አልሞት ባይ ተጋዳዩ ጃኮብ ዙማ

አልሞት ባይ ተጋዳዩ ጃኮብ ዙማ

የነጩ አገዛዝ አፓርታይድ ከተገረሰሰበት ከአውሮፓውያኑ 1994 ጀምሮ ደቡብ አፍሪካ እንደ ጃኮብ ዙማ አነጋጋሪና አስገራሚ ፕሬዚዳንት አይታ አታውቅም። ወደ ስልጣን የመጡበት ሂደት የህዝብ ፕሬዚዳንት ቢያስብላቸውም ተደጋጋሚ የሙስና ክሶች እንዲሁም ከሥልጣን ይውረዱ ጥያቄዎች ጥላሸትን አጥሎባቸዋል።