ጋቦን፡ በሆስፒታል ክፍያ መያዣነት የቆየችው ህፃን ነፃ ሆነች

Five-month old Angel has been reunited with her mother

ጋቦናዊት እናት ለአንድ የግል ክሊኒክ ክፍያ ባለመፈፀሟ ምክንያት ልጇን በተያዥነት ለወራት ከያዘባት በኋላ ህፃኗ የለቀቀ ሲሆን እናቷም እፎይታ እንዳገኘች ገልፃለች።

የህፃኗ እናት ለቢቢሲ እንደገለፀችውም በባለፉት አምስት ወራት ከልጇም ጋር በመለያየቷ ጡቷ እንደደረቀ ነው።

ይህ ጉዳይ ሀገሪቷን በድንጋጤ ያንቀጠቀጠ ሲሆን በምላሹም ማህበረሰቡ ድጋፍን ችሯታል።

በቤተሰቡም ስም ዘመቻ ከተከፈተ በኋላ ነው ወደ መቶ ሺ ብር የነበረው የሆስፒታል ክፍያ የተከፈለው።

ለዚህ ክፍያ አስተዋፅኦ ካደረጉት መካከል አንዱ ፕሬዚዳንቱ አሊ ቦንጎ ናቸው።

የክሊኒኩ ዳይሬክተር ሰኞ ዕለት ህፃናትን በመጥለፍ ክስ እስር ቤት የገቡ ሲሆን ከአንድ ቀንም በኋላ ክሱ ውድቅ እንደተደረገ የቢቢሲ አፍሪክ ቻርለስ ሰቴፋን ከመዲናዋ ሊበርቪል ዘግቧል።

ህፃኗ ኤንጅልም በመጨረሻ በዚህ ሳምንት በመዲናዋ ሰሜን የሚገኘውን ክሊኒክንም ለቃ መሄድ እንደቻለችም ተገልጿል።

የህፃኗ እናት ሶኒያ ኦኮሜ ለቢቢሲ እንደገፀችው ምንም እንኳን እፎይታን ብታገኝም ከምሬት በኋላ የመጣ ነው ብለዋል " ልጄን መልሼ በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ። በጣም የሚያሳዝነኝ ጉዳይ ግን ልጄን አሁን ማጥባት አልችልም ምክንያቱም ጡቴ ደርቋል" ብላለች።

ከዚህም በተጨማሪ ህፃኗ ክትባት አልተሰጣትም በሚልም አማራለች።

የጋቦን ሚዲያ ታይም እንደዘገበው ይህ ክፍያ ህፃኗ ያለጊዜዋ በመወለዷ በህፃናት ማቆያ ለ35 ቀናት የቆየችበት ነው።

ተያያዥ ርዕሶች