የቪክቶሪያ ሐይቅ በተለያዩ ኬሚካሎች በመበከሉ የተነሳ የሚሰጠው የአሳ ምርት በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል

የቪክቶሪያ ሃይቅ በዙሪያው ላሉ ነዋሪዎች ለዘመናት የአሳ ምርት ሲሰጥ ቆይቷል። ከ1980 ጀምሮ ግን የብዝሃ-ሕይወት ይዞታው በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል። ይህ ደግሞ በሐይቁ የአሳ ምርት ላይ ህይወታቸውን ለመሰረቱ አስደንጋጭ ነው።