የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሲመለስ አርሴናል ቶተንሃምን ያስተናግዳል

mark lawrenson Image copyright BBC Sport

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሲመለስ አርሴናል ቶተንሃምን በሚያስተናግደበት የምሳ ሰዓት ጨዋታ ይጀመራል።

የቢቢሲ ስፖርት ተንታኙ ላውሮ "ቀደም ባለው ጊዜ ቢሆን ኖሮ ለአርሴናል የአሸናፊነት ዕድሉን እሰጥ ነበር፤ አሁን ግን ነገሮች ተቀይረዋል" ይላል።

ላውሮ የዚህን ተጠባቂ ጨዋታ ጨምሮ የሳምንቱን ሌሎች ጨዋታዎች ግምት እንዲህ ያስቀምጣል።

ቅዳሜ

አርሴናል ቶተንሃም

Image copyright BBC Sport

ሁለቱ ክለቦች በጣም በጥንቃቄ እንደሚጫወቱና ለአቻ ውጤት እንደሚሄዱ አስባለሁ። በውጤቱም ደስተኛ እንደሚሆኑ ጭምር።

አርሰን ቬንገር ባለፈው ከማንቸስተር ሲቲ ጋር በነበራቸው ጨዋታ አድልዎ ተፈፅሞብናል ቢሉም ሲቲ ማሸነፍ ይገባው ነበር።

ቶተንሃም ታግሎም ቢሆን ከክሪስታል ፓላስ ጋር የነበረውን ጨዋታ ማሸነፍ ችሏል።

ቶተንሃሞች በዚህ ሳምንት በተሻለ ብቃት እንደሚታዩ አስባለሁ፤ ምክንያቱም ሃሪ ኬይን፣ ዴሊ አሊና ሃሪ ዊንክስ ከጉዳት ተመልሰዋልና።

ላውሮ፡ 1 - 1

ቦርንማውዝ ከሃደርስፊልድ

Image copyright BBC Sport

ይህንን ጨዋታ ቦርንማውዝ እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ። ባለፈው ቦርንማውዞች ከኒውካስል ጋር በነበራቸው ፍልሚያ ያሳዩት ብቃት እጅግ ድንቅ ነበር።

በጨዋታው መጀሪያ ግማሽ ላይ ከፍተው እየተጫወቱ የነበሩት ቦርንማውዞች በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ ተንቀሳቅሰዋል። ውጤቱ ለቡድኑ ምን ያህል ትርጉም እንደነበረውም በጨዋታው ማብቂያ ላይ አስልጣኙ የነበረውን ፈንጠዚያ አይቶ መረዳት ይቻላል።

ላውሮ፡ 2 - 0

በርንሌይ ከስዋንሲ

Image copyright BBC Sport

በርንሌይ ግስጋሴያቸውን ሲቀጥሉበት ስዋንሲዎች በተቃራኒው ወደ ወራጅ ቀጣና እያመሩ ይገኛሉ። ስዋንሲዎች ይህን ሊቀይሩት እንደሚችሉ አምናለሁ ግን አጥቂ ክፍላቸው በጣም መጠናከር አለበትም ባይ ነኝ።

ስዋንሲ በርንሌይ ላይ ምንም ዓይነት አደጋ ይፈጥራል ብዬ አላስብም።

ላውሮ፡ 2 - 0

ክሪስታል ፓላስ ከአቬርተን

Image copyright BBC Sport

የእንግሊዙ ሩብን ሎፍተስ-ቺክ ብሔራዊ ቡድኑ ከጀርመን ጋር በነበረው ጨዋታ ያሳየውን ብቃት በቡድኑ ክሪስታል ፓላስም ይደግመው ይሆን የሚለው የበርካቶች ጥያቄ ነው። ነገር ግን ብቁ ሆኖ መሰለፍ ከቻለ ብቻ ነው።

ኤቨርተን በተጠባባቂ አሰልጣኙ ዴቪድ አንስዎርዝ እየተመራ ለዚህ ጨዋታ መቅረቡ አስገርሞኛል። ምክንያቱም በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በነበረው ክፍት ጊዜ ኤቨርተን አዲስ አሰልጣኝ ይቀጥራል የሚል ተስፋ ነበረኝ።

ኤቨርተን ምንም ዓይነት ለውጥ ሳያሳይ ወደ ጨዋታው ሲመጣ ፓላስ ግን ሮይ ሆጅሰንን ከቀጠረ በኋላ በጣም ጥሩ የአቋም ለውጥ ማምጣት ችሏል።

ላውሮ፡ 2 - 1

ሌይስተር ሲቲ ከማንችስተር ሲቲ

Image copyright BBC Sport

ሌይስተር የሲቲን የማሸነፍ ጉዞ ይገታው ይሆን? አይመስለኝም።

የሌይስተር አስልጣኝ ከሲቲ ጋር በሚኖረው ጨዋታ ምን ዓይነት ቅርፅ ይዞ እንደሚመጣ ለማየት ጓጉቻለሁ። በተለይ ደግሞ በጄሚ ቫርዲ ብቻ ሲቲ እንዴት ሊቋቋመው እንደሚችል ማየትም እፈልጋለሁ።

ሌይስተር ከዚህ ጨዋታ የሚያገኘው ማንኛውም ዓይነት ነጥብ እንደ ተጨማሪ ነው የማየው።

ላውሮ፡ 0 - 2

ሊቨርፑል ከሳውዝሃምፕተን

Image copyright BBC Sport

ባለፈው የክረምት ዝውውር መስኮት ሊቨርፑል በጣም ፈልጎት ሳውዝሃምፕተን ግን በፍፁም ሊሸጠው ያልፈለገው ቪርጂል ቫን ዳይክ የጨዋታው መነጋገሪያ ርዕስ እንደሚሆን አስባለሁ።

በጨዋታው ላይ ሳዲዮ ማኔ መሰለፍ ባይችልም ሊቨርፑል ግን ያሸንፋል ባይ ነኝ።

ላውሮ፡ 2 - 0

ዌስትብሮምከቼልሲ

Image copyright BBC Sport

ቼልሲዎች ባለፈው ጨዋታ ዩናይትድን ሲያሸንፉ አሁንም ምን ያህል ጠንካራ እንደሆኑ ማሳየት ችለዋል። ለቶኒ ፑሊስ ቡድን ዌስትብሮም በዚህ ሳምንት ለቼልሲዎች ሌላ ፈተና እንደሚሆኑም እሙን ነው።

ከነሃሴ ጀምሮ በተደረጉ ጨዋታዎች ቶኒ ፑሊስ ማሸነፍ ተስኗቸዋል። ይህም ጨዋታ እጅገ ተስፋ የሚጣልበት አይደለም።

ላውሮ 0 - 2

ማንችስተር ዩናይትድ ከኒውካስል

Image copyright BBC Sport

የራፋ ቤኒቴዝ ቡድን ኒውካስል በዚህ የውድድር ዘመን እያሳየ ያለው ብቃት አስደሳች ነው። ነገር ግን ጠንካራ አማካይ እንደሚያስፈልጋቸው እርግጥ ነው።

ኒውካስል ለማንችስተር አስቸጋሪ እንደሆነ ባምንም ውጤቱ ግን ለቀያዮቹ ሰይጣኖች እንደሚሆን አልጠራጠርም።

ላውሮ፡ 2 - 0

ዕለተ ዕሁድ

ዋትፎርድ ከዌስትሃም

Image copyright BBC Sport

ዴቪድ ሞዬስ የዌስትሃም አሰልጣኝ በመሆን በሚያከናውኑት የመጀመሪያ ጨዋታቸው ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ መመልከት የሚያጓጓዋ ይመስለኛል።

ምንም እንኳ ዌስትሃም ወራጅ ቀጣና ውስጥ ቢገኝም በጣም ምርጥ ብቃት ያላቸው ተጫዋቾችን የያዘ ቡድን ነው።

ላውሮ፡ 2 - 0

ሰኞ

ብራይተን ከስቶክ

Image copyright BBC Sport

ብራይተን በጣም በሚገርም ሁኔታ ያልተጠበቀ ድንቅ ውጤት በማስመዝገብ የብዙዎችን አፍ ማዘጋት የቻለ ቡድን ሆኗል።

ቢሆንም ስቶክ ታግሎ ውጤት ማምጣት የሚችል ቡድን ነው። ለዚህም ነው ይህንን ጨዋታ ስቶክ ያሸንፋል ብዬ በልበ ሙሉነት የምናገረው።

ላውሮ፡ 0 - 2