የእየሱስ ትክክለኛ ገፅታ በታሪክ አጥኚዎች አይን

Ilustración de un rostro que podría ser el de Jesús.

የፎቶው ባለመብት, Cícero Moraes/BBC Brasil

ከብዙ ክፍለ-ዘመናት በኋላም በጥበብም ሆነ በእምነት አውሮፓን ማዕከል ያደረገው ምልከታ እየሱስ ላይ ያለንን ምስል ቀርፆታል።

ይህም ቆዳው ነጭ፣ ፂም ያለው፣ ቡናማ ረዥም ፀጉርና ሰማያዊ አይን ያለው ነው።

በዓለም ላይ በሚገኙ ቢሊዮን ክርስቲያኖችም ይህ ምስል የሚታወቅ ሲሆን ከእውነታው ጋር የሚገናኝ አይደለም።

በዘርፉ ላይ ያሉ የታሪክ ምሁራን እንደሚሉት እየሱስ ጥቁር፣ ፀጉሩ አጠር ያለና በዚያን ጊዜ የነበሩ ይሁዳውያንንም ሊመስል እንደሚችል ነው።

የእየሱስ መልክ ምን እንደሚመስል የኢየሱስን የህይወት ታሪክ በሚተርከው አዲስ ወንጌል ምን እንደሚመስል አለመጠቀሱ ሰዎች ብዙ መላምቶችን እንዲሰጡ አድርጓቸዋል።

መፅሀፍ ቅዱስ ኢየሱስ መልኩም ይሁን በአጠቃላይ የውጭ አካሉ ምን እንደሚመስል ፍንጭ አይሰጥም።

ረዥም ይሁን አጭር፤ ውብ ይሁን ጠንካራ ምንም አይልም።

ተቀራራቢ እድሜ የሚሰጥ ሲሆን ይህም 30 ዓመት ነው" በማለት "ኢየሱስ ምን ይመስል ነበር?" የሚለው መፅሀፍ ደራሲና በለንደን በሚገኘው ኪንግስ ኮሌጅ የስነ-መለኮትና የሀይማኖት ጥናት ኒውዚላንዳውው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ጆአን ቴይለር ይናገራሉ።

"የመረጃ እጥረት በጣም ጎልቶ ይታያል። የእየሱስ ተከታይ የነበሩት የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ስለዚህ መረጃ የተጨነቁ አይመስሉም። ለነሱ ከውጫዊ አካሉ በላይ በመልዕክቶቹ ላይ አትኩሮት ሰጥተዋል። " የሚሉት ደግሞ የታሪክ ምሁሩ፣ በብራዚል በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰርና "ታሪካዊው ኢየሱስ፡ አጭር መግቢያ" ደራሲ አንድሬ ሊዮናርድ ናቸው።

የአንደኛው ክፍለ-ዘመን የራስ ቅል አፅም

በአውሮፓውያኑ 2001 ቢቢሲ ያዘጋጀው ጥናታዊ ፊልም ላይ እንደተዘገበው ሪቻርድ ኒቭ የተባለ ሳይንቲስት ሳይንሳዊ እውቀቱን ተጠቅሞ የእየሱስ መልክ ምን እንደሚመስል ለማወቅ ሞክሮ ነበር።

በዚህም መሰረት በሶስተኛው ክፍለ-ዘመን የጥንት አይሁዳውያን የራስ ቅሎች አፅምን ሞዴል በመጠቀም ኢየሱስ የሚመስለውን ቅርፅ ሰርተዋል።

የይሁዳውያን አፅመ-ቅሬት እንደሚያሳየው የአማካኝ ቁመታቸው 1.6 ሜትር እንዲሁም አብዛኛው ወንዶች ከአምሳ ኪሎ በትንሽ በለጥ እንደሚሉ ነው።

ቴይለርም የእየሱስን ውጫዊ አካላዊ አቋም በተመለከተ ተመሳሳይ መደምደሚያ ላይ ደርሷል።

" በዚያን ወቅት የነበሩ ይሁዳውያን አሁን ካሉት ኢራቃውያን ጋር ይመሳሰላሉ። ሳስበው እየሱስ ጠቆር ያለ ወይም ቡናማ ቀለም ፀጉር ነበረው፤ ቡናማ አይኖችና ጠየም ያለ ቆዳ ያለው እንደ መካከለኛ ምስራቃዊ ሰው ይመስለኛል" ይላሉ።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ጠየም ያለና ረዥም ፀጉር

ብራዚላዊው የግራፊክ ዲዛይነር ባለሙያ ሲሴሮ ሞራኤስ የእየሱስን ፊት ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ምን ሊመስል እንደሚችል ቀርፆት ነበር።

ሞራኤስ እንደሚለው "እየሱስ በርግጠኛነት ጥቁር ነበር። በተለይም በቀጠናው የነበረውን መልክ በማየት፤ እንዲሁም በበረሀና ሀሩር ፀሀይ ባለበት የሚኖሩ ወንዶችን በማጥናት ነው እዚህ መደምደሚያ ላይ የደረስኩት" ይላሉ።

ሌላኛው ጥያቄ የእየሱስ ፀጉር ነው። የመፅሀፍ ቅዱስም አንዱ ክፍል በሆነው በጳውሎስ ወደ ቆሮንቶስ መልዕክት "ወንድ ልጅ ረዥም ፀጉር ሊኖረው ነውር ነው" ስለሚል ብዙ ጊዜ እንደሚሳለው እየሱስ ረዥም ፀጉር ሊኖረው አይችልም።

"በሮማውያን ዘንድ ለወንድ ተቀባይነት ያለው የተላጨ ፂምና አጭር ፀጉር ነበር። ምናልባት በጥንት ጊዜ ፈላስፋዎች ፂማቸውን ያስረዝሙ ነበር" በማለት የታሪክ ምሁሩ ይናገራሉ።

ፕሮፌሰር ሊዮናርዶ ቼቪታሪዝ "ታሪካዊው እየሱስ፡ አጭር መግቢያ" የሚለው መፅሀፍ ደራሲ ሲሆኑ ሶስተኛው ክፍለ-ዘመን ላይ የነበረው የእየሱስ ምስል ወጣትና አጭር ፀጉር የነበረው ነው ይላሉ።

"ከፂማም አምላክ ይልቅ ወጣት ፈላስፋና መምምህር ነበር የሚመስለው" በማለት ይገልፃሉ።

ዊልማ ስቴጋል የተባሉ በብራዚል በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ የስነ-መለኮት ተመራራማሪ ክርስትና ጅማሮ ላይ የተለያየ ገፅታ እንደነበረው ከነዚህም ውስጥ በጊዜው እንደነበሩ ፈላስፋና መምህራን ፂም፤ ፂም የሌለው እንዲሁም ከጭንቅላቱ ጀርባ የፀሀይ አምላክ እንደሆነ ተደርጎ ይሳል ነበር።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

መለኮታዊ ገፅታ

ቴይለር በበኩላቸው እነዚህ ምስሎች ለዘመናት እየሱስን መለኮታዊ ገፅታ እንዳለው፣ የአምላክ ልጅ አድርገው ሲሆን የሰው ልጅ የሆነውን እየሱስን አይስሉትም ነበር።

"ይህ ሁሌም የሚያስደንቀኝ ነገር ነው። እየሱስን ባየው ደስ ይለኝ ነበር" በማለት ይናገራሉ።

ፂም የተሞላበት ፊት ያለው የእየሱስ ምስል በመካካለኛው ክፍለ-ዘመን በተለይም በባይዛንታይን ኢምፓየር ከፍተኛ ዕውቅናን አግኝቷል።

ፕሮፌሰር ቼቪታይዝ እንደሚሉት የእየሱስ ምስል የሚሳለው እንደ ዘመኑ ከነበሩት ነገስታት አካላዊ ገፅታ ሉዓላዊነትን በተጎናፀፈ መልኩ ነበር።

የማህበረሰብ አጥኚው ፍራንቼስኮ ቦርባ ሪቤይሮ ኔቶ በሳኦ ፖሎ በሚገኘው የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪ ሲሆኑ እሳቸው እንደሚሉትም " በታሪክ ውስጥ የእየሱስ ገፅታ በክርስትና መጀመሪያ ወቅት ፍልስጥኤማውያንን መምሰሉ ለብዙዎች አሳሳቢ ጉዳይ አልነበረም" ይላሉ።

በምስራቃዊ ካቶሊክ ቤተክርስቲያኖች ዘንድ የእየሱስ ገፅታን ለመሳል ጥብቅ የሆነ ህግም በማውጣት፤ ከአለማዊው ውጭም መንፈሳዊ የሆኑ ጥበቦችንም ሊያሳይ ይገባል ተብሎ እንደሚታመን ይናገራሉ።

" ከተለያዩ ሰዎች ጋር በሚሳልበት ወቅት ከሁሉም ተለቅ ብሎ እንዲታይና ሲሆን ይህም ያለውን ታላቅነት ምሳሌ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በመስቀል ላይ ተሰቅሎም በህይወት እንዳለና ከአጠቃላይ ፀጋው ጋር ነው የሚሳለው" ይላሉ።

የምዕራቡ ዓለም ቤተክርስቲያን እነዚህን ህግጋትንም ሆነ ባህል ስለማይከተሉ በዘመናትም ውስጥ የእየሱስን ምስል በዘፈቀደና እንደፈለጉት አድርገው ይስሉ ነበር ይላሉ።

በእምነቶች ላይ ያሉ ታሪካዊ ሰዎች የባህል የበላይነት ያለበት አካል ነፀብራቅ እየሆኑ እንደመጡ ይናገራሉ።

የእየሱስ ክርስቶስ ምስል ሰማያዊ አይን መሆንና ብሎንድ ፀጉር ያለው መሆኑ ችግር የለውም ችግሩ የሚመነጨው ግን ይህ መለኮታዊ ኃይል መወከል ያለበት በአውሮፓውያን ነው ተብሎ ሲታሰብ ነው ይላሉ።

በፖርቹጋል ቅኝ ግዛት ስር በነበረችው ጥንታዊ ቻይና በቻይና አለባበስ ተስሏል እንዲሁም በኢትዮጵያ ጠይም መልክ ያለው የእየሱስ ምስሎችም እንዳሉ ይገልፃሉ።