንደገጠመው በአጭር የፅሁፍ መልዕክት አሳውቆ ነበር።

ለነፃነት በተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ ካሜሮናውያን ህይወታቸውን አጡ

የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የሆኑት ጆን ፈሩ ነዲ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ቢያንስ ከ30 ሰዎች በላይ ተገድለዋል።

ሪፖርቶች አንደሚያሳዩት በሰሞኑ ተቃውሞ ከ50 በላይ ሰዎች ሲቆስሉ ከ200 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ለእስር ተዳርገዋል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ