ሰራዊቱ መፈንቅለ-መንግሥት የሚለውን ቃል ለምን ፈራው?

Image copyright AFP

"ማሳወቅ የምንፈልገው ጦሩ መንግሥት ገልብጦ ስልጣን አልያዘም" ዕለተ ረቡዕ ንጋት ጄኔራል ሲቡሲሶ ሞዮ በዚምባብዌ ብሔራዊ ቴሌቪዥን (ዜድቢሲ) ላይ በመቅረብ ያነበቡት መግለጫ ነው።

ጄኔራሉ ቀድመው መፈንቅለ-መንግሥት አይደለም ማለትንም መርጠዋል።

  • ግን ለምን?

የአፍሪካ ሕብረትም ሆነ የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማሕበረሰብ (ሳድክ) መፈንቅለ-መንግሥት አካሂደው ስልጣን ለያዙ አካላት ዕውቅና አይሰጡም።

በ2015 በቡርኪና ፋሶው የቀድሞ መሪ ብሌይዝ ኮምፓዎሬ መንግሥት ላይ ተፈፅሞ የነበረውን መፈንቅለ-መንግሥት የአፍሪካ ሕብረት ከመቃወሙም በላይ ሃገሪቱ ላይ ቅጣት አስተላልፎም ነበር።

የሃገሪቱ ጦር በፍጥነት ወታደራዊ ያልሆነ መንግሥት ማቋቋሙ ይታወሳል።

ገና ከአሁኑ የደቡብ አፍሪካው መሪ ጃኮብ ዙማ ሳድክን በመወከል በዚምባብዌ የሚካሄድ ማንኛውንም ዓይነት ሕገ-ወጥ የሥልጣን ሽሽግግር በማሕበረሰቡ ተቀባይነት የለውም ሲሉ ተሰምተዋል።

ለዚህም ይመስላል የዚምባብዌ ጦር መፈንቅለ-መንግሥት ሳይሆን የጦር ወንጀለኞችን በቁጥጥር ሥር በማዋል ላይ ነኝ ሲል የሚሰማው።

እስካሁን ድረስ ድምፃቸው ያልተሰማው ሙጋቤ በቁም እሥር ላይ እንደሚገኙ ተዘግቧል።

• ዛኑ ፒኤፍ ፓርቲ፡ ''ሮበርት ሙጋቤ በቁጥጥር ስር ውለዋል''

ተያያዥ ርዕሶች