እውነተኛ ውበትን ፍለጋ

Image copyright Mihaela Noroc
አጭር የምስል መግለጫ ከግራ ወደ ቀኝ ፎቶግራፎቹ የተነሱት ፓሪስ ፈረንሳይ፣ ደቡብ ኦሞ ኢትዮጵያ እና ግሪክ ነው።

ፎቶግራፈር ሚሃኤላ ኖሮክ ''አሁን ወደ ጉግል ሄደው Beautiful women (ውብ ሴቶች) ብለው ጉግል ያድርጉ'' ትላለች። እጅግ በርካታ ምስሎችን ይመለከታሉ። ያገኟቸውን ምስሎች በትኩረት ይመልከቱ።

ሚሃኤል የምትመለከቷቸው ምስሎቹ ''የሴት ልጅን ውበት መወከል የማይችሉ እና እጅግ በጣም ወሲብ ቀስቃሽ የሚባሉ አይነት ምስሎች ናቸው'' ትላለች።

እውነት ነው። በምስሉ ላይ የሚታዩት አብዛኛዎቹ ሴቶች ባለተረከዝ ጫማ የተጫሙ እና ስስ ልብሶችን የለበሱ ናቸው። ከዚህ በላይ ደግሞ ''ውብ ሴቶች'' የተባሉት የሰውነት ቅርፃቸው የተስተካከለ፣ ነጭ፣ ወጣት እና ቆዳቸው እንከን የሌለሽ ሆነው ይታያል።

ሚሃኤላ ''የሴት ልጅ ውበት ማለት ይህ ነው?'' ስትል ትጠይቃለች።

አለመታደል ሆኖ የሴት ልጅን ውበት በዚያ መልክ የሚገልጹ አሉ። ''አለመታደል ሆኖ ውበ ሴቶችን ከቁስ ጋር የሚያዛምዱ እና በወሲብ እይታ ውስጥ የሚከቷቸው በርካቶች ናቸው'' ትላለች።

Image copyright Mihaela Noroc
አጭር የምስል መግለጫ ከግራ ወደ ቀኝ ፎቶግራፎቹ የተነሱት በጀርመን፣ ጣሊያን እና ፈረንሳይ ነው።

''ሴቶች ግን እንደዛ አይደሉም። የራሳችን የሆነ ታሪክ አለን፣ የራሳችን ተጋድሎ እና ኃይል አለን። በርካቶች ግን በሌላ መልክ ቀርበዋል።''

ሚሃኤላ በቅርቡ እሷ የነሳቻችውን የአምስት መቶ ሴቶች ፎቶግራፍ የያዘ እና ''አትላስ ኦፍ ቢዩቲ''' የተሰኘ መጽሃፍ አስመርቃለች።

Image copyright Mihaela Noroc, India
አጭር የምስል መግለጫ ፑሽካር ህንድ። ሚሃኤላ በመላው ዓለም ሴቶች የጸጥታ ኃይል አስከባሪ አባል ሆነው ሳይ ደስታ ይሰማኛል ትላለች።

ሮማኒያዊቷ ፎቶግራፍ አንሺ ለ'ውበት' ምንም አይነት ትርጉም አትሰጥም። በተለያየ የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙ፣ በተለያየ የሥራ መስክ ላይ የተሰማሩ እና የተለያየ የኋላ ታሪክ ያላቸውን ሴቶች ውበትን ሊለኩ የሚችሉበት ተመሳሳይ መመዘኛ ሊኖር አይችልም ትላለች።

''ሰዎች ፎቶግራፎቼን ማየት ያስደስታቸዋል። ለዚህም ምክንያቱ ፎቶ የማነሳቸው ሴቶች በአከባቢያችን የሚገኙትን ነው ብዬ አምናለው'' ስትል ታስረዳለች።

የማነሳቸው ፎቶግራፎች በጣም ቀላል እና ተፍጥሯዊ ሊባሉ የሚችሉ ናቸው። ይህም ውብ ሴቶችን በዚህ መልክ ስለማናያቸው ፎቶግራፎቼን የተለዩ ያደርጋቸዋል ስትል ስለ ሥራዎቿ ትናገራለች።

ከ500 በላይ ፎቶግራፎችን የያዘው መጽሃፏ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ13 ሃገራት ወስጥ ተዘዋውራ ያነሳቻቸው ፎቶዎች አካቷል።

Image copyright Mihaela Noroc
አጭር የምስል መግለጫ ካፕቴን ቤሪኒስ ቶሬስ የሜክሲኮ ፌደራል ፖሊስ ሄሊኮፕተር አብራሪ ነች።

በአንዳንድ ሃገራት ሴቶችን ፎቶግራፍ ማንሳት በጣም ከባድ ነው። ''ወግ አጥባቂ በሆኑ ማሕብረሰቦች ውስጥ ሴቶች እንደፍላጎታቸው መሆን አይችሉም። ከዚህ በላይ ደገሞ ሁሉንም እንቅስቃሴያቸውን በቅርብ የሚከታተል አይጠፋም። በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ የምትኖር ሴት ፎቶግራፍ ለመነሳት ፍቃደኛ ልትሆን አትችልም። ፍላጎት ቢኖራት እንኳን የወንድ አጋሯን ፍቃድ ማግኘት ይኖርባታል'' ስትል በስራዋ ላይ ስለሚያጋጥሟት ችግሮች ታስረዳለች።

Image copyright Mihaela Noroc
አጭር የምስል መግለጫ አቢ እና አንጄላ የተባሉት እህትማማቾች በኒው ዮርክ አሜሪካ
Image copyright Mihaela Noroc
አጭር የምስል መግለጫ የወታደራዊ ሙዚየም አስጎብኚ፤ ፕዮንግያንግ ሰሜን ኮሪያ
Image copyright Mihaela Noroc
አጭር የምስል መግለጫ እናት እና ሁለት ልጆች ሶሪያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ሸሽተው ግሪክ በሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ይኖራሉ።

ሚሃኤላ የዓለማችን ተዋቂ እና ባለፀጋ ግለሰቦች ለውበት እውነተኛ ያልሆነ መገለጫዎች ከመስጠታቸውም በላይ የማይጨበጥ አድረገውታ ትላለች።

ይሁን እንጂ በጊዜ ሂደት ውስጥ ተፍጥሯዊ የሆነው ውበት በዓለም ተቀባይነቱ እየጨመረ መምጣቱ አይቀርም ስትል ሚሃኤላ ትናገራለች።

Image copyright Mihaela Noroc
አጭር የምስል መግለጫ ከግራ ወደ ቀኝ ሚሃኤላ ፎቶግራፎች ያነሳችው ኔፓል ካትማንዱ እና በአይስላንድ ዋና ከተማ ሬኬጂቨ ነው።

ተያያዥ ርዕሶች