በዓለማችን ኩባንያዎች የሚያቀርቧቸው ምርጥ የሥራ ጥቅማጥቅሞች እኚህ ይሆኑ?

የኢትዮጵያ ተራሮች Image copyright Getty Images

ኤይርቢኤንቢ የተሰኘው የቤት ኪራይ ድርጅት ለአሜሪካውያን ሠራተኞቹ በዓመት አንድ ጊዜ 2ሺህ ዶላር በመስጠት በየትኛውም የዓለም ክፍል ባለ የድርጅቱ ቤት ውስጥ እንዲቆዩ ያደርጋል።

በፈረንጆቹ 2016 ድርጅቱ ለሥራ ምቹ የሆነ ኩባንያ በመባል መሰል ድርጊቶችን በሚገመግም ድረ-ገፅ ተሸልሟል።

ማሲልዶዊ የተባለ የእንግሊዝ ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ድርጅትም በበኩሉ ለሠራቶኞቹ ማበረታቻ በማበርከት ይታወቃል። የድርጅቱ ከፍተኛ አማካሪ ሮው ዴቪስ ስትናገር ድርጅቱ ባበረከተላት ማበረታቻ ሁለት ጊዜ ወደ ኒው ዮርክ አራት ጊዜ ደግሞ ላስ ቬጋስ ሄዳ የእረፍት ጊዜዋን አሳልፋለች።

"እንዲህ ዓይነት ማበረታቻዎች ሲሰጡኝ ወደፊት የሚኖረውን ከፍ ያለ ነገር በማሰብ በርትቼ እንድሰራ እሆናለሁ" በማለት ታክላለች።

ገደብ የለሽ እረፍት

Image copyright Getty Images

ኔትፍሊክስ እና ሊንክድኢን የተሰኙት የአሜሪካ ኩባንያዎች ለሠራተኞቻቸው ገደብ የለሽ እረፍት በመስጠት ይታወቃሉ። ቨርጂን ማኔጅመንት የተሰኘው የእንግሊዝ ተቋምም በፈረንጆቹ 2014 ገደብ የለሽ እረፍትን ለሠራተኞቹ ተግባራዊ አድርጓል።

ገደብ የለሽ የተባለው የእረፍት ሁኔታ አስገራሚ ቢመስልም እውነታውን ግን ወዲህ ለየት ብሊ ልናገኘው እንችላለን።

የአእምሮ ልህቀት ባለሙያው ዶ/ር ትራቪስ በራድቤሪ እንደሚሉት "በሥራ ላይ ያለ ነፃነት ሠራተኞች የእኔነት ስሜት እንዲሰማቸው ያደርጋል። የሃላፊነት ስሜታቸው ላቅ እያለ ሲመጣ እረፍት ላይወስዱ ሁላ ይችላሉ።"

እንቁላል ማቀዝቀዣ

Image copyright Getty Images

አፕል እና ፌስቡክ የተሰኙት የቴክኖሎጂ ኩባንዎች ሴት ሠራቶኞችን ለመሳብ አንድ አጨቃጫቂ የሆነ ሃሳብ በማምጣት አንድ ወቅት ላይ ዓለምን ጉድ አስኝተው ነበር።

የዘር እንቁላላቸውን በማቀዝቀዣ ውስጥ ለሚያስቀምጡ ሴት ሠራተኞች ድርጅቶቹ 20ሺህ ዶላር ለመክፈል ወሰኑ። ይህንን ያደረጉበት ምክንያትም የዘር እንቁላላቸውን በማቀዝቀዣ ውስጥ ያስቀመጡ ሴት ሠራተኞች ኋላ ላይ ልጅ መውለድ እንዲችሉ ነው።

"ሴቶች ለቤተሰብ እና ወዳጅ ዘመድ ያላቸውን የሚሰጡትን ያህል እንክብካቤ ለአፕልም እንዲሰጡ እንፈልጋለን" ሲል አፕል ተደምጧል።

የዕሐዕ ድርጅቶቹ አቋም ለብዙ ትችት ዳርጓቸው ነበር። ተቺዎች ሴቶች በጊዜያቸው ቤተሰብ መመስረት እንዳይችሉ ያደርጋል ሲሉ ድርጊቱን ኮንነው ነበር።

እንቁላልን የማቀዝቀዙ ሃሳብ የታሰበውን ያህል ስኬታም አልነበረም። በእንግሊዝ በ2014 የተደረገ ጥናት እንደሚያሳው ከቀዘቀዙ እንቁላሎች መሃል 22̀ በመቶ ብቻ ስኬታማ መሆን ችለዋል።

ከውሻዎት ጋር ወደሥራ ቦታ

Image copyright Getty Images

ታዋቂው ኩባንያ ገጉልን ጨምሮ በርካታ መስሪያ ቤቶች የቤት እንስሳ በተለይ ደግሞ ውሻ ይዞ ወደሥራ ቦታ መምጣትን ይደግፋሉ።

አለርጂ ላለባቸው ሰዎች አመቺ ባይሆንም ውሻዎትን ወደ ሥራ ቦታ ይዞ መምጣት ሠራተኞችን ውጤታማ እንዲሆኑ እንደሚያደርግ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ጉግል የተሰኘው ኩባንያ ውሻ ወዳድ በሆኑ ሠራተኞች የተሞላ ሲሆን በድርጅቱ የስነ-ምግባር መመሪያ ላይም እንዲህ የሚል አንቀጽ ሰፍሯል፡ 'ድመት እንወዳለን። ነገር ግን ይህ የውሻ ወዳዶች ኩባንያ ነው። ስለዚህ ወደ ቢሯችን የሚመጡ ደመቶች ጭንቀት ሊገባቸው ይችላል።'

ተያያዥ ርዕሶች