እነሆ የቤተሰብ ፎቶ

father and two kids Image copyright SIAN DAVEY

ሲያን ዴቪስ የተባለው እንግሊዛዊ ተጓዥ ጋዜጠኛ ቤተሠብ ፈርጀ ብዙ የሕብረተሰብ አካል እንደሆነ የሚመስክሩ ፎቶዎችን እየዞረ ሲያነሳ ከርሟል። ምስሎቹን በካሜራው ዓይን ያነሳቸው ሰዎቹ ለማዕድ በተቀመጡበት ወቅት ነው። ተናጋሪ ያላቸውን ፎቶዎች እነሆ!

በመግቢያው ላይ ሩ እና ፒተር ከተባሉ ሁለት ልጆቹ ጋር የምትመለከቱት ቶም በቤት-መሰል መኪናው ውስጥ ምግብ ሲያበስል የተነሳው ፎቶ ነው።

Image copyright SIAN DAVEY

ትውልደ ዚምባብዌያዊው ቺሻሚሶ ኩንዲ የልጅነት ጊዜውን በእርሻ ውስጥ ነበር ያሳለፈው። ምህንድስና ያጠናው ቺሻሚሶ ከትዳሩ ሦስት ልጆች አፍርቷል።

"አባል የነበርኩበት ፓርቲን ሙጋቤ ማሳዳድ ሲጀምሩ ለደህንነቴ በመስጋት ወደ እንግሊዝ ሃገር ተሰደድኩ። ነገሮች ሲመቻቹልኝ ቤተሰቦቼን አመጣለሁ የሚል ተስፋ ነበረኝ። እንዲህ እያልኩ እነሆ 16 ዓመታት ተቆጠሩ" ይላል ቺሻሚሶ።

"የመጣሁ ሰሞን ሳውዝሃምፕተን ውስጥ መንገድ ላይ ነበር ማድረው። ብዙ ጊዜ ዝናብ ደብድቦኛል።"

የቺሻሚሶ ቤተሰቦች አሁንም ዚምባብዌ ውስጥ ይኖራሉ።

Image copyright SIAN DAVEY

"በ18 ዓመቴ ነበር ሆሊን የወልደኳት" ትላለች ሬቤካ። "አቅጄው ስላልነበር በዛ ዕድሜዬ ልጅ ማሳደግ ከብዶኝ ነበር።"

ሬቤካ እና ሆሊ ከሬቤካ እናትና አባት አቅራቢያ ይኖራሉ። "ፍቅራችን ለየት ያለ ነው" ትላለች ሬቤካ።

Image copyright SIAN DAVEY

ጂም ከጆይስ ጋር ለ63 ዓመታት ዘልቋል። ነገር ግን ከሦስት ዓመታት በፊት ጆይስ አለፈች፤ ጂምም በብችኝነት ኑሮውን መግፋት ያዘ።

ጂም የመጃጀት በሽታ ተጠቂ ሲሆን፤ ሁሌም በሳምንቱ መጨረሻ ልጁ ሪቻርድ ሊጎበኘው ራቅ ወዳለው ስፍራ ይመጣል። የቤተሰቡ አባላትም ከያሉበት ይሰባሰባሉ።

ሪቻርድ ስለአባቱ ሲናገር "ለሁሉም ሰው ምላሹ ፈገግታ ነው። የእርሱ ፈገግታ ለእኛ ሁሉ ነገራችን ነው።"

Image copyright SIAN DAVEY

ከልጅነታቸው ጀምሮ የሚተዋወቁት ኬት እና አያን ሞሪሰን አሁን ላይ ሁለት ልጆች አፍርተው ይኖራሉ።

ኬት ስትናገር "ልጆቻችን ኒያል እና አሜሊያ ለቀጣይ ሕይዋታቸው የሚሆን ስንቅ እንዲኖራቸው እኔና ባሌ ሁሌም እንተጋለን" ትላለች።

Image copyright Denis and her two kids dining together

"እኛ ቤት ነገሮችን ለማድረግ ጊዜ ወይም ወቅት አንጠብቅም፤ ሲሆን ይሆናል ነው" ትላለች ዴኒስ።

አራት ልጆቿን ለብቻዋ የምታሳድገው ዴኒስ በርሚንግሃም ውስጥ የልዩ ፍላጎት አስተማሪ በመሆን ትሠራለች።

ልጆቿን ግልጽ፣ ታማኝ እና እርስ በርስ እንዲደጋገፉ አድርጋ አሳድጋለች። ልጆቿ የየራሳቸው ተሰጥኦ ያላቸው ሲሆኑ ትንሹ ልጇ ሬማር በሌይስተር ሲቲ እግር ኳስ ቡድን ውስጥ ችሎታውን እያሳደገ ይገኛል።

Image copyright SIAN DAVEY

ቶም እና አና በጓደኞቻቸው አማካይነት ነው የተዋወቁት። "እርስ በርስ ጥሩ ስሜት ነበረን። በመጨረሻ አንድ እንደምንሆን አናውቅ ነበር" ይላል ቶም።

ከስምንት ዓመት በፊት የተወለደው ቢሊ የአካል እና የአእምሮ ዕድገት በሽታ ተጠቂ ነው። በጨቅላ ዕድሜው ብዙ መከራዎችን አልፏል።

አና "ፈገግታው ከብዙ ነገሮች ይታደገዋል" ስትል ትናገራለች።

Image copyright SIAN DAVEY

ክርስቲና ሴባስትያንን የተገላገለችው በ26 ዓመቷ ነው። አባቱ በውትድርና ዘርፍ ስላለ ብዙ ጊዜ ቤት አይገኝም።

ቀን ቀን በካሸርነት ማታ ማታ ደግሞ በአንድ ሆቴል ውስጥ በሼፍነት ታገለግላለች። እሷ ሥራ ላይ በምትሆን ጊዜ ሴባስትያንን እናቷ ጋር ታስቀምጠዋለች።

"ቁርስ ላይ ብቻ ነው ብዙ ጊዜ የምንገናኘው። አንድ ላይ ስንሆን እንዴት ደስ እንደሚል" ባይ ናት ክርስቲና።

ተያያዥ ርዕሶች