ኬንያ ሳተላይት ልታመጥቅ ነው

Kenyan flag

በናይሮቢ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ኢንጂነሮች ከአንድ የጃፓን የምርምር ተቋም ባገኙት ድጋፍ ከአንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ ሳተላይት ገንብተዋል።

ይህ ሳተላይት የግብርና ሥራን ለመከታተልና የኬንያን የባህር ጠረፍ ለመቆጣጠር ተግባር ጥቅም ላይ ይውላል ተብሏል።

ጃፓን ለሳተላይቱ ግንባታ የሚያስፈልገውን ወጪ የሰፈነች ቢሆንም ግንባታውን ያከናወኑት ኬንያዊያን ባለሙያዎች ናቸው።

ሳተላይቱ በመጪው መጋቢት ወደ ዓለም አቀፉ የህዋ ጣቢያ የሚመጥቅ ሲሆን ከአንድ ወር በኋላ ደግሞ ሥራውን እንዲጀምር ይደረጋል።

ይህም በአፍሪካ ሳተላይት ወደ ህዋ ካመጠቁ ስድስት ሃገራት መካከል ኬንያን ያሰልፋታል።

ይህን ሳተላይት የገነባው የናይሮቢ ዩኒቨርሲቲቀወ ቡድን፤ በማደግ ላይ ባሉ ሃገራት የሚገኙ የትምህርት ተቋማት የራሳቸውን ሳተላይት እንዲገነቡ ለማገዝ በተባበሩት መንግሥታትና በጃፓን መንግሥት ከተጀመረው ፕሮጀክት ተጠቃሚ ለመሆን የመጀመሪያው ነው።