የሳምንቱ መጨረሻ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት

ሳም አላርዳይስ የኤቨርተን አሰልጣኝነታቸውን ጊዜ ቅዳሜ ከሃደርስፊልድ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀምራሉ። በጉዲሰን ፓርክ ምን ውጤት ያስመዘግቡ ይሆን?

የቢቢሲ ስፖርቱ የእግር ኳስ ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን ኤቨርተን 2 ለ 0 ያሸንፋል ይላል፤ ይስማማሉ?

ቅዳሜ

Image copyright BBC Sport

ቼልሲ ከ ኒውካስል

ረቡዕ ዕለት ከስዋንሲ ጋር የተጫወተው ቼልሲ ጥሩ ባይጫወትም አሸንፎ ለመውጣት ግን ችሏል።

የላውሮ ግምት፡ 2 ለ 0

Image copyright BBC Sport

ብራይተን ከ ሊቨርፑል

ሊቨርፑል ስቶክን 3 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ በተወሰነ ደረጃ ዕድለኛ ነበር። ነገር ግን የየርገን ክሎፕ ቡድን ሞሀመድ ሳላህ ከተቀያሪ ወንበር ተነስቶ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር አሸናፊነቱን ለማረጋገጥ ችሏል።

የላውሮ ግምት፡ 0 ለ 2

Image copyright BBC Sport

ኤቨርተን ከ ሀደርስፊል

ሳም አላርዳይስ የኤቨርተን አሰልጣኝነት ሥራቸውን በመልካም ውጤት ይጀምሩታል ብዬ እጠብቃለሁ።

የላውሮ ግምት፡ 2 ለ 0

Image copyright BBC Sport

ሌስተር ከ በርንሌይ

የሌስተሩ አሰልጣኝ ማስደመማቸውን ይቀጥላሉ።

የላውሮ ግምት፡ 1 ለ 1

Image copyright BBC Sport

ስቶክ ከ ስዋንሲ

ሁለቱም ቡድኖች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ቢሆኑም ስዋንሲ ግን በበለጠ ችግር ውስጥ ነው።

የላውሮ ግምት፡ 2 ለ 0

Image copyright BBC Sport

ዋትፎርድ ከ ቶተንሃም

ማክሰኞ ዕለት በሌስተር የተሸነፉበትን ጨምሮ በቅርቡ ቶተንሃም ደካማ አቋምን ያሳየ ነው።

የላውሮ ግምት፡ 1 ለ 2

Image copyright BBC Sport

ዌስት ብሮም ከ ክሪስታል ፓላስ

አዲሱ የዌስት ብሮም አሰልጣኝ አለን ፓርዲው ለቦታው ተስማሚ ጥሩ አሰልጣኝ ናቸው።

የላውሮ ግምት፡ 2 ለ 1

Image copyright BBC Sport

አርሰናል ከ ማንችስተር ዩናይትድ

ይህ በቀዳሚው ስድስት ደረጃዎች ውስጥ በሚገኙ ሁለት ቡድኖች መካከል የሚደረግ ትልቅ ጨዋታ ነው። አቻ ይለያያሉ ብዬ እገምታለሁ።

የላውሮ ግምት፡ 1 ለ 1

ዕሁድ

Image copyright BBC Sport

ቦርንማውዝ ከ ሳውዝሃምፕተን

ሳውዝሃምፕተን በሳምንቱ አጋማሽ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ባደረገው ጨዋታ ጥሩ ውጤትን አስመዝግቧል። በ96ኛው ደቂቃ ላይ በስተርሊንግ ግብ ተሸንፏል።

የላውሮ ግምት፡ 0 ለ 2

Image copyright BBC Sport

ማንችስተር ሲቲ ከ ዌስት

በሳምንቱ አጋማሽ ጨዋታ ዌስት ሃም በኤቨርተን ሽንፈት ገጥሞታል። በቀጣይ ጨዋታዎች ለማገገም የሚያስችል ውጤት ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል፤ በተጨማሪም በጥር ወር የዝውውር መስኮት ችግራቸውን ለመፍታት ይሞክራሉ።

የላውሮ ግምት፡ 3 ለ 0