ለወራት ውቅያኖስ ላይ የጠፉ ሁለት ሴቶች ተገኙ

ፓሲፊክ ውቅያኖስ ላይ Image copyright Alamy

ሁለት ሴቶች ከውሾችቻቸው ጋር በፓሲፊክ ውቅያኖስ ላይ አቅጣጫ ስተው አምስት ወራት ለሚጠጋ ጊዜ ከቆዩ በኋላ የአሜሪካ ባሕር ኃይል እንደታደጋቸው ባለሥልጣናት ተናገሩ።

ጄኔፈር አፕል እና ታሻ ፉያባ በትንሽ ጀልባ ከሃዋይ ተነስተው ውደ ታሂቲ ሲጓዙ ነበር በመጥፎ የአየር ምክንያት የጀልባዋ ሞተር በመበላሸቱ ወደፈለጉት አቅጣጫ መሄድ ሳይችሉ ቀርተው ባሕር ላይ ለወራት የዋለሉት።

ጀልባዋም በሰፊው ውቅያኖስ ላይ ከጃፓን ደቡብ ምሥራቅ በኩል 1500 ኪሎሜትሮችን እርቃ ተጉዛ ነበር።

ከጠፉበት ሊገኙ የቻሉት ዓሣ አስጋሪዎች ካዩአቸው በኋላ ለአሜሪካ ባለሥልታናት በማሳቃቸው ነው።

ሁለቱ ሴቶች በግንቦት ወር ላይ የባሕር ላይ ጉዟቸውን የጀመሩት ወዳሰቡበት ቦታ ለመድረስ ያቀዱት በንፋስ ግፊትና በጀልባቸው ሞተር ኃይል በመጠቀም ነበር ሲል በአካባቢው ያለ የአሜሪካ ባሕር ኃይል ገልጿል።

''በባሕር ጉዞ ላይ ለሁለት ወራት ከቆዩ በኋላ ካሰቡበት አለመድረሳቸውን ሲረዱ የድረሱልን ጥሪ ማሰማት ጀምረው ነበር ይላል የባሕር ኃይሉ የወጣው መግለጫ።

የአሜሪካ ባሕር ኃይል እነዳለው ሁለቱ የባሕር ላይ ተጓዦች የድረሱልን ጥሪያቸውን በየዕለቱ እያደርጉ ቢቀጥሉም ለሌሎች መርከቦች ወይም በምድር ላይ ላለ ጣቢያ ቅርብ ስላልነበሩ የጥሪ መልዕክታቸው ሳይሰማ ቀርቷል።

ነገር ግን ጥቅምት 14 ላይ ጀልባዋ በውቅያኖሱ ላይ ስትዋልል የታይዋን ዓሣ አጥማጅ መርከበኞች ተመልክተው በጓም ደሴት ላይ ለሚገኙ የአሜሪካ ባለሥልታናት ካሳወቁ በኋላ ነው የተገኙት።

''የባሕር ኃይል አባላቱን ስናይ በጣም ነበር የተደሰትነው፤ ህይወታችንን ነው ያተረፉት'' ስትል አፕል ተናግራላች።

ሁለቱ ሴቶችና ሁለት ውሾቻቸው ለወራት በውቅያኖሱ ላይ በቆዩበት ጊዜ ጀልባዋ ላይ የነበረ የደረቅ ምግብ ክምችትና እየተመገቡና የውሃ ማጣሪያን ይጠቀሙ ነበር።

ተያያዥ ርዕሶች