የላውሮ የፕሪምየር ሊግ እና ኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታዎች ግምት

የቢቢሲው ስፖርት ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን

ቅዳሜ ዕለት ቶተንሃም እና ማንቸስተር ዩናይትድ በኤፍ ኤ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ ቦታ ለማግኘት በዌምብሌይ ይፋለማሉ።

በፕሪምየር ሊጉ ዌስት ብሮምና ሊቨርፑል በሚያደረጉት ጨዋታ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ነጥብ ይጥላሉ ያለው ላውሮ ጨዋታው 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ይጠናቀቃል ሲል ክሪስታል ፓላስ ደግሞ ዋትፎርድን 2 ለ 1 የሸንፋል በማለት ግምቱን አስቀምጧል።

በሌላኛው የቅዳሜ ጨዋታ፤ ቶተንሃም እና ማንቸስተር ዩናይትድ በኤፍ ኤ ካፕ ሩብ ፍጻሜ ይገናኛሉ። እንደ ላውሮ ግምት ከሆነ ጨዋታው 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቆ ዩናይትዶች በመለያ ምት ያሸንፋሉ።

እሁድ- ቼለሲ ከ ሳውዝሃምፕተን በሚያደርጉት የኤፍ ኤ ካፕ ሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ደግሞ፤ ቼልሲ 2 ለ ባዶ ያሸንፋል ሲል ግምቱን አስቀምጧል።

ስቶክ ከ በርንሌየይ 1 ለ 1 አቻ የይያያሉ የያለው ላውሮ፤ አርሰናልን ከዌስትሃም በሚያገናኘው ፕሪምየር ሊጉ አርሰናል 2 ለ ባዶ ያሸንፋል ሲል ገምቷል።

ሻምፒየኖቹ ማንቸስተር ሲቲዎች ከስዋንሲ ሲጫወቱ፤ በላውሮ ግምት ሲቲዎች 3 ለ ባዶ ያሸንፋሉ።

ሰኞ- ኤቨርተን ኒውካስልን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ያሸንፋልም ብሏል ላውሮ።

ተያያዥ ርዕሶች