የአሜሪካ ሕግ አውጪዎች በይነ-መረብን በተመለከተ ሁላችንንም የሚነካ ውሳኔ አሳልፈዋል።

የአሜሪካ ሕግ አውጪዎች በይነ-መረብን በተመለከተ ሁላችንንም የሚነካ ውሳኔ አሳልፈዋል።

የአሜሪካ ፌደራል ኮሚዩኒኬሽን ኮሚሽን በኦባማ ዘመን ተግባራዊ የሆነውን የበይነ-መረብ ገለልተኝነት በመባል የሚታወቀውና ሁሉም መረጃ በተመሳሳይ ፍጥነት እኩል እንዲቀርብ የሚፈቅደው ፖሊሲ እንዲያበቃ ድምፅ ሰጥቷል። አሁን የበይነ-መረብ አገልግሎት አቅራቢዎች የተገልጋዮቻቸውን እንቅስቃሴ መወሰን ይችላሉ። ተቺዎች ግን ይህ ውሳኔ በይነ-መረብን ለቅድመ ምርመራ የተጋለጠና ሁሉንም እኩል የማያገለግል ውድ ያደርገዋል ሲሉ ስጋታቸውን ይገልፃሉ።