አደራ የበላው ፖስተኛ ታሰረ

የፖሰታ ሳጥን Image copyright Getty Images

በጣልያን ቪቼንዛ አንድ ፖስተኛ ለዓመታት ማድረስ የነበረበትን ፖስታዎች የመኪና ማቆሚያ ውስጥ አከማችቶ በመገኘቱ ለእስር ተዳርጓል።

የ56 ዓመቱ ፖስተኛ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2010 ጀምሮ ያላደረሳቸው ፖስታዎች በአጠቃላይ 570 ኪሎ ግራም መዝነዋል።

እነዚህ ፖስታዎች በ40 ፕላስቲክ ሳጥኖች ታጭቀው ነበር የተቀመጡት። ፖስታዎቹ የደብዳቤዎች፣ የክፍያ ደረሰኞችና የባንክ የሂሳብ ዝውውር ደረሰኞች ነበሩ።

የጣልያን ፖሊስ እንዳስታወቀው ይህ በአገሪቱ ለሚመለከታቸው ሰዎች መድረስ ሲኖርበት ያልደረሰ ከፍተኛው የፖስታዎች ክምችት ነው።

የቪቼንዛ ከተማ ፖስታ አገልግሎት ጊዜው ቢያልፍም ፖስታዎቹን መድረስ ላለባቸው ሰዎች እንደሚያደርስ ገልጿል።

በሌላ በኩል ደግሞ ፖስተኛው ላይ ክስ ተመስርቶ ተጠያቂ እንደሚሆን አስተውቋል።

ተያያዥ ርዕሶች