የፕሪሚዬር ሊጉ የበዓል ማግስት ጨዋታዎች ግምት

አለን ፓርዲው የዌስትብሮም አሰጣኝነት መንበር ከተቆናጠጡ በኋላ ሶስት ነጥብ ለማግኘት እየታገሉ ይገኛሉ። በቦክሲንግ ደይ በማንሰራራት ላይ ካለው ኤቨርተን ጋር የሚጫወቱት ፓርዲው ውጤት ይቀናቸው ይሆን?

ይሄንንና ሌሎች የገና በዓል ማግስት ጨዋታዎችን ግምት ላውሮ ከታች እንደሚከተለው አስቀምጧል። እርስዎም የራስዎን ግምት በማስቀመጥ ከላውሮ ጋር መገዳደር ይችላሉ።

'ቦክሲንግ ደይ'

ማክሰኞ

ቶተንሃም ከሳውዝሃምፕተን

የፎቶው ባለመብት, BBC Sport

ሳውዝሃምፕተን ካለፉት 10 ጨዋታዎች አንድ ብቻ ነው ማሸነፍ የቻለው፤ ይህ ደግሞ ለአሰልጣኝ ሞሪሲዮ ፔሌግሪኖ መልካም ዜና እንዳልሆነ እሙን ነው።

ወደ ዌምብሌይ የሚያቀናው ሳውዝሃምፕተን ድል ይቀናዋል የሚል እምነት የለኝም።

በተቃራኒው ከበርንሌይ ጋር በነበረው ፍልሚያ ጥሩ ብቃት ላሳዩት ቶተንሃሞች ድል እንደሚሆን አምናለሁ።

የላውሮ ግምት፡ 2 - 0

ቦርንማውዝ ከዌስትሃም

ቦርንማውዝ ካለፉት ሰባት ጨዋታዎች አንዱንም ማሸነፍ አልቻለም፤ አሰልጣኝ ኤዲ ሃዊም ምንም ዓይነት ጫና ሳይደርስባቸው መቀጣላቸውም አስገርሞኛል።

ዌስትሃም ደግሞ ከቦርንማውዝ አንድ ከፍ ብለው 17ተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ዌስትሃም ባለፈው ጨዋታ በኒውካስትል በገዛ ሜዳቸው መሸነፋቸው ደግሞ ሌላው በጣም ያስደነቀኝ ጉዳይ ነው።

የላውሮ ግምት፡ 1 - 1

ቼልሲ ከብራይተን

የፎቶው ባለመብት, BBC Sport

ቅዳሜ ዕለት ዋትፎርድን ከመርታታቸው በፊት ብራይተኖች ሰባት ጨዋታዎችን ያለሶስት ነጥብ ተጉዘው ነበር።

አሁን ደግሞ ወደ ስታንፎርድ ብሪጅ በማቅናት ከቼልሲ ጋር ይፋለማሉ። ነገር ግን ውጤት ይቀናቸዋል ብዬ አላምንም።

ቼልሲ ከኤቨርተን ጋር በነበራቸው ጨዋታ የኤቨርተንን ተከላካይ ጥሰው ማለፍ ተስኗቸው ነበር። ብራይተን ጋር ተመሳሳይ ዕጣ ይሆናል ብዬ ግን አላስብም።

የላውሮ ግምት፡ 2 - 0

ሃደርስፊልድ ከስቶክ

ሃደርስፊልድ ካለፉት አራት ጨዋታዎች ሰባት ነጥቦችን በመሰብሰብ ማገገም ችሏል። ስቶክ ሲቲም በጣም አስፈላጊ ሶስት ነጥቦችን መሰብሰብ ችለዋል።

ለሃደርስፊልድም ሆነ ለስቶክ አንድ ነጥብ በጣም በቂ እንደሆነ እገምታለሁ።

የላውሮ ግምት፡ 1 - 1

ማንችስተር ዩናይትድ ከበርንሌይ

የፎቶው ባለመብት, BBC Sport

በርንሌይ ከቶተንሃም ጋር የነበረውን ጨዋታ እንደማያሸንፍ ገምቼ ነበር፤ ምክንያቱም ቶተንሃም ጠንክረው እንደሚቀርቡ አስቤ ነበርና ነው።

ከሌይስተር ጋር በነበራቸው ጨዋታ አቻ የወጡት ዩናይትዶች በዚህ ጨዋታ የተገኘውን ቀዳዳ ፈልገው ሶስት ነጥብ እንደሚያገኙ አምናለሁ።

የላውሮ ግምት፡ 2 - 0

ዋትፎርድ ከሌይስተር

ዋትፎርዶች አሁንም ወደ ተሻለ አቀም መምጣት አልቻሉም፤ ባለፈውም ጨዋታ በብራይተን ተሸንፈዋል። ካለፉት ስድስት ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ብቻ ነው ማግኘት የቻለው።

ቀበሮዎቹ (ሌይስተር) ደግሞ ታግለውም ቢሆን በስተመጨረሻ ከዩናይትድ ጋር ነጥብ መጋራት ችለዋል።

የላውሮ ግምት፡ 1 - 2

ዌስትብሮም ከኤቨርተን

አላርዳይስ የተካነበትን ነገር በኤቨርተን እያሳየን ይገኛል፤ ይህም ቡድኑን ለማሸነፍ ከባድ ያደርገዋል።

አለን ፓርዲው የዌስትብሮም አሰጣኝነት መንበር ከተቆናጠጡ በኋላ ሶስት ነጥብ ለማግኘት እየታገሉ ይገኛሉ። በቦክሲንግ ደይ በማንሰራራት ላይ ካለው ኤቨርተን ጋር የሚጫወቱት ፓርዲው ውጤት ይቀናቸዋል ብዬ እገምታለሁ።

የላውሮ ግምት፡ 1 - 0

ሊቨርፑል ከስዋንሲ

የፎቶው ባለመብት, BBC Sport

ሊቨርፑል ስዋንሲ ላይ ጎል እንደሚያስቆጥር አልጠራጠርም፤ ነገር ግን በቀጣይ ከሌይስተር ጋር ለሚኖራቸው ጨዋታ ሲሉ ዩርገን ክሎፕ የተወሰኑ ተጫዋቾቻቸውን እንዳያሳርፉ ስጋት አለኝ።

ክሎፕ ይህን የሚያደርጉ ከሆነ በራሳቸው ላይ ችግር እንደመጥራት ነው የማየው ምክንያቱም ስዋንሲ ቢያንስ አንድ ነጥብ ለማግኘት እንደሚታገሉ አልጠራጠርም።

የላውሮ ግምት፡ 3 - 0

'ቦክሲንግ ደይ' ረቡዕ ሲቀጥል

ኒውካስትል ከማንቸስተር ሲቲ

የፎቶው ባለመብት, BBC Sport

ቤኔቴዝ ለዚህ ጨዋታ ትልቅ ትኩረት በመስጠት ተጫዋቾቻቸው በደንብ ጠንክረው እንዲፋለሙ እንደሚያደርጉ እሙን ነው።

ቢሆንም ሲቲ አሁን ካለው አቋም አንፃር ኒውካስትል ይሳካለታል የሚል ግምት የለኝም።

የላውሮ ግምት፡ 0 - 2

ክሪስታል ፓላስ ከአርሴናል

የፎቶው ባለመብት, BBC Sport

ልክ እንደ አላርዳይስ ሁሉ ሮይ ሆጅሰንም ቡድናቸውን አጠንክረው ለተጋጣሚ የሚከብድ አድረገውታል።

አርሴናል በበኩሉ በጣም ወጥ አቋም ያጣ ቡድን ሆኗል። እኔ ጨዋታው በአቻ ውጤታ ይጠናቀቃል ባይ ነኝ።

የላውሮ ግምት፡ 1 -1