በቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ የነበሩ ኤርትራውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ

የኤርትራ ባንዲራ Image copyright Getty Images

በቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ የነበሩ በርካታ ኤርትራውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ። በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል የ13 ዓመት ታዳጊ ይገኝበታል።

የታሳሪዎቹ ዘመዶች እንዳሉት ወጣቶቹ እስር ቤት ሳሉ የሞቱትን የ90 ዓመት አዛውንት ሐጂ ሙሳ መሐመድ ኑርን ለመቅበር እየሄዱ ነበር።

ሐጂ ሙሳ በቁጥጥር ስር የዋሉት ባለፈው ዓመት እርሳቸው የቦርድ አባል በሆኑበት ትምህርት ቤት ላይ ተፈፃሚ የሚሆን የመንግሥትን ደንብ በመቃወም ነበር።

ባለፈው ህዳር የእርሳቸውን መታሰር ተከትሎ በአስመራ ጎዳናዎች ላይ መጠነኛ ተቃውሞ የነበረ ቢሆንም ወዲያው ፖሊስ ሰልፈኞቹን በትኗቸዋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች ቤተሰቦች ስለ ደህንነታቸው እንደሚሰጉ ተናግረዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የኤርትራ መንግሥት ምንም አይነት አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አይደለም።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ