ኢትዮጵያ፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ ለ6 ወራት እንሚቆይ ተገለጸ

መከላከያ ሚኒስትር ሲራጅ ፈርጌሳ
የምስሉ መግለጫ,

የሃገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች በኣንድ ኮማንድ ስር ይታዘዛሉ ተብለዋል

የኢትዮጵያ የሚንስትሮች ምክር ቤት ከዓርብ የካቲት 9 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለ6 ወራት ንደሚቆይ የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ አስታውቁ።

በሃገሪቷ የተከሰተውን ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ለመቀልበስ የሚንስትሮች ምክር ቤት ከትናንት ዓርብ ጀምሮ የሚተገበር የአስቸኳይ ጊዜ ማወጁን ይታወሳል።

ኣቶ ሲራጅ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፡ ይህ የስድስት ወራት ገደብ ሊራዘምን እንምችልም ጠቅሰዋል።

እሳቸው እደገለጹት፡ የሃገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች የማራጋጋቱ ስራ ለመወጣት በአንድ ኮምንድ ፓስት ስር እንደሚሆኑና፡ በጠቅላይ ሚኒስተር እንደሚታዘዙ ይሆናለ።

ከዚ በተያያዘ፡ ሃገሪቱን ሰለምና መረጋጋት ለማደፍረስ በሚጥሩ ያላቸውን 'የውስጥና የውጭ ሃይሎች ህጋዊ እርምጃ' እንደሚወስዱ የብሔራዊ የጸጥታዉ ምክርቤት ዛሬ ባወጣዉ መግለጫ ገልጸዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አተገባበር በሚመለከት ዝርዝር መረጃ ለጸጥታ ሃይሎች እንተሰጣቸው መከላከያ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የምስሉ መግለጫ,

ኢትዮጵያ ኣጋትሟት ያለው ኣለመረጋጋት ለጠቅላይ ሚኒስትሪ ከስልጣን መወረድ ዋነኛ ምክንያት ሆኗል

ኣገሪቱ ተከስቶ ባለው ቀውስ ምክንያት ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በገዛ ፍቃዳቸው ከስልጣን ለመውረድ ጥያቄ ማቅረባቸውና፡ የኢህኣዴግ ስራ ኣስፈጻሚ ጣያቄአቸው እንደ ተቀበለና፡ የድርጅቱ ምክርቤት የመጨረሻ ውሳኔ ብቅርቡ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

አዋጁ የዜጎች ዴሞክራሲያዊ እና ፖለቲካዊ መብቶች ላይ ገደብ ይጥላል የሚል ስጋት ፍጥሯል።

በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 93 መሰረት የሚንስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ ይችላል።

የሚንስትሮች ምክር ቤት ዓርብ ከሰዓት መግለጫ እንደሚሰጥ ተገልጾ ሲጠበቅ ቢቆይም፤ ከስድስት ሰዓታት ቆይታ በኋላ ለጋዜጠኞች የተባለው መግለጫ ሳይሰጥ ቀርቶ አንዲበተኑ ተደርጎ ነበር።

ምሽት ሁለት ሰዓት ላይ የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ያለ ተጨማሪ ማብራሪያ አዋጁ እንደታወጀ ዘግበዋል።

ከአንድ ዓመት ቀደም ብሎ ለዘጠኝ ወራት የዘለቀ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመላው ሃገሪቱ ተግባራዊ እንደነበር ይታወሳል።