ሲሪል ራማፎሳ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሆኑ

ሲሪል ራማፎሳ

በኤኤንሲ የበላይነት በሚመራው ፓርላመንትም ብቸኛ እጩ አድርጎ ያቀረባቸው ሲሆን ዜናው ሲሰማም የፓርላመንት አባላቶቹ በዘፈን ደስታቸውን ገልፀዋል።

የ65 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋው ራማፎሳም በመጀመሪያው ቀን የተናገሩት በዙማ አስተዳደር ወቅት የተንሰራፋውን ሙስና እንደሚያጠፉ ነው።

ፓርቲያቸው ኤኤንሲ ዙማን ከሥልጣን እንዲወርዱ ካለበለዚያ እንደሚያወርዷቸው ማስጠንቀቃቸው የሚታወስ ነው።

በብዙ የሙስና ውንጀላዎች ተዘፍቀዋል ቢባሉም ዙማ ምንም ስህተት እንዳልሰሩ ይናገራሉ።

አንደኛው የቀረበባቸውም ክስ ከባለፀጋዎቹ የጉፕታ ቤተሰብ ጋር አሻጥር በመስራት በሀገሪቱ ፖሊሲ ተፅእኖ እንዲፈጥሩ ፈቅደውላቸዋል የሚል ነው።

ከሶስቱ የጉፕታ ወንድማማቾች በአንደኛው አጄይ ጉፕታ ላይ የእስር እዝም ትናንት እንደወጣም ባለስልጣናት ተናግረዋል።

ሮብ ዕለትም ቤታቸው በፖሊስ ተከቦ እንደነበር ተዘግቧል። ቤተሰቡ ከምንም አይነት የሙስና ጉዳዮች ነፃ ነን በማለት ክደዋል።

የመጀመሪያ ቀን ንግግራቸው በሙስና ላይ ያተኮረው ራማፎሳ አርብ እለት ለህዝቡ ንግግር ያደርጋሉ ተብለው ይጠበቃሉ።

ይህ የዘገየበት ምክንያትም ዙማ ከስልጣን አልወርድም እምቢተኝነታቸው ስለፀኑ ነው።

አንደኛው ተቃዋሚ ፓርቲ ለኢኮኖሚ ነፃነት ታጋዮች (ኢኮኖሚክ ፍሪደም ፋይተር) ፓርላማ የነበረውን ክርክር ረግጠው ወጥተዋል።

ኤኤንሲ አዲስ ፕሬዚዳንት ከመምረጥ አዲስ ምርጫ ያስፈልጋልም ብለዋል።

በመጨረሻም ህልማቸው ተሳካ

ከአፓርታይድ መገርሰስና ስልጣኑን ኤኤንሲ ከተቆጣጠረበት ጀምሮ ራማፎሳ ፕሬዚዳንት ለመሆን ይፈልጉ ነበር።

ኔልሰን ማንዴላ የሳቸው ስልጣንን ተተኪ አድርገውም ስላልመረጧቸው የፖለቲካውን አለም ትትው ወደ ቢዝነሱ ተቀላቀሉ።

በመጨረሻም ራማፎሳ ህልማቸውን አሳኩ።

ቅድሚያ የሚሰጡትም የተሟሟተውን የደቡብ አፍሪካን ኢኮኖሚ ማነቃቃት ነው። ቀላል እንደመይሆንም እየተነገረ ሲሆን ምክንያቱም የስራ አጥነት ቂጥር 30% ሲሆን ለወጣቱም 40% ነው።

ራማፎሳ ስልጣን ከያዙ በኋላ በደቡብ አፍሪካ አዲስ ተስፋ እያቆጠቆጠ ይመስላል። ገበያውም በዙማ መልቀቅ የተደሰተ ይመስላል።

የደቡብ አፍሪካ የገንዘብ ኖታ በሶስት አመት ውስጥ ከነበረው ጠንካራ ቦታም ተመልሷል። አንዳንዶች ግን አሁን ቢሆን ይናፍቋቸዋል ምክንያቱም ይላል የቢቢሲው ሚልተን ኢንኮሲ ለከፍተኛ ትምህርት ክፍያን ማስወገዳቸው አንዱ ውጤታቸው ስለሆነ ነው።

በዘረኛው የነጩ አፓርታይድ አገዛዝ ወቅት በኤኤንሲ የወታደራዊ ክንፍ የነበሩት ዙማ በተለያዩ የስልጣን እርከኖችም በማለፍ ፕሬዚዳንት ሆነዋል።