የብራዚል ሴቶች እግር ኳስ በቀዳሚነት የሚመርጡት ስፖርት አይደለም
የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።

የብራዚል ሴቶች እግር ኳስን እንዴት ያዩታል?

ብራዚል ውስጥ ከ30 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች እግር ኳስ እንዳይጫወቱ ዕገዳ ተጥሎባቸው ቆይቷል። ታዳጊ ሴቶች አሁንም በእግር ኳስ ሜዳዎች ላይ ለመጫወት አዳጋች ይሆንባቸዋል። የ12 ዓመቷ አና ሉይዛ እና የ13 ዓመቷ ሉይዛ እግር ኳስ መጫወት ቢወዱም መቀለጃ ይሆናሉ ወይም አብረዋቸው በሚጫወቱ ወንዶች ከሜዳ እንዲወጡ ይደረጋሉ። ታዳጊዎቹ ቢቢሲ 100 ሴቶች ባዘጋጀው ሙከራ ላይ በመሳተፍ በብራዚል ያለውን ግንዛቤ ለመቀየር እየሰሩ ነው። ሁለቱ ታዳጊዎች ውጤታማ በሆነው የብራዚል እግር ኳስ ውስጥ በይበልጥ እንዲዋሃዱ ለማድረግ ለአንድ ሳምንት ከተለያዩ ባለሙያዎች ጋር ጊዜያቸውን አሳልፈዋል።