ጣሊያናዊው 'ረክሰዋል' ያላቸውን ዘመዶቹን መረዘ

የመርዝ ብልቃጥ Image copyright Thinkstock

የጣሊያን ፖሊስ ከሃይማኖት አንፃር 'ረክሰዋል' ያለቸውን የቤተሰቡን አባላት በአይጥ መርዝ ገድሏል ያለውን ግለሰብ መያዙን አስታወቀ።

የ27 ዓመቱ ማቲያ ዴል ዞቶ መርዛማውን ታሊየም የተባለ ኬሚካል በምግባቸው ላይ በመጨመር በአባቱ በኩል ያሉትን አያቶቹንና አክስቱን ገድሏል ተብሎ ነው የተከሰሰው።

በተጨማሪም ሌሎች አምስት ዘመዶቹ በመርዙ ምክንያት ሆስፒታል ገብተው ህክምና እየተደረገላቸው ነው።

ፖሊስ ግለሰቡ ኮምፒውተር ውስጥ መርዙን የገዛበት ደረሰኝን ካገኘ በኋላ ነበር ዴል ዞቶን ሚላን አቅራቢያ በምትገኘው ሞንዛ ስፍራ በቁጥጥር ስር ያዋለው። ከተያዘ በኋላም በሰጠው የዕምነት ቃል ረክሰዋል ያላቸውን የቤተሰቡን አባላት ''ለመቅጣት'' የፈፀመው ድርጊት እንደሆነ መናገሩን አቃቤ ህግ ገልጿል።

እናቱ ለመርማሪዎች እንደተናገሩት ዴል ዞቶ በቅርቡ ብዙም የማይታወቅ የዕምነት ቡድንን መቀላቀሉን የጣሊያን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ታሊየም በውሃ ውስጥ በቀላሉ የሚዋሃድ ሲሆን ሽታና ጣዕም አልባ መርዝ ነው።

ተያያዥ ርዕሶች