የጦር መሣሪያ እና አሜሪካ በቁጥሮች

US in comparison to other countries

ስቴፈን ፓዶክ የተባለ አሜሪካዊ 59 ሰዎችን በጥይት በመግደል 500 የሚሆኑትን ባቆሰለ ማግስት አሜሪካ ውስጥ መሰል ድርጊቶች ምን ያህል የሰው ነፍስ እያጠፉ እንሆነ የሚያሳይ መረጃ መውጣቱን ቀጥሏል።

በፈረንጆቹ 2015 ብቻ በአሜሪካ 372 ጅምላ የጦር መሣሪያ ጥቃቶች የደረሱ ሲሆን፤ 475 ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ 1800 የሚደርሱት ቆስለዋል።

ጅምላ የጦር መሣሪያ ጥቃት ማለት ጥቃት ፈጻሚውን ጨምሮ ቢያንስ የአራት እና ከዚያ በላይ ሰዎችን ሕይወትን የሚያጠፋ ጥቃት ነው ሲሉ ባለሙያዎች ይተነትኑታል።

በአንድ ወቅት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የጦር መሣሪያን አስመልክቶ እንባ እየተናነቃቸው ሲናገሩ የሚያሳይ ምስል ወጥቶ መነጋገሪያ እንደነበረ የሚታወስ ነው። ፕሬዝደንቱ የጦር መሣሪያን በተመለከተ ለማሻሻል ያሰቡት ሕግ ሳይሳካላቸው እንደቀረ ይታወቃል።

እርግጥ የሆነው ቁጥር ይፋ ባይሆንም አሜሪካ ውስጥ 300 ሚሊዮን የጦር መሣሪያዎች ቢያንስ 75 ከመቶ በሚሆኑ አሜሪካውያን እጅ ስር እንዳሉ ይነገራል።

ተያያዥ ርዕሶች