ግብፃዊቷ ሙዚቀኛ በሙዝ አበላሏ የሁለት ዓመት እስር ተፈረደባት

Shyma appears in the video for I Have Issues Image copyright Shyma

የግብፅ ፍርድ ቤት በሙዚቃ ቪዲዮዋ ላይ በተገላለጠ መልኩ ሙዝ አግባብ በሌለው መልኩ በልታለች ያላትን ሙዚቀኛ የሁለት አመት እስር ፈርዶባታል።

ወግ አጥባቂ በሆነው ማህበረሰብ ውስጥ ቪዲዮው ከፍተኛ ተቃውሞ በማስነሳቱ ነው የ25 ዓመት እድሜ ያላት ሺይማ አህመድ ባለፈው ወር ለእስር የበቃችው።

'ስሜት በመቀስቀስ' እንዲሁም 'ነውረኛ' የሆነ ፊልም ሰርታለች በሚል ጥፋተኛ ሆና እንደተገኘች የሃገሪቱ ሚዲያ ዘግቧል።

እሷ ብቻ ሳትሆን ቪዲዮውንም ዳይሬክት ያደረገው በሌለበት የሁለት አመት የእስር ፍርድ ተፈርዶበታል።

ሻይማ በቁጥጥር ስር ከመዋሏ በፊት ይቅርታ የጠየቀች ሲሆን "አግባብ የሌለው ባህርይም አሳይቻለሁ" ብላለች።

በተጨማሪም " ይሄ ሁሉ ይፈጠራል ብዬ አላሰብኩም፤ ከዚህ ሁሉ ሰው ጥቃት ይደስርብኛል ብዬ አልገመትኩም" በማለት አሁን የጠፋው የፌስቡክ ገጿ ላይ ፅፋ ነበር።

ባለፈውም አመት የግብፅ ፍርድ ቤት ሶስት ሴት ዳንሰኞችን 'ስሜት ቀስቃሽ' ቪዲዮ ሰርታችኋል በሚል የስድስት ወራት እስር ፈርዶባቸዋል።

ሌላኛዋ ሙዚቀኛ በበኩሏ ከናይል ወንዝ መጠጣት ለህመም ያጋልጣል በማለቷ ድፍረትን የተሞላ ንግግር በአደባባይ አድርጋለች በሚል ፍርዷን እየጠበቀች ነች።

ሽሪን አብደል ዋሀብ የተባለችው ግብፃዊ ሙዚቀኛ ባለፈው ወር የሙዚቃ ዝግጅት ላይ "ከናይል ወንዝ ጠጥታችኋል ወይ?" የተሰኘውን ዘፈን ዝፈኚ ስትባል በሽታ ያመጣል በማለቷ ነው ክሱ የተመሰረተባት።

ምላሿም "ከናይል ወንዝ መጠጣት ቢልሀርዚያ በሽታን ያስከትላል" የሚል ነው።

ሰኞ ዕለትም የግብፅ የሙዚቀኞች ማህበር ይህችኑ ሙዚቀኛ ከማንኛውም የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ለሁለት ወራት እንዳትሳተፍ አግዷታል።

ተያያዥ ርዕሶች