የቻይናውን መሪ የሚተካ አልተገኘም

Image copyright AFP

ቻይና በሃገሪቱ ከፍተኛ የአመራር ደረጃ ላይ የሚገኙ አባላቶችን ይፋ ስታደርግ ባልተለመደ ሁኔታ ዢ ጂንፒንግን ማን እንደሚተካ አልተነገረም።

ዢ ስማቸው በሃገሪቷ ህገ-መንሥስት ላይ ከሰፈረ ከአንድ ቀን በኋላ ቻይናን ለቀጣይ አምስት ዓመታት ምናልባትም ከዚያ በላይ እንደሚመሩ ይፋ ተደርጓል።

ሰባት አባላትን የሚይዘው እና በቻይና ከፍተኛ ስልጣን ያለው የፖሊት ቢሮ ቋሚ ኮሚቴ፤ አምስት አዳዲስ የኮሚቴ አባላት ሹመትን ይፋ አድርጓል።

ሰባቱም የፖሊት ቢሮ ቋሚ ኮሚቴ አባላት እድሜያቸው ስድሳ እና ከዚያ በላይ ነው።

ነባር አባላት ሲቀየሩ፤ ዢ ጂንፒንግ እና ጠቅላይ ሚንስትሩ ሊ ኬዬጊያን ብቻ ናቸው የኮሚቴው አባል ሆነው መቆየት የቻሉት።

አጭር የምስል መግለጫ የፖሊትቢሮ ቋሚ ኮሚቴ አባላት

ዢ የቋሚ ኮሚቴውን አባላት ቁጥር ከሰባት ወደ አምስት በመቀነስ ተፅእኖ ፈጣሪነታቸውን ያገዝፉታል የሚል ጥርጣሬ ነበር።

ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ የቻይና መሪዎች አዳዲስ ባለሥልጣናትን ወደ ቋሚ ኮሚቴው በማምጣት ግልፅ የሆነ የስልጣን ርክክብ ሲያደርጉ ተስተውለዋል።

የቋሚ ኮሚቴው አባላት ይፋ የተደረጉት በኮንግረሱ ስብሰባ ማብቂያ ላይ ነበር።

በሥነ-ስርዓቱ ላይ ቢቢሲን ጨምሮ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን እንዳይሳተፉ ተከልክለዋል። ይህም የፕሬስ ነፃነትን የሚጋፋ ነው ተብሎ ትችት ቀርቦበታል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ