አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው ኦብነግ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እየተደራደረ ነው

የኦብነግና የኢትዮጵያ መንግሥት ድርድር

የኢትዮጵያ መንግሥት ከኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ ኣውጪ ግንባር (ኦብነግ) አንጃ ጋር እየተደራደረ መሆኑን አንድ የመንግስት የውስጥ አዋቂ ለቢቢሲ አረጋግጧል።

የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ከአምስት ዓመት በፊት በሽብርተኝነት ከፈረጃቸው አምስት ድርጅቶች መካከል የሆነው ኦብነግ የኦጋዴን ግዛትን ነፃ ለማውጣት በነፍጥ የሚታገል ድርጅት ነው።

በአመራሩ ውስጡ የተፈጠረው መከፋፈል ተከትሎ አንዱ አንጃ በናይሮቢ ከመንግስት ጋር ለመደራረደር የሚያስችለውን ቅድመ ሁኔታ ላይ መስማማቱን ለማወቅ ተችሏል።

ድርድሩ በይፋ እንዳልተጀመረ የሚናገሩት እኚሁ የውስጥ አዋቂ በናይሮቢ ውስጥ ትናንት እሑድ የተጀመረው ንግግር የድርጅቱ አንጃ አመራር ወታደሮቹን ይዞ ለመግባትና በመንግስት ምህረት ተደርጎላቸው መልሰው የሚቋቋሙበት ሁኔታ ላይ ይደራደራሉ።

በድርድሩ የኢትዮጵያን መንግስት ወክሎ ከሚነጋገረው ቡድን ውስጥ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ኢሌ እና ኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር አለምሰገድ እንደሚገኙበት ምንጫችን ገልፀውልናል።

ከዚህ ቀደም ከድርጅቱ ተነጥሎ የወጣው አመራር ጋር ድረድር ተካሂዶ የተወሰነ አመራር ከእነ ወታደራዊ ኃይሉ ትጥቅ ፈትቶ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋርም እርቅ አውርዷል።

ከጥቂት ወራት በፊት የሶማልያ መንግስት አንድ ከፍተኛ የኦብነግ መሪ ለኢትዯጵያ መንግስት ተላልፎ እንዲሰጥ ማድረጉ ይታወሳል።

ተያያዥ ርዕሶች