የአፍሪካ ሳምንት በምስል

ባሳለፍነው ሳምንት አፍሪካ እና አፍሪካዊያንን ሊያሳዩ የሚችሉ የተለያዩ ምስሎችን እንደሚከተለው ቀርበዋል።

A woman at a rally in Abuja Image copyright Reuters

ባለፈው ማክሰኞ በናይጄሪያ ዋና ከተማ አቡጃ ሴቶች የተሻለ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በሚጠይቅ ሠላማዊ ሰልፍ ላይ አንድ ሠልፈኛ ፎቶ እየተነሳች ትታያለች

Fifi Loukoula Image copyright AFP

የኮንጎ ብራዛቪሏ ፊፊ ሉኩላ ሜክሲኮ ባዘጋጀችው በዓለም ፓራ የክብደት ማንሳት ሻምፒዮንሺፕ ላይ ስትወዳደር

Cameroonian handball player Image copyright EPA

በጀርምን እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም የሴቶች የእጅ ኳስ ውድድር ላይ የካሜሮኗ ቫኔሳ ጂፕሙ ሜዲቤ የኔዘርላንድ ተጫዋቾችን ለማለፍ ስትሞክር

A dancer Image copyright AFP

የሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካርን የሚያገለግለው አዲስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲከፈት ሴኔጋላዊቷ ዳንሰኛ በትርኢት ላይ

Sierra Leonean singer Janka Nabay Image copyright AFP

ባህላዊ የቡቡ ሙዚቃ ተጫዋች ሆነው ሴራሊዮናዊው ሙዚቀኛ ጃንካ ናባይ ባለፈው ረቡዕ በፈረንሳይ ሬንስ ከተማ በተዘጋጀ ፌስቲቫል ላይ

People looking out of windows Image copyright AFP

አልጄሪያዊያን በዋና ከተማቸው አልጀርስ በመስኮታቸው በኩል በመሆን የፈረንሳዩን ፕሬዝዳንት በጉዳና ላይ እያዩ ነው...

French President Emmanuel Macron Image copyright AFP

ከፈረንሳይ ቅኝ አገዛዝ ለመላቀቅ ከፍተኛ ጦርነት ውስጥ ገብታ የነበረችውን አልጄሪያን ፕሬዝዳንት ኢማኑዌል ማክሮን ለመጀመሪያ ጊዜ ጎብኝተዋል።

Protesters burn a US flag Image copyright Reuters

እሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ ናት ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መግለጻቸውን ተከትሎ ሐሙስ በቱኒዝያ ተቃዋሚዎች የአሜሪካንን ሰንደቅ ዓላማ አቃጥለዋል።

A migrant protestsing Image copyright EPA

በሊቢያ የሚገኙ ስደተኞች መሸጣቸውን ተከትሎ አቴንስ በሚገኘው የግሪክ ፓርላማ ፊት ለፊት ስደተኞች የተቃውሞ ሠልፍ አካሂደዋል. . .

A woman plays with a child Image copyright AFP

ወደ አውሮፓ ለመሻገር ስትሞክር በሊቢያ ስትሰቃይ የቆየች ናይጄሪያዊት ባለፈው ማክሰኞ ወደ ሃገሯ ተመልሳለች።

Children drawing in Juba Image copyright AFP

በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ግቢ ህጻናት የሃገሪቱን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪርን ምስል ሲስሉ

A child Image copyright AFP

በቀድሞዋ ዛዬር በአሁኗ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ባለፈው እሁድ ይህ ህጻን በአንድ አሮጌ አዳራሽ ውስጥ

A supermoon rises Image copyright EPA

በደቡብ አፍሪካዋ ኬፕ ታውን ከተማ ቴብል ተራራ አቅራቢያ ጨረቃ ደምቃ ታይታለች።

Swahili Fashion Week Image copyright AFP

የአፍሪካ ምርቶችን ለማስተዋወቅ የስዋሂሊ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ሃገራት በዓመታዊው ዝግጅት ላይ ተካፍለዋል. . .

Queen Elizabeth II Image copyright AFP

ንግስት ኤልዛቤት በእንግሊዝ የናይጄሪያ አምባሳደር የሆኑትን ጆርጅ አዴሶላ ኦጉንታዴ እና ባለቤታቸውን በባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት ባለፈው ረቡዕ ሲቀበሉ

የፎቶ ምንጮች ኤኤፍፒ፣ ኢፒኤ እና ሮይተርስ ናቸው።