ቢቢሲ አዲስ አገልግሎቶችን በኢግቦ እና ዩሮባ ቋንቋዎች ጀመረ

የቢቢሲ ኢግቦ እና ዮሩባ አዲስ አገልግሎቶች ዛሬ ጀመሩ። ከሶስቱ አዳዲስ አገልግሎቶች መካከል ዛሬ የጀመሩት የሁለት ቋንቋ አገልግሎቶች በናይጄሪያ እና ምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ ላሉ አድማጭ ተመልካቾች ተደራሽ ይሆናሉ።

ቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ እ.አ.አ. ከ1940 በኋላ እያካሄደ ያለው ከፍተኛ የማስፋፊያ አካል ናቸው።

የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት እ.አ.አ. በ2015 ለወርልድ ሰርቪስ ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

የኢግቦ አገልግሎት በአብዛኛው በምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ናይጄሪያ እና በውጪ ባሉ የማህብረሰቡ ቋንቋ ተናጋሪዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን፤ የዮሩባ አገልግሎት ደግሞ ደቡብ ምዕራብ ናይጄሪያ፣ ቤኒን እና ቶጎ ባሉ አድማጭ ተመልካቾች ላይ ተኩረት አድርጎ ይሠራል።

አገልግሎቶቹ፤ ነፃና ገለልተኛ የሆነ ዜና ብቻ ሳይሆን ስፖርት፣ መዝናኛ፣ ንግድ፣ ጤና፣ ትምህርት እና ሴቶች ላይ ያተኮሩ ዘገባዎችን ያካትታል።