የዚህ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ትንበያ

epl 2017/18 Image copyright STF

የቢቢሲ የእግርኳስ ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን የዚህን ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ውጤት ትንበያ አስቀምጧል። ከላውሮ የተሻለ ግምት ይኖሮት ይሆን?

የሊቨርፑሉ አስልጣኝ የርገን ክሎፕ ወደ አንፊልድ ከመጡ ወዲህ ከቶተንሃም ጋር ከደረጓቸው አምስት ጨዋታዎች አንድም ሸንፈት አላስተናገዱም። በዚህ ሳምንትስ ምን ይፍጠራል? ክሎፕ ያለመሸነፍ ጉዞአቸውን ያስጠብቃሉ ወይስ. . . ?

የዚህ ሳምንት የላውሮ ተቀናቃኝ ሆኖ የቀረበው የእንግሊዝ ክሪኬት ቡድን አምበል ጆ ሩት ነው።

ሌሎች የሳምንቱ መጨረሻ ጨዋታዎችን ጨምሮ የላውሮ ቅድመ ትንበ ያእነሆ።

አርብ

ዌስትሃም ከብራይተን

Image copyright BBC Sport

ባለፈው ሳምንት የአንዲ ካሮል በቀይ ካርድ መውጣት ዋጋ ቢያስከፍላቸውም ዌስትሃሞች ወደ ተሻለ ቅርፅ እየመጡ እንደሆነ ይሰማኛል።

ብራይተኖችም ባለቀ ሰዓት በተቆጠረባቸው ፍፁም ቅጣት ምት ከኤቨርተን አቻ ቢለያዩም የተሻለ ብቃት እያሳዩ ይገኛሉ።

ብራይተኖች ዌስትሃሞችን እንደሚፈትኑ ባምንም የቢሊች ቡድን ሙሉ ሶስት ነጥብ ይዞ እንደሚወጣ እገምታለሁ።

የላውሮ ግምት፡ 2 - 0

የሩት ግምት፡ 1 - 0

ቅዳሜ

ቼልሲ ከዋትፎርድ

Image copyright BBC Sport

ቼልሲ ባለፈው ሳምንት ከፓላስ ጋር በነበረው ጨዋታ ያሳየው እንቅስቃሴ በጣም አስደንግጦኛል። ቢሆንም እንዲህ በቀላሉ የቼልሲ ብቃት ይወርዳል የሚል እምነት የለኝም።

አሁን ባላቸው የተጫዋቾች ስብስብ ቼልሲዎች ዋንጫ ማንሳታቸው ነገር ተስፋው የቀጨጨ እንደሆነ እንደሚረዱት አምናለሁ።

ዋትፎርድ አሁን ላይ በጣም ጥሩ አቋም እያሳየ ይገኛል። ከሜዳው ውጭ ካደረገው አራት ጨዋታ ሶስቱን ሰያሸንፍ በአንዱ አቻ መለያየት ችሏል።

የላውሮ ግምት፡ 2 - 0

የሩት ግምት፡ 3 - 0

ሃደርስፊልድ ከማንቸስተር ዩይትድ

Image copyright BBC Sport

ከዚህም በፊትም ብየዋለሁ አሁንም እለዋለሁ፤ ሃደርስፊልድ ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን በርካታ ጎል ማስቆጠርም ይጠበቅባቸዋል።

ዩናይትድ ወደሃደርስፊልድ ሜዳ ተጉዞ አሸንፎ እንደሚመጣ አምናለሁ። ግን ምን ያህል ሃደርስፊልዶች ለዩናይትድ ፈታኝ ሊሆኑ እንደሚችሉ አላውቅም።

የላውሮ ግምት፡ 0 - 2

የሩት ግምት፡ 1 - 2

ማንቸስተር ሲቲ ከበርንሌይ

Image copyright BBC Sport

በርንሌይ በዚህ የውድድር ዘመን ያሳዩት ብቃት እጅግ አስደናቂ ነው። ቀንደኛ ደጋፊያቸው የሆነ ሰው እንኳ ቡድኑ ካለፉት ስምንት ጨዋታዎች አንድ ብቻ ተሸንፎ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣል ብሎ አያስብም።

ነገር ግን የሲቲ አጨዋወት ዘይቤ ከሁሉም አቅጣጫ ወደጎል መሄድን የሚከተል ስለሆነ ለበርንሌይ ፈተና እንደሚሆን እሙን ነው።

የላውሮ ግምት፡ 3 - 0

የሩት ግምት፡ 4 - 1

ኒውካስትል ከክሪስታል ፓላስ

Image copyright BBC Sport

ፓላስ በስተመጨረሻም ቼልሲን በማሸነፍ የመሸነፍ ጉዞውን ገቷል። ሮይ ሆድሰን በስልጠና ሜዳ ላይ ምን ዓይነት ለውጥ እያመጡ እንደሆነም ማሳያ ነው።

አሁን ወደ ሴይንት ጄምስ ፓርክ ስታድዬም ሄደው የተሻለ ውጤት ይዘው እንደሚመጡም ተስፋ አለ።

የላውሮ ግምት፡ 2 - 1

የሩት ግምት፡ 2 - 0

ስቶክ ከርንማውዝ

Image copyright BBC Sport

ያላቸውን የተጫዋቾች ስብስበ በመመልከት ስቶክም ሆነ በርንማውዝ በዚህ የውድድር ዘመን ታግለው ውጤት እንዲያመጡ አልጠብቅም። ሁለቱንም ወራጅ ቀጣና ውስጥ ነው የሚገኙትና።

ከሁለቱ ቡድኖች ግን የበርንማውዝ ነገር ያሳስበኛል።

የላውሮ ግምት፡ 1 - 1

የሩት ግምት፡ 1 - 1

ስዋንሲ ከሌይስተር

Image copyright BBC Sport

የሌይስተር ባለቤቶች ቡድኑ ካቻምና ዋንጫ ስላነሳ ብቻ የሰንጠረዡ አናት ላይ እንዲቀመጥ እየጠበቁ ይመስለኛል። ለስዋንሲ ይህ ጥሩ አጋጣሚ ነው።

በስዋንሲ ብቃትም ብዙ መተማመን አላደረብኝም።

የላውሮ ግምት፡ 2 - 1

የሩት ግምት፡ 2 - 2

ሳውሃምፕተን ከዌስትብሮም

የቶኒ ፑሊስ ቡድን ባለፈው ሳምንት ከሌይስተር ጋር በነበረው ጨዋታ አቻ ተለያይቷል። በሊጉ ጨዋታ ካሸነፉ እነሆ ስድስት ጨዋታዎች አለፏቸው።

ሳውዝሃምፕተን ባለፈው ከኒውካስትል ጋር በነበረው ጨዋታ በሁለት ጎል ከመመራት ተነስቶ አቻ መውጣት ችሏል።

እኔ ቅዱሳኑ ባጊዎቹን ያሸንፋሉ ባይ ነኝ።

የላውሮ ግምት፡ 2 - 1

የሩት ግምት፡ 2 - 1

እሁድ

ኤቨርተን ከአርሴናል

Image copyright BBC Sport

ኤቨርተንም ሆነ አርሴናል ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት ተስኗቸዋል። የኤቨርተን ግን ባስ ያለ ይመስላል።

አርሴናል ጉልበት ያላቸው እና አጥቅተው የሚጫወቱ ቡድኖች እጅግ ይፈትኑታል። ኤቨርተን ከታላላቅ ክለቦች ጋር ሲጫወት እንደ አንበሳ በማጓራት በሚታወቁት ደጋፊዎቹ በመታገዝ ከጨዋታው አንድ ነገር እንደሚያተርፍ አስባለሁ።

የላውሮ ግምት፡ 1 - 1

የሩት ግምት፡ 2 - 1

ቶተንሃም ከሊቨርፑል

Image copyright BBC Sport

ሳምንቱ ለቶተንሃም ቀና ይመስላል። በፕሪሚየር ሊጉ በርንማውዝን ሲረቱ በቻምፒየንስ ሊግ ደግሞ በቤርናቢዩ ከማድሪድ አቻ ተለያይተዋል።

ሊቨርፑልም በቻምየንስ ሊጉ ማሪቦርን በሰፊ ጎል ልዩነት አሸንፏል። ሊቨርፑሎች በዚህ ጨዋታ ጎል እንደሚያስቆጥሩ አስባለሁ ግን ቶተንሃም ጎል እንዳያስቆጥር ያግዱታል ብዬ አላምንም።

የላውሮ ግምት፡ 1 - 1

የሩት ግምት፡ 3 - 2