ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ እና ንግስት ይርጋ ክሳቸው ተቋረጠ

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ እና ንግስት ይርጋ
የምስሉ መግለጫ,

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ እና ንግስት ይርጋ

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ እና ንግስት ይርጋ ክሳቸው ተቋረጠ።

ከወልቃይት አማራ የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ ከነበሩት ሰዎች መካከል ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ እና ንግስት ይርጋ ጨምሮ ከአንድ መቶ በላይ እስረኞቸን ክሳቸው እንዲቋረጥ መደረጉ ተዘገበ።

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ እና ንግስት ይርጋ በተጨማሪ ተሻገር ወልደ ሚካኤል ጌታቸው አደመና አታላይ ዛፌ ይገኙበታል።

ክሳቸው ከተቋረ ውስጥ ሃምሳ ስድስት የግንቦት ሰባት እንዲሁም አርባ አንድ ከኦነግ ጋር በተያያዘ የተከሰሱ ነበሩ።

በሌላ በኩል ደግሞ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞና አሳምነው ጽጌን ጨምሮ ሌሎች ግለሰቦች በይቅርታ እንዲፈቱ ጉዳያቸው እየታየ ነው።