ትራምፕ ከዢ ጋር ስለሰሜን ኮሪያ ጉዳይ ይነጋገራሉ

Donald Trump and first lady Melania walk down the stairs on Air Force One Image copyright Reuters

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ቻይና ባደረጉት ጉብኝት ትኩረታቸውን በሰሜን ኮሪያ ጉዳይ ላይ በማድረግ ውይይት ያደርጋሉ ተብሏል።

ትራምፕ በደቡብ ኮሪያ ፓርላማ ተገኝተው ቻይና ሰሜን ኮሪያን ይበልጥ እንድታገል ከጠየቁ በኋላ ነው ቤጂንግ የደረሱት።

ቻይና የሰሜን ኮሪያን ኒውክለር ፕሮግራም ልትቆጣጠረው ትችላለች ብላ ብታስብም ቤጂንግ በበቂ ሁኔታ እየተንቀሳቀስኩ ነው ብላለች።

የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ትራምፕን ሞቅ ባለ ስነ-ስርዓት ተቀብለዋቸዋል።

Image copyright Reuters

"ከታላቅ ፖለቲካዊ ድል" በኋላ ዢንን ለማግኘት በመዘጋጀታቸው ትራምፕ ደስተኛ መሆናቸውን ጠቅሰው ለዢ ሙገሳ ችረዋል።

ትራምፕ በቻይና ምን ዓይነት አቀባበል ጠበቃቸው?

ትራምፕ እና ባለቤታቸው ሜላኒያ ቤጂንግ ሲደርሱ በቀይ ምንጣፍ፣ ወታደራዊ ባንድ እና ሁለቱን ሃገራት ሰንደቅ ዓላማ በያዙ ህጻናት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የቀድሞው አሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ከስልጣን ከመውረዳቸው ጥቂት ቀደም ብሎ ወደ ቻይና ሲያቀኑ ቀይ ምንጣፍ ያልነበረ ሲሆን ይህም ታስቦ የተደረገበት ነው ተብሏል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕና ቀዳማዊ እመቤት ሜላኒያ የቻይና ነገስታት መቀመጫ የነበረችውን ፎርቢደን ሲቲን የጎበኙ ሲሆን ከሰዓት በኋላ የሻይ ግብዣ ተደርጎላቸዋል።

Image copyright Reuters

ትራምፕ የልጅ ልጃቸው በማንዳሪን ቋንቋ ስትዘፍን የሚያሳይ ቪዲዮ ለዢ ማሳየታቸውን የቻይና መንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። ዢ ቪዲዮው አስደናቂ መሆኑን መናገራቸውንም ጠቁመዋል።

ከሌሎች አሜሪካ ፕሬዝዳንቶች በተለየ መልኩ ትራምፕና ሜላንያ ከቻይናው መሪ እና ባለቤታቸው ጋር በጋራ በፎርቢደን ከተማ እራት እንደሚመገቡ ሲ ኤን ኤን ዘግቧል።

"ለማይረሳው ቀንና ምሽት" ሲሉ ሲሉ ትራምፕ ለቻይናው መሪ ምስጋናቸውን በትዊተር ገጻቸው አስተላልፈዋል።