"ይህ ፈጠራ ወደፊት ብዙ ነገሮችን እንደሚቀይር ከአሁኑ መናገር እችላለሁ።''

ፕላስቲክ እንዴት ኑሮን ሊቀይር ቻለ Image copyright ALAMY

"ካልተሳሳትኩ በቀር ይህ ፈጠራ ወደፊት ብዙ ነገሮችን እንደሚቀይር መናገር እችላለሁ።'' ሌዎ ቤክላንድ ይህንን ፅሁፍ ያሰፈረው በ43 ዓመቱ በአውሮፓውያኑ ሐምሌ 1907 ነበር፤ ።

ቤልጂየም የተወለደው ሌዎ አባቱ ጫማ ሰፊ ነበሩ። ልጁን ወደ ጫማ ሰሪነት በ13 ዓመቱ አባቱ ቢያስገቡትም እናቱ ግን ለልጁ ሌሎች ነገሮች ያስተምሩት ነበር።

በእናቱ እርዳታ ሌዎ ወደ ማታ ትምህርት ገባ፤ ወደ ጌንት ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባውን ነፃ የትምህርት ዕድል ማግኘትም ቻለ። በ20 ዓመቱ በኬሚስትሪ ጥናት የዶክትሬት ዲግሪውን አገኘ።

የአስጠኚውን ሴት ልጅ ካገባ በኋላ ወደ ኒው ዮርክ በማቅናት ለፎቶግራፍ የሚሆኑ ወረቀቶች በማምረት ረብጣ ገንዘብ ማግኘትም ቻለ። በአውሮፓውያኑ ሐምሌ 1907 ኒው ዮርክ ከተማ በገነባው ቤት ውስጥ የራሱን ቤተ-ሙከራ በመገንባት ምርምሩን ተያያዘው።

በዚያው ዓመት ሐምሌ ወር መጨረሻ ሌዎ ፕላስቲክ መሰል ግኝት ማግኘት ቻለ፤ 'ባኬላይት' ብሎም ጠራው። ስለ ፕላስቲክ በዛን ጊዜ የፃፈው ነገር እውን እየሆነ መምጣት ጀመረ። በአጭር ጊዜ ውስጥ ፕላስቲክ በየቦታው ተዳረሰ።

እምቅ ኃይል

ፕላስቲክ አሁን ላይ ከሚመረተው ጠቅላላ የነዳጅ ምርት ስምንት በመቶ ያህሉን ይጠቀማል፤ ግማሹን በጥሬ ዕቃነት ግማሹን ደግሞ በኃይል መልክ።

ባኬላይት ኮርፖሬሽን ምርቱን በሚያስተዋውቅበት ወቅት "ሰዎች የእንስሳትን፣ ንጥረ ነገርንና አትክልቶችን ድነበር ተጋፍቷል። አሁን አራተኛውን ሥርወ-መንግሥት ይዘን መጥተናል፤ ተገፍቶ የማይልቅ ድንበር" ሲል ነበር ያስነገረው።

ኮርፖሬሽኑ ፕላስቲክን "ለሺህ ጥቅሞች የሚውል ዕቃ" ሲል ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ለገበያ ያቀረበው።

ስልኮች፣ ሬዲዮ፣ የጦር መሣሪያ፣ ኩባያ፣ ጌጣጌጥ. . . በርካታ ዕቃዎች ምንጫቸው ከፕላስቲክ ነው። አልፎም ፕላስቲክ በመጀመሪያው የአቶም ቦምብ ውስጥም ይገኝ ነበር።

ባኬላይት ያገኘው ስኬት በአውሮፓውያኑ 1920ዎቹና 30ዎቹ ሰዎች ወደ መሰል ምርምሮች እንዲገቡ ምክንያት ሆነ። ናይለንና ስቶኪንግ የመሳሰሉ ፕላስቲክ ነክ ምርቶች ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ።

የፕላስቲክ ታዋቂነትና ባለፉት ዓመታት እጅጉን እየላቀ መጣ። በሚቀጥሉት 20 ዓመታትም የፕላስቲክ ጥቅም በእጥፍ እንደሚያድግ ነው ባለሙያዎች የሚያስረዱት።

Image copyright Getty Images

ተለዋዋጭ ትርጉም

ፕላስቲክ አካባቢ ላይ ያለውን አሉታዊ ተፅዕኖ ማንም አይክድም። በዓይናችን ለምናየው ጉዳት በዘለለ ፕላስቲክ የእንስሳት ዕድገት ላይ እያሳደረ ያለው ትልቅ ተፅዕኖ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።

ፕላስቲክ መሬት ውስጥ ከገባ በኋላ ውሃ ይዞት ወደ ውቅያኖስ ይወርዳል። የውቅያኖስ አካላትም ይመገቧቸዋል። ፕላስቲኮቹ በእንስሳቱ አማካይነት ተመልሰው በምግብ መልክ ወደ ሰዎች ይመጣል።

በዚያው ልክ ፕላስቲክ ያለው ጥቅም የትየለሌ ነው።

ከፕላስቲክ የሚመረቱ ተሽከርካሪዎች እጅግ ቀላልና ዝቅ ያለ መጠን ያለው ነዳጅ የሚጠቀሙ ናቸው። በፕላስቲክ የሚታሸጉ ምግቦች ለብዙ ጊዜ ሳይበላሹ መቆየት ይቻላሉ። ፕላስቲክ ከሌሎች ባሕላዊ ዕቃዎች በተለየ ለብዙ ጊዜ የመቆየት ባህሪ ስላለው የቆሻሻ መጠንን ይቀንሳል።

Image copyright copyrightREDETEC

መልሶ መጠቀም

ፕላስቲክን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ላይ ብዙ ሊለፋ እንደሚገባ በተደጋጋሚ ሲነገር ይሰማል። ምክንያቱም ነዳጅ ለዘላለም ሊቆይ ስለማይችል።

አንዳንድ የፕላስቲክ ምርቶችን መልሱ ጥቅም ላይ ማዋል እጅጉን ከባድ ነው። አብዛኛዎቹን ምርቶችን ግን መልሶ መጠቀም ይቻላል። ነገር ግን ከፕላስቲክ ማሸጊያዎች ውስጥ ሰባት በመቶውን ብቻ መልሰን እየተጠቀምን እንደሆነ ይነገራል። ሌሎች የፕላስቲክ ምርቶችን መልሶ የመጠቀም ሂደት ላይ ችግር አለ ይላሉ ባለሙያዎች ።

በተለይ ፕላስቲክ አምራቾች ምርቱን መልሶ ጥቅም ማዋል ላይ ቢሠሩ ትልቅ ለውጥ እንደሚመጣ እሙን ነው።

በዚህ ረገድ ታይዋን እያንዳንዱን የፕላስቲክ ምርት መልሳ ጥቅም ላይ በማዋልና ይህንን በማያደርጉ ዜጎች ላይ ደግሞ ቅጣት በማስተላለፍ ትልቅ ለውጥ ማምጣት ችላለች።

አሁንም አዲስ የፕላስቲክ ምርቶችን ማግኘቱ ጉዳይ ያከተመ አይመስልም። ሌዎ በ1907 የፃፈው ማስታወሻም ከመቶ ዓመታት በኋላ እውን ሆኖ ተግኝቷል።

ተያያዥ ርዕሶች