በአትላንታ አየር ማረፊያ መብራት በመቋረጡ በረራዎች ተሰናከሉ

Passengers affected by widespread power outage sit in airport terminal and wait for updates Image copyright EPA

በአትላንታዋ ሀርትስፊልድ ጃክሰን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መብራት በመቋረጡ ምክንያት ጣቢያው ግማሽ በግማሽ እንዲዘጋና በረራዎችም በከፍተኛው መዘግየት እንዲያጋጥማቸው ምክንያት ሆኗል።

ይህ አየር ማረፊያ በዓለም ስራ ከሚበዛባቸው አንዱ ሲሆን በቀንም ውስጥ ከ250 ሺ መንገደኞች በላይ እንዲሁም 2500 በረራዎችን ያስተናግዳል።

ተጓዦቹ ለሰዓታትም ያህል ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ በተዋጠው አውሮፕላን ማረፊያና በአውሮፕላን ውስጥ ተቀምጠው ነበር።

በአየር ማረፊያው እንዲያርፉ እቅድ ተይዞላቸው የነበሩ በረራዎች ወደ ሌላ አየር መንገድ አቅጣጫቸውን እንዲቀለብሱ ወይም መውጫ አየር ማረፊያው ላይ እንዲያርፉ ተደርገዋል።

አየር ማረፊያው ባወጣውም መግለጫው እሁድ ዕለት ከ12 ሰዓት በኋላ ያጋጠመ ነው ብለዋል።

ለአየር መንገዱ የመብራት አቅርቦት የሚሰጠው ጆርጂያ ፓወር በበኩላቸው በመሬት ስር እሳት ተነስቶ ሳይሆን እንዳልቀረ ያምናሉ።

እሳቱ የተነሳበት ምክንያት እንደማያውቁና እሁድ ሌሊትም መብራት ይመለሳል ብለዋል።

በረራዎቹን የሚቆጣጠረው ማማ በትክክለኛ መንገድ እየሰራ ቢሆንም ብዙዎቹ አየር መንገዶች እንደ ዩናይትድ፣ሳውዝዌስትና የአሜሪካው አየር መንገድ በዕለቱ ስራ ሙሉ በሙሉ አቋርጠዋል።

በተለያዩ ድረ-ገፆችም የታዩ ፎቶዎች መንገደኞች በጨለማ ውስጥ ሲጠብቁ አሳይተዋል።

የዴልታ አየር መንገድ በትዊተር ገፁ እንዳሰፈረው ያረፉ መንገደኞችን ለማስወረድ ቢሞክሩም የነበሩት በሮች ትንሽ በመሆናቸው እክል እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል።

የአካባቢው ፖሊስ ሁኔታውን ለማረጋጋት ተጨማሪ ፖሊሶች እንደላኩ ገልፀዋል።

አትላንታ 80% የሚሆነው ከአሜሪካ ህዝብ በሁለት ሰዓት በረራ መገኘቷ በሀገሪቷ ተመራጭ አየር መንገድ እንዲሁም ከሌላ ሀገር ለሚመጡትም ዋነኛ አየር መንገድ ሆኖም ያገለግላል።

ተያያዥ ርዕሶች