ሃሰተኛ መድሃኒቶችን ለገበያ ያቀረቡ ተፈረደባቸው

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ባሳለፍነው ዓመት በአይቮሪ ኮስት 50 ቶን የሚመዝን ሃሰተኛ መድሃኒት እንዲወገድ ተደርጎ ነበር

የቤኒን ፍርድ ቤት ሃሰተኛ መድሃኒቶችን ሸጠዋል ያላቸውን የህክምና እቃዎች አምራች ኩባንያ ከፍተኛ አመራሮችን አሰረ።

በምዕራብ አፍሪካ ሃሰተኛ መድሃኒቶችን ለመቆጣጠር ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተካሄደ ይገኛል።

መድሃኒቶች ሃሰተኛ ናቸው የሚባሉት ይዘዋል የተባለው ንጥረ-ነገር ሳይኖራቸው ወይም አነስተኛ ሆኖ ሲገኘ ነው።

አብዛኛውን ጊዜ ሃሰተኛ መድሃኒቶች ትክክለኛ ከሚባሉት መድሃኒቶች ጋር ተመሳሳይ ገጽታ እንዲኖራቸው ተደርጎ ይሰራል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ሰባቱ ግለሰቦች በቤኒን እና በቀጠናው ለሚገኙ ሀገራት ከህመም ማስታገሻዎች እሰከ ጸረ-ወባ መድሃኒቶች ድረስ በጅምላ ያከፋፈሉ ነበር።

ግለሰቦቹ የአራት ዓመት እስራት እና የ$190,000 ቅጣት ተላልፎባቸዋል።