የዶክተር መረራ ጉዲና ክስ ተቋረጠ

ዶ/ር መረራ ጉዲና Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ዶ/ር መረራ ጉዲና

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራር የሆኑትና ታዋቂው ፖለቲከኛ የዶ/ር መረራ ጉዲና ክስ ተቋረጠ። ዶ/ር መረራ በ2016 በብራስልስ የአውሮፓ የፓርላማ አባላትን ስብሰባ ተካፍለው ሲመለሱ ነበር በቁጥጥር ስር የዋሉት።

ዛሬ የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ሕግ በሰጠው መግለጫ የፍርድ ሂደታቸው በመታየት ላይ የሚገኙ የ528 ተጠርጣሪዎች ክስ መቋረጡን አስታውቋል።

ከሚፈቱት እስረኞች መካከል 115 በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ሥር የሚገኙ ሲሆን በክልል ደረጃ የሚገኙትን ደግሞ ክልሉ በሚወስነው መሠረት ተግባራዊ ይሆናል። እሰካሁን ድረስም የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ብቻ 413 የሚሆኑ የእስረኞችን ስም ዝርዝር አቅርቦ ክሳቸውን ለማቋረጥ ወስኗል ብለዋል።

በመግለጫው ወቅት ክሳቸው ተቋርጦ ከሚፈቱ እሰረኞች መካከል የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች የሚገኙበት አንደሆነ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው፤ ''በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ስም ዝርዝራቸው ይፋ ሲደረግ የምንመለከተው ይሆናል'' ብለው ነበር። አቶ ጌታቸው በኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኛ የለም በማለት አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

እንደ አቶ ጌታቸው አምባዬ መግለጫ ከሆነ እስረኞቹ በሁለት ቀናት ውስጥ ይፈታሉ።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ