የፕሪሚዬር ሊጉ ምርጥ 11 ተጫዋቾች

ፖል ፖግባ Image copyright Matthew Peters

መሪው ማንችስተር ሲቲ በገዛ ሜዳው በዩናይትድ በተሸነፈበት፤ ሊቨርፑል እና ቼልሲ ነጥብ በጣሉበት እንዲሁም አርሴናል እና ቶተንሃም እያንዳንዳቸው ሶስት ነጥብ ባገኙበት ሳምንት የትኞቹ ተጫዋቾች ጎልተው ወጡ? ጋርዝ ክሩክስ ምላሽ አለው።

ግብ ጠባቂ፡ - ጆ ሃርት (ዌስትሃም)

Image copyright BBC Sport

የሚገርም ብቃት ከጆ ሃርት! ሃርት እንደዚህ መጫወት ከቀጠለ የግብ ጠባቂ እጥረት ለገጠማት እንግሊዝ ምላሽ ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለሁ።

ቡድኑ ዌስትሃም ከቼልሲ ባደረገው ጨዋታ ያዳናቸው ኳሶች በጣም የሚገርሙ ነበሩ። በተለይ የማርከስ አሎንሶን ኳስ ያዳነበት መንገድ የሚደንቅ ነበር።

ተከላካዮች፡ - ሲመስ ኮልማን (ኤቨርተን)፣ አሽሊ ያንግ እና ክሪስ ስሞሊንግ (ዩናይትድ)፣ ሴዛር አዝፕሊኬታ (ቼልሲ)

Image copyright BBC Sport

ሲመስ ኮልማን ከጉዳት ተመልሶ ለኤቨርተን ድንቅ ብቃት ሲያሳይ መመልከት ያስደስታል። ወደ ቀደመ አቋሙ እንደተመለሰ ባሳየበት ፍልሚያ ለሊቨርፑሎች ፈተና ሆኖ ነበር የዋለው።

አሽሊ ያንግ አሁንም በጣም የሚደንቅ አቋም ከማሳየት ወደኋላ እያለ አይደለም። በያዝነው ውድድር ዓመት የያንግ አቋም እጅጉን የበሰለ ሆኖ ተገኝቷል። ከሲቲ ጋር በነበረው ጨዋታ ከማንኛውም የቡድን አጋሩ በላቀ አራት ጎል ሊሆኑ የሚችሉ ኳሶችን በማዳን አስፈላጊነቱን አስመስክሯል።

ክሪስ ስሞሊንግን በዚህ ሳምንት ምርጥ አስራአንድ ውስጥ ላካትተው የቻልኩበት ዋነኛው ምክንያት በኮምፓኒ ጎል ስሜቱ ሳይጎዳ ተመልሶ ጠንካራ ሆኖ መገኘቱ ነው። በመከላከሉ ላይ የጎላ ሚና ከመጫወቱም በላይ የማሸነፊያዋን ጎል ማስቆጠር መቻሉም በጣም የሚያስሞግሰው ነበር።

ሴዛር አዝፕሊኬታለቼልሲ ወሳኝ መሆኑን አሁንም እያስመሰከረ ነው። ዕድሜ ለአዝፕሊኬታ ይሁንና ቼልሲ አንድ ነጥብ ይዞ መውጣት ችሏል።

አማካዮች፡ - ጆንጆ ሼልቪ (ኒውካስል)፣ ሉካ ሚሊቮጄቪች (ክሪስታል ፓላስ)፣ ፖል ፖግባ (ዩናይትድ)

Image copyright BBC Sport

ጆንጆ ሼልቪቡድኑ ከ2016 የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ዋንጫ አሸናፊ ሌይስተሮች ጋር በነበረው ፍልሚያ ያሳየው አቋም ጥሩ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም አቋሙ ላይ ትልቅ ለውጥ መታየት ችሏል።

ሉካ ሚሊቮጄቪችበያዝነው የውድድር ዘመን 12 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል። እኚህ ጎሎች ለቡድን ክሪስታል ፓላስ ትልቅ ሚና አላቸው። ለጓደኞቹ የሚያቀብላቸው ካሶችም እጅግ ግሩም ነበሩ።

ፖል ፖግባ ለደርቢው አጊጦበት የመጣው የፀጉር ቁርጥ ብቻ ሳይሆን የአጨዋወት ስታይሉም ለየት ያለ ነበር። ለተቃራኒ ቡድን አስጨናቂና ያልተጠበቀ አቋም ማሳየትም ይችልበታል። ተቀናቃኙ ሲቲ ላይም ያደረገው ይህን ነበር። ፖግባ ሁለት ጎሎችን በማስቆጠር የቡድን አጋሮቹን ሰሜት ከማነቃቃቱም በላይ በ6 ዓመታት ውስጥ ሊጉን የሚመራ ቡድን ላይ ሁለት ጎል ያስቆጠረ ተጫዋች ሆኗል።

አጥቂዎች፡ - ክሪስትያን ኤሪክሰን (ቶተንሃም)፣ ዊልፍሬድ ዛሃ (ክሪስታል ፓላስ)፣ ማርኮ አርቶቪች (ዌስት ሃም)

Image copyright BBC Sport

ክሪስትያን ኤሪክሰን በስቶክ ሜዳ ላይ ነግሶ ነበር የዋለው። ቶተንሃሞች ቼልሲን በሜዳው በረቱ በሳምንቱ ስቶክንም በሜዳው መርታታቸው ድንቅ ብቃት ላይ እንዳሉ ማሳያ ነው። ለዚህ ደግሞ የኤሪክሰን አስተዋፅኦ የሚናቅ አይደለም።

ዊልፍሬድ ዛሃ በዚህ የውድድር ዘመን ለቡድኑ ያበረከተው የትየለሌ ነው። አምስት ኳሶች ወደጎል ሞክሮ ሶስት የተሳኩ ሲያገኝ አንድ ማስቆጠር ችሏል።

ማርኮ አርቶቪች አነሆ ሌላ ድንቅ ብቃት ማሳየት ችሏል። ለቺቻሪቶ አመቻችቶ ያቀበላት ኳስም በጣም አሪፍ ነበረች።

ተያያዥ ርዕሶች