ማንችስተር ዩናይትድ ከቶተንሃም. . . የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታን ማን ያሸንፍ ይሆን?

ላውሮ Image copyright BBC Sport

ማንቸስትር ዩናይትድ በያዝነው የውድድር ዘመን የመጀመሪያቸው የሆነውን ሽንፈት በሃደርስፊልድ ሜዳ አስተናግዷል። ቅዳሜ ዕለት ከቶተንሃም የሚጫወተው ዩናይትድ መሰል ሽንፈት ይገጥመው ይሆን?

'አልመሰለኝም' ይላል የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ውጤት የሚተነብየው የቢቢሲ ስፖርቱ ማርክ ላውረንሰን። ጨዋታው 1 አቻ ይጠናቀቃል ባይም ነው።

ቅዳሜ

ማንስትር ዩናይትድ ከቶተንሃም

Image copyright BBC Sport

ባለፈው ቅዳሜ ዩናይትድ በሃደርስፊልድ ሲሸነፍ ተመልክቻለሁ። በጣም ያስገረመኝ ነገር ቢኖር ዮናይትዶች በመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ያሳዩት ደካማ እንቅስቃሴ ነው። ከግብ ጠባቂው ዴ ሂያ ሌላ የዩናየትድ ተጫዋቾች ሜዳ ላይ አይታዩም።

ከዩናይትድ ጋር በተመሳሳይ ነጥብ ላይ የሚገኙት ቶተንሃሞች ከዚህ ጨዋታ አንድ ነጥብ ካገኙ ጥሩ ይመስለኛል።

ላውሮ፡ 1 - 1

አርሴናል ከስዋንሲ

Image copyright BBC Sport

እርግጥ መድፈኞቹ አሁን ላይ አሳማኝ የሆነ አቋም እያሳዩ ነው ለማለት ይከብዳል። ነገር ግን ጎሎችን በማስቆጠር ላይ ናቸው፤ ኤቨርተን ላይ አምስት ጎል ማዝነብ ችለዋል።

ስዋንሲ በዚህ ዓመት ከሜዳቸው ውጭ ካደረጓቸው ጨዋታዎች በአንዱ ብቻ ነው የተሸነፉት። ይህን ጉዟቸውን ኤሜሬትስ ላይም ማስቀጠል እንደሚፈልጉ ባስብም ቀላል እንደማይሆን ግን እገምታለሁ።

ስዋንሲ አሁን ላይ ከሊጉ ወገብ በታች ነው የሚገኙት፤ ለተወሰነ ጊዜ ያክልም እዛው እንደሚቆዩ አስባለሁ።

ላውሮ፡ 3 - 0

ክሪስታል ፓላስ ከዌስትሃም

Image copyright BBC Sport

ዕለተ ረቡዕ ዌስትሃሞች በካራባዎ ዋንጫ ቶተንሃምን ያሸነፉበት መንገድ በጣም አስገራሚና ለአሰልጣኝ ቢሊች እፎይታን የሰጠ ነበር።

ክሪስታል ፓላሶች ከኒውካስትል ጋር በነበራቸው ጨዋታ ማሸነፍ ቢገባቸውም ኳስ ወደጎል መቀየር ባለመቻላቸው ሊሸነፉ ችለዋል። ንስሮቹ ተመሳሳይ አቋም አሳይተው ጎል ማስቆጠር ከቻሉ ቢያንስ አንድ ነጥብ የሚያጡ አይመስለኝም።

ላውሮ፡ 1 - 1

ሊቨርፑል ከሃደርስፊልድ

Image copyright BBC Sport

ሊቨርፑል ያሸንፋል ባልኩባቸው ጨዋታዎች ውጤት እየቀናው አይደለም። ነገር ግን ከሃደርስፊልድ ጋር በሚኖራቸው ጨዋታ እንደሚያሸንፉ እገምታለሁ።

ሃደርስፊል ከዩናይትድ ጋር በነበራቸው ፍልሚያ ድንቅ ነበሩ። ቢሆንም በዚህ ጨዋታ ቀያዮቹ ተሽለው እንደሚገኙ እጠብቃለሁ።

ላውሮ፡ 2 - 0

ዋትፎርድ ከስቶክ

Image copyright BBC Sport

አሁን አሁን የስቶክ ነገር እያሳሰበኝ ይገኛል፤ ባለፈው በሜዳቸው በቦርንማውዝ መሸነፋቸውን ተከትሎ። ማርክ ሂዩዝ አሁን ላይ ጨዋታዎችን ማሸነፍና ቡድናቸውን መታደግ ይጠብቅባቸዋል።

ቢሆንም ዋትፎርድ ቀላል ቡድን ነው ማለት አይደለም። ስቶክ በመከላከል ክፍላቸው የሚሠራውን ስህተት መቀነስ ከቻሉ የተሻለ ነገር ሊያሳዩ ይችላሉ ብዬ አስባለሁ።

ላውሮ፡ 1 - 1

ዌስትብሮም ከማንቸስተር ሲቲ

Image copyright BBC Sport

ዌስትብሮም ሌላኛው ያልተስተካከለ አቋም ላይ ያለ ቡድን ነው። በሊጉ ከነሃሴ ጀምሮ አንድም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻሉም። በተፃራሪ ማንቸስተር ሲቲ እስካሁን ምንም ዓይነት ሽንፈት አላስተናገዱም።

በዚህ ጨዋታ ሲቲ ይሸነፋል የሚል ግምት ጭራሹኑ የለኝም ቢሆንም የቶኒ ፑሊስ ቡድን ሲቲዎች በርካታ ጎሎች ሲያስቆጥሩ ቆሞ ያያል የሚልም እምነት የለኝም።

ላውሮ፡ 0 - 2

ቦርንማውዝ ከቼልሲ

Image copyright BBC Sport

ቦርንማውዝ ባለፈው ጨዋታ ስቶክን ቢያሽንፉም አሁንም በወራጅ ቀጣና ውስጥ ነው የሚገኙት። ለተወሰኑ ሳምንታት እዚያ እንደሚቆዩም አስባለሁ።

ሰማያዊዎቹ በአንፃሩ ባለፈው ሳምንት ከዋትፎርድ ጋር በነበራቸው ጨዋታ ያሳዩት ፍልሚያ የኮንቴ ቡድን ምንም ቢሆን ለሸንፈት ዝግጁ እንዳልሆነ የሚያሳይ ነው።

የዋንጫ ባለቤትነታቸውን የማስጠበቁ ነገር ባያሳምነኝም አቋማቸውን አስተካክለው ጠንካራ ተፎካካሪ እንደሚሆኑ ግን አስባለሁ።

ላውሮ፡ 0 - 2

ዕለተ እሁድ

ብራይተን ከሳውዝሃምፕተን

Image copyright BBC Sport

ሳውዝሃምፕተን በአጥቂ ክፍላቸው በኩል የተሻለ ስብስብ አላቸው። በሊጉ ወገብ ላይም ተደላድለው ተቀምጠው ይገኛሉ።

ብራይተኖች ዌስትሃም ላይ ባለፈው አርብ የተቀዳጁት ድል እጅግ አሪፍ ነበር። በተለይ በሜዳቸው እያገኙ ያሉት ነጥብ ብራይተኖችን እየጠቀማቸው ይገኛል።

ሁለቱም ቡድኖች ከዚህ ጨዋታ አንድ አንድ ነጥብ ቢያገኙ ቅር የሚሰኙ አይመስለኝም። የኔም ግምት 1 አቻ እንደሚለያዩ ነው።

ላውሮ፡ 1 - 1

ሌይስተር ከኤቨርተን

Image copyright BBC Sport

ሌይስተሮች በምክትል አሠልጣኝ ክላውድ ፑዌል ለመዝለቅ ለምን እንደወሰኑ ይገባኛል። ምክንያቱ ደግሞ ሰውየው ልምድ ያላቸው መሆናቸው ነው፤ በተለይ ደግሞ ከሳውዝሃምፕተን ጋር በነበራቸው ቆይታ።

ኤቨርተን ግን ሮናልድ ኩማንን በማን ሊተካ እንደሚችል አላውቅም። ግን በጊዜያዊ አሠልጣኛቸው ዳቪድ አንስዎርዝ ሃላፊነታቸውን እንዴት ሊወጡ እንደሚችሉ እንመለከታለን።

ለኤቨርተን ዓመቱ አስቸጋሪ እንደሚሆንባቸው እገምታለሁ።

ላውሮ፡ 2 - 0

ሰኞ

በርንሌይ ከኒውካስል

Image copyright BBC Sport

እንደእውነቱ ከሆነ በኒውካስል ብቃት እጅግ ተደንቂያለሁ። እንዲህ የተሻለ አቋም ያሳያሉ እምነት አልነበረኝም።

ልክ እንደዛው ሁሉ በርንሌይ ለሽንፈት የማይበገር ጠንካራ ቡድን ሆኖ መጥቷል።

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ጥሩ ፍልሚያ የሚታይበት እንደሆነ አስባለሁ።

ላውሮ፡ 1 - 2