ህንዳዊቷ ጥሎሽ ባለመክፈሏ ኩላሊቴን ሰርቆኛል ስትል ባሏን ወነጀለች

Blue-gloved hands of medical latex exchange a surgical scissors, while a third hand can be seen holding a clamp and cotton swab Image copyright Getty Images

ጥሎሽ አልከፈልሽም በማለት የህንዳዊቷን ኩላሊት የሰረቁት ባለቤቷና የባለቤቷ ወንድምን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።

የሀገሪቱ ሚዲያ እንደዘገቡትም በምዕራብ ቤንጋል ነዋሪነቷን ያደረገችው ይህች ሴት ከሁለት ዓመታት በፊት በከፍተኛ ሆድ ህመም ትሰቃይ ነበርም ይህንንም ተከትሎ ባለቤቷ የትርፍ አንጀት ቀዶ ጥገና ለማድረግም ማመቻቸቱ ተዘግቧል።

በአውሮፓውያኑ ባለፈው ዓመት መጨረሻም ላይ በተደረገላት ሁለት የህክምና ምርመራዎች አንደኛዋ ኩላሊቷ እንደሌለም ማረጋገጥ ተችሏል።

ባለቤቷም ለዓመታት ያህልም "ጥሎሽ" ልትሰጠው እንደሚገባም ሲጨቀጭቃትም ነበር።

በህንድ ባህል የጥሎሽ ክፍያ ከሴት ሙሽሪት ቤተሰብ ለወንድ ቤተሰብ የሚሰጥ ሲሆን ከተከለከለም ከአምስት አስርት ዓመታት በላይን አስቆጥሯል።

ይህ ጥቃት የደረሰባት ሪታ ሳርካር ለህንድ ሚዲያ እንደተናገረችውም ለዓመታትም ያህል በጥሎሽ ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የቤት ውስጥ ጥቃትም ባሏ ያደርስባትም እንደነበር ገልፃለች።

"ባለቤቴ ኮልካታ በሚገኝ አንድ የግል ህክምና ወሰደኝ፤ እሱም ሆነ በሆስፒታሉ የሚሰሩ ሰራተኞች የትርፍ አንጀቴን በቀዶ ህክምና ባስወጣው እንደሚሻለኝ ነገሩኝ" በማለት ለሂንዱስታን ታይምስ ተናግራለች።

"ባለቤቴም ኮልኮታ ላይ ስለተፈፀመው ቀዶ ጥገና ለማንም ትንፍሽ እንዳልልም አስጠነቀቀኝ" ትላለች።

ከወራትም በኋላ ህመም ሲሰማት ቤተሰቦቿ ዶክተር ጋር ወሰዷት። በተደረገው ምርመራ የቀኝ ጎን ኩላሊቷ እንደጠፋም ታወቀ። ይህ የተረጋገጠውም በሁለተኛው ምርመራ ነው።

"ለምን ስለ ቀዶ ህክምናው ለማንም እንዳልናገር ያደረገኝ ምክንያቱን አሁን ተረዳሁት" በማለት ለሂንዱስታን ታይምስ ተናግራለች።

"ቤተሰቦቼ ጥሎሽ መክፈል ስላልቻሉ ባሌ ኩላሊቴን ሸጠው" ብላለች።

ተያያዥ ርዕሶች