የብራዚል እስር ቤት በእስረኞች ቁጥጥር ሥር ይገኛል

የብረዚል ጦር Image copyright Getty Images

በብራዚል መዲና ሪዮ ዲ ጄኔሮ የሚገኝ እስር ቤት በእስረኞች ቁጥጥር ስር ውሏል። እስረኞቹ የእስር ቤቱን ሰራተኞችም አግተዋል።

የታጠቁ አድማ በታኝ ፖሊሶች እስር ቤቱን ከበውት የሚገኙ ሲሆን ታሳሪዎቹ በከተማዋ አደገኛ ከሚባሉ የማፊያ ቡድኖች መካከል የአንዱ አባላት ናቸው።

አመጹን ከቀሰቀሱት እስረኞች መካከል ሶስቱ በጥይት ተመትተዋል።

አመጹ የተቀሰቀሰው የብራዚል ፕሬዚዳንት ሚኬል ቴምር ሪዮ ዲ ጄኔሮ በብራዚል የጦር ኃይል ቁጥጥር ሥር እንድትሆን ውሳኔ ካስተላለፉ በኋላ ነው።

የእስር ቤቱ ሃላፊዎች እስረኞቹ አመጹን የቀሰቀሱት የፕሬዚዳንቱን ውሳኔ በመቃወም ሳይሆን አይቀርም ብለዋል።

ተያያዥ ርዕሶች