የፕሪሚየር ሊጉ የሳምንቱ ምርጥ አስራአንድ

ዩናይትድ፣ ኒውካስል፣ ኤቨርተን፣ አርሴናል፣ ቼልሲ፣ ሌይስተር፣ በርንሌይና ቶተንሃም ድል ቀንቷቸዋል፤ ሃደርስፊልድን የገጠመው ስዋንሲ ደግሞ 79 ደቂቃዎችን በ10 ተጫዋቾች ተፋልሞ አንድ ነጥብ ይዞ መውጣት ችሏል።

እስቲ አስገራሚ ፍልሚያዎችን ካየንበት ያለፈው ሳምንት የሊጉ መርሃ ግብር ነጥረው የወጡ ምርጥ አስራአንዶችን እንመልከት ይለናል የኳስ ተንታኙ ጋርዝ ክሩክስ።

ግብ ጠባቂ - ፒተር ቼክ

Image copyright BBC Sport

ከዋትፎርድ ጋር በነበረው ጨዋታ ፍፁም ቅጣት ምት ማዳን የቻለው ቼክ ምንም ጎል ሳይቆጠርበት ያሳለፈው 200ተኛ ድሉን አጣጥሟል። ይህን ስኬት በማሳካትም3 በፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያውና ብቸኛው ግብ ጠባቂ መሆን ችሏል።

ተከላካይ መስመር

Image copyright BBC Sport

የሳምንቱ ምርጥ ተከላካዮች አሽሊ ያንግ እና ስሞሊንግ ከዩናይት እንዲሁም ማቲው ሎውተን ከበርንሌይ ሆነዋል።

አሽሊ ያንግ ለሩስያው የዓለም ዋንጫ ከእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ጋር ሊጓዝ ይችላል ብዬ ሳስብ ሁለም ይገርመኛል። ነገር ግን ተጫዋቹ ከዕለት ዕለት የሚያሳየው ብቃት መጨመር ደግሞ ይበልጡኑ ያስገርመኛል።

ከሊቨርፑል ጋር በመነበረው ጨዋታ ያንግ በጣም ድንቅ ነበር።

ሌላኛው 'ቀይ ሰይጣን' ክሪስ ስሞሊንግም ከሊቨርፑል ጋር በነበረው ፍልሚያ ድንቅ ብቃት ማሳየት ችሏል። እኔ ስሞሊንግ ባይኖር ዩናይትድ ሊሸነፍ ይችል ነበር ባይ ነኝ።

በርንሌዩ ማቲው ሎውተን ወደ ዌስትሃም አጋማሽ 18 ንፁህ ኳሶችን መጣል የቻለ ሲሆን 13 ስኬታም ነበሩ። ቡድኑ በርንሌይ በዌስትሃም ሜዳ 3 ነጥብ ይዞ ለመውጣቱ ትልቁን ድርሻ እንደተጫወተም የማይካድ ነው።

አማካይ

Image copyright BBC Sport

የዚህ ሳምንት ምርጥ አማካዮች የኒውካስሉ ኬኔዲ፣ የቼልሲው ዊሊያን፣ የአርሴናሉ ሚኪ እና የሌይስተሩ ማህሬዝ ናቸው።

ኒውካስል ከሳውዝሃምፕተን ጋር በነበረው ጨዋታ አሪፍ ሆኖ ይሁን ወይ ሳውዝሃምፕተን ደካማ ሆኖ ሶስት ነጥብ ይዞ መውጣት የቻለው? አሁን መልስ አላገኘሁም። ነገር ግን የኬኔዲን ድንቅ ብቃት መሸሸግ የማይቻል ነበር።

የቼልሲው ዊሊያን ብቃት ምርጥ መሆን ለቼልሲ ጠቃሚነቱ እየጎላ መጥቷል። እንጂ ቼልሲ አሁን ባላቸው አቋም ሙሉ በሙሉ ሶስት ይዘው ይወጣሉ ብዬ ለመተማመን እያዳገተኝ ነው። ካፓላስ ጋር በነበረው ፍልሚያ ያስተዋልኩት ይህን ነው።

አርመናዊው ሄንሪክ ሚኪታርያን ከዋትፎርድ ጋር በነበረው ፍልሚያ የአርሴናል ደጋፊዎች ፊት ላይ ደስታ መዝራት ችሏል።

ሌላኛው የሳምንቱ ምርጥ አማካይ ሪያድ ማህሬዝ ወደ ቀደመ አቋኡ የተመለሰ ይመስላል። የሚያቀብላቸው ኳሶች ኢላማቸውን የጠበቁና ስኬታማም ነበሩ።

አጥቂዎች

Image copyright BBC Sport

ድንቅ ብቃት መሳየት የቻለው ራሽፎርድ፣ ጄሚ ቫርዲ እና አሽሊ ባርንስ የዚህን ሳምንት ምርጥ አስራአንድ ያሟሉ አጥቂዎች ናቸው።

የዩናይትዱ ታዳጊ አጥቂ ራሽፎርድ ከጨዋታው መጠናቀቅ በፊት ሞሪንሆ ባይቀይረው ኖሮ ሃት-ትሪክ ሊሰራ ይችል ነበር። ለኔ ልጁ ሙሉ ተጫዋች የሆነ ሲሆን ሞሪንሆም እንደ ትልቅ ሰው ሊያዩት ይገባል ባይ ነኝ።

እርግጥ ነው ከማህሬዝ የተሻገረችው ኳስ እጅግ ድንቅ ነበረች የጄሚ ቫርዲ አጨራረስ ግን በጣም ልዩ ነበር። የቫርዲ እና ማህሬዝ ጥምረት ሌይስተርን የደረጃ ሰንጠረዡ አስተማማኝ ሥፍራ ላይም አስቀምጧቸዋል።

የዌስትሃምን ድክመት በእጅጉ የተረዳው የበርንሌዩ ሾን ዳይስ የአሽሊ ባርንስን ብቃት መረዳት ችሏል ባይ ነኝ። ባርንስ ባለፉት ሶስት ተከታታይ ጨዋታዎች ጎል ማስቆጠር የቻለበት ድንቅ ብቃት ላይ ይገኛል።

ተያያዥ ርዕሶች